Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa

መጽሐፈ ዮዲት 10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


ዮዲትና ሆሎፎርኒስ ዮዲት ወደ ሆሎፎርኒስ ሰፈር ሄደች

1 ስለዚህ ዮዲት ወደ እስራኤል አምላክ መጮዃን ከጨረሰች በኋላና እነዚህን ቃላት መናገር ከፈጸመች በኋላ፥

2 ከወደቀችበት ተነሣች፤ አገልጋይቷን ጠርታ በሰንበታትና በበዓላት ቀኖች ወደምትቀመጥበት ቤት ወረደች።

3 የለበሰችውን ማቅ አወለቀች፤ የመበለትነት ልብስዋን ተወች፥ ሰውነትዋንም በውኃ ታጠበች፥ ጥሩ ሽቶ ተቀባች፤ ጠጉርዋን አበጠረች፥ በራስዋም ላይ ሻሽ አደረገች፤ ባሏ ምናሴ በሕይወት በነበረበት ጊዜ ትለብሰው የነበረውን የደስታ ልብስዋን ለበሰች።

4 ጫማዋን አደረገች፥ አምባርዋን፥ አልቦዋን፥ ቀለበትዋን፥ ጉትቻዋንና ጌጥዋን ሁሉ አደረገች፤ የሚያዩአትን ወንዶች ሁሉ ዐይን ለማማለል እራሷን እጅግ አስዋበች።

5 አገልጋይዋን የወይን አቁማዳ፥ የዘይት ማሰሮ አስያዘቻት፤ በከረጢት ውስጥ በሶና የደረቅ በለስ ፍሬ፤ ቂጣ ሞላች፤ ዕቃዎቿን ሁሉ በደንብ ጠቀለለችና አገልጋይዋን አሸከመቻት።

6 ወደ ቤቱሊያ ከተማ በር ሄዱ፤ በዚያም ዑዚያንና የከተማይቱን ሽማግሌዎች ካብሪስንና ካርሚስን አገኙአቸው።

7 ፊትዋ በጣም ተለውጦ እና የተለየ ልብስ ለብሳ ባዩአት ጊዜ በውበትዋ እጅግ ተደነቁ፤ እንዲህም አሏት፦

8 “ለእስራኤል ልጆች ክብርና ለኢየሩሳሌም ልዕልና የአባቶቻችን አምላክ ሞገስን ይስጥሽ፥ ዕቅድሽንም ያሳካልሽ።”

9 እርሷም ለእግዚአብሔር ሰገደች፤ እንዲህም አለቻቸው፦ “ከእኔ ጋር የተነጋገራችሁበትን ነገር ወጥቼ እንድፈጽም የከተማይቱን በር እንዲከፈትልኝ እዘዙ።” እርሷ እንደ ጠየቀችው እንዲከፍቱላት ጐልማሶቹን አዘዙአቸው።

10 በከፈቱላትም ጊዜ ዮዲት ወጣች፥ አገልጋይቷም ከእርሷ ጋር፤ የከተማይቱ ሰዎች ተራራውን እስክትወርድና ሸለቆውን አልፋ እስክትሄድ ድረስ ይመለከቷት ነበር፤ ከዚያ በኋላ ግን ሊያዩአት አልቻሉም።

11 በቀጥታ በሸለቆው ሄዱ፤ የአሦርያውያን ዘበኞች አገኙአት።

12 ያዟትና እንዲህ ሲሉ ይጠይቋት ጀመር፦ “ከማን ወገን ነሽ? ከየት ትመጫለሽ? ወዴትስ ትሄጃለሽ?” እርሷም እንዲህ ስትል መለሰችላቸው፤ “እኔ የዕብራውያን ልጅ ነኝ፥ ለእናንተ መብል እንዲሆኑ ተላልፈው ሊሰጡ ስለሆነ ከእነርሱ ፊት ጠፍቼ መጣሁ።

13 እኔ የመጣሁት የሠራዊቶቻችሁ ዋና የጦር አዛዥ የሆነውን ሆሎፎርኒስን ለማግኘትና ለእርሱ እውነተኛ ነገርን ለመንገር ነው፤ ከሰዎቹ አንድም ሳይሞትበት ተራራማውን አገር በሙሉ መያዝ እንዲችል መከተል የሚገባውን መንገድ አሳየዋለሁ”።

14 ሰዎቹ ቃሏን በሰሙ ጊዜና ፊትዋንም ባዩ ጊዜ፥ በውበትዋ በዓይናቸው የምትደነቅ ሆና አገኙአት፥ እንዲህም አሏት፦

15 “ወደ ጌታችን ለመቅረብ በፍጥነት ወርደሽ በመምጣትሽ ሕይወትሽን አዳንሽ፤ አሁንም ወደ ድንኳኑ ሂጂ፤ ከእኛ መካከል ጥቂቶቹ ወደ እርሱ ያደርሱሻል፥ በእጁም ያስረክቡሻል።

16 በፊቱ በቆምሽ ጊዜ ልብሽ አይፍራ፥ ይህንን ቃልሽን ንገሪው፤ መልካም ያደርግልሻል።”

17 ከእርሷና ከአገልጋይዋ ጋር የሚሔዱ መቶ ሰዎች ከእነርሱ መካከል መረጡ፤ ወደ ሆሎፎርኒስ ድንኳንም አደረሱአቸው።

18 በየድንኳኑ ስለ ዮዲት መምጣት ተወርቶ ነበርና በሰፈሩ ሁሉ ታላቅ መደነቅ ሆነ፥ መምጣቷንም እስኪነግሩላት ድረስ ከሆሎፎርኒስ ድንኳን ውጭ ቆማ በመጠበቅ ላይ ሳለች ሰዎች በዙሪያዋ ተሰበሰቡ።

19 በውበቷ ተደነቁ፥ በእርሷም ምክንያት የእስራኤልን ልጆች አደነቁ፥ እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ፦ “እንዲህ ያሉ ሴቶች ያሉትን ሕዝብ የሚንቀው ማነው? ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳ ማስቀረት መልካም አይደለም፥ ከተውናቸው ምድሪቱን ሁሉ ሊስቡ ይችላሉ።”

20 በሆሎፎርኒስ አጠገብ የሚገኙ ጠባቂዎችና አገልጋዮቹ ሁሉ መጥተው ወደ ድንኳኑ አስገቧት።

21 ሆሎፎርኒስ በከፋይ፥ በወርቅ፥ መርገድና በከበረ ድንጋይ በተሠራ መጋረጃ ውስጥ በአልጋው ላይ ተጋድሞ ነበር።

22 ስለ እርሷ በነገሩት ጊዜ የብር መቅረዝ መብራት በፊቱ ተይዞ ወደ ድንኳኑ ሰፊ ስፍራ መጣ።

23 ዮዲት በሆሎፎርኒስና በጦር አለቆቹ ፊት በመጣች ጊዜ፥ በቁንጅናዋ ሁሉም ተደነቁ፤ እርሷም በግንባርዋ ተደፍታ እጅ ነሣችለት፥ አሽከሮቹ ግን አነሷት።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos