ሰቈቃወ INTRO1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)መግቢያ ሰቈቃወ ኤርምያስ፥ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስት መቶ ሰማንያ ሰባት ዓመት ኢየሩሳሌም በመፍረስዋና ሕዝብዋም በመሰደዱ ምክንያት የቀረቡ አምስት የኀዘን ቅኔዎች ስብስብ ነው። የመጽሐፉ አብዛኛው ክፍል ስለ ለቅሶና ስለ ኀዘን የሚያወራ ቢሆንም እንኳ፥ በእግዚአብሔር ስለ መታመንና በተስፋ ስለ መኖር የሚናገር ክፍልም ይገኝበታል፤ አይሁድ በአምስት መቶ ሰማንያ ሰባት ዓመት ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በሀገሪቱ ላይ የደረሰውን ጥፋት ለማስታወስ በጾምና በኀዘን ዓመታዊ የአምልኮ ሥርዓቶችን በሚፈጽሙባቸው ቀኖች ውስጥ እነዚህን ቅኔዎች ይዘምሯቸዋል። አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት የመጀመሪያው ሰቆቃ (1) የኢየሩሳሌም መከራና ኀዘን (1፥1-22) ሁለተኛው ሰቆቃ (2) እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ላይ ያመጣው ቅጣት (2፥1-22) ሦስተኛው ሰቆቃ (3) የተስፋ መልእክት (3፥1-66) አራተኛ ሰቆቃ (4) የኢየሩሳሌም ጥፋት (4፥1-22) አምስተኛው ሰቆቃ (5) ምሕረት ለማግኘት የሚደረስ ጸሎት (5፥1-22) ምዕራፍ |