Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዕዝራ INTRO1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1

መግቢያ
መጽሐፈ ዕዝራ የሁለቱ ዜና መዋዕል መጻሕፍት ተከታይ ሲሆን የሚተርከውም ጥቂት የአይሁድ ስደተኞች ከባቢሎን ስለ መመለሳቸውና በኢየሩሳሌም የሕይወትና የአምልኮ ተሐድሶ ስለ መከሠቱ ነው፤ እነዚህም ሁኔታዎች በሚከተለው ደረጃ ቀርበዋል፦
1. በፋርስ ንጉሠ ነገሥት በቂሮስ ፈቃድ የመጀመሪያዎቹ አይሁድ ስደተኞች ከባቢሎን ተመለሱ።
2. ቤተ መቅደሱ እንደገና ታንጾ ተመረቀ፤ አምልኮተ እግዚአብሔርም በኢየሩሳሌም እንደገና ተጀመረ።
3. ከብዙ ዓመቶች በኋላ የእግዚአብሔር ሕግ ምሁር በነበረው በዕዝራ መሪነት ሌሎች የአይሁድ ስደተኞች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ዕዝራ የእስራኤልን መንፈሳዊ ቅርስ ወደ ነበረበት ለመመለስ ሕዝቡ የመንፈሳዊውንና የሥጋዊውን ኑሮ እንደገና እንዲያደራጁ ረዳቸው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የአይሁድ ከምርኮ ወደ ሀገራቸው መመለስ (1፥1—2፥70)
የመሠዊያው እንደገና መሠራትና የቤተ መቅደሱ ሥራ መጀመር (3፥1—4፥5)
ኢየሩሳሌምን እንደገና በመሥራት ላይ የተከሠተ ችግር (4፥6-23)
የቤተ መቅደሱ ሥራ መጠናቀቅ (4፥24—6፥22)
ዕዝራ አይሁድን ወደ ኢየሩሳሌም መርቶ መሄዱ (7፥1—8፥36)
ዕዝራ አሕዛብ ሴቶችን ያገቡ ወንዶች እንዲፈቱ ማስገደዱ (9፥1—10፥44)
ምዕራፍ

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos