Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa

መጽሐፈ ባሮክ 4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ይህች የእግዚአብሔር ትእዛዝ መጽሐፍና ለዘለዓለም የምትኖር ሕግ ነች። አጥብቀው የሚይዟት ሁሉ በሕይወት ይኖራሉ፥ የሚተዉአት ይሞታሉ።

2 ያዕቆብ ሆይ ተመለስና ያዛት፤ ወደ ብርሃንዋ ጮራም ሂድ።

3 ክብርህን ለሌላ አትስጥ፥ ጥቅምህን ለባዕድ አትስጥ።

4 እስራኤል ሆይ እኛ የተባረክን ነን፤ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘው ነገር ተገልጦልናልና!


የኢየሩሳሌም ቅሬታዎችና ተስፋዎች

5 የእስራኤል መታሰቢያ፥ ሕዝቤ ሆይ በርቱ፤

6 ለአሕዛብ ተሽጣችሁ ነበር ለጥፋት ግን አይደለም፥ ነገር ግን እግዚአብሔርን በማስቆጣታችሁ ለጠላቶቻችሁ ተላልፋችሁ ተሰጥታችሁ ነበር።

7 ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለአጋንንት በመሠዋት ፈጣሪያችሁን በጣም አስቆጣችሁት።

8 የተንከባከባችሁን ዘላለማዊ አምላክ ረስታችሁታል፥ ያሳደገቻችሁን ኢየሩሳሌምንም አሳዝናችኋል።

9 የእግዚአብሔር ቁጣ በእናንተ ላይ ሲመጣ ባየች ጊዜ እንዲህ አለች፦ “የጽዮን ጐረቤቶች ስሙ፥ እግዚአብሔር ጽኑ ኀዘን አምጥቶብኛል፤

10 ዘላለማዊ አምላክ ያመጣባቸውን ወንዶች ልጆቼንና የሴቶች ልጆቼን መማረክ አይቻለሁና።

11 በሐሴት አሳደግኋቸው፥ ነገር ግን በልቅሶና በኀዘን ሸኘኋቸው።

12 በብዙዎች በተጣልሁት፥ በመበለቷ በእኔ ማንም ደስ አይበለው፤ በልጆቼ ኃጢአት ምክንያት ባዶ ቀርቻለሁ፥ ከእግዚአብሔር ሕግ ርቀዋልና።

13 ትእዛዞቹን አላወቁም፤ በእግዚአብሔር ትእዛዛት መንገድ አልተከተሉም፤ በሱ ጽድቅ መሠረት የተማሩትን ተከትለው አልሄዱም።

14 የጽዮን ጐረቤቶች ይምጡ፤ ዘላለማዊው ያመጣባቸውን የወንዶች ልጆቼና የሴቶች ልጆቼ መማረክ አስታውሱ።

15 የማያፍር፥ ባዕድ ቋንቋ የሚናገር፥ ሽማግሌን የማያከብርና ለሕፃን የማይራራ ሕዝብ ከሩቅ አመጣባቸው።

16 የመበለትዋን የተወደዱ ልጆች ነጠቁ፤ ከሴቶች ልጆችዋም ለይተው ብቻዋን አስቀሩአት።

17 ነገር ግን እኔ እንዴት ልረዳችሁ እችላለሁ?

18 ይህን ክፉ ነገር ያመጣባችሁ እርሱ ከጠላቶቻችሁ እጅ ያወጣችኋልና።

19 ሂዱ ልጆቼ ሂዱ፤ እኔ ምድረ በዳ ሆኜ ተትቻለሁና።

20 የሰላም ልብሴን አወለቅሁ፥ ለልመናዬም ማቅን ለበስሁ፤ በዘመኔን ሁሉ ወደ ዘላለማዊው እጮሃለሁ።

21 ልጆቼ ጽኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ጩኹ፤ ከጠላቶቻችሁ አገዛዝና እጅ ያወጣችኋል።

22 እንዲያድናችሁ ተስፋዬን በዘላለማዊ አድርጌአለሁና፥ ከዘላለማዊው አዳኛችሁ ፈጥኖ ስለሚመጣላችሁ ምሕረት፥ ከቅዱሱ ደስታ መጣልኝ።

23 እኔ በኀዘንና በልቅሶ ሸኝቻችኋለሁና፥ ነገር ግን እግዚአብሔር በደስታና በሐሤት እናንተን መልሶ ለዘለዓለም ለእኔ ይሰጣችኋል።

24 የጽዮን ጎረቤቶች አሁን መማረካችሁን እንዳዩ፥ እንዲሁም ከታላቅ ክብርና ከዘላለማዊው ውበት ጋር ከእግዚአብሔር ወደ እናንተ የሚመጣውን መዳናችሁን ፈጥነው ያያሉ።

25 ልጆቼ ከእግዚአብሔር የመጣባችሁን ቁጣ በትዕግሥት ተቀበሉ፤ ጠላቶቻችሁ አሳደድዋችሁ፥ ነገር ግን ውድቀታቸውን በፍጥነት ታያላችሁ፤ አንገታቸውንም ትረግጣላችሁ።

26 ለግላጋ ልጆቼ በሻከረው መንገድ ሄዱ፤ እንደ ተዘረፉ መንጋዎች በጠላቶች ተወስደው ነበር።

27 ልጆቼ ጽኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ጩሁ፤ ይህን ያመጣባችሁ እርሱ ያስባችኋልና፤

28 ከእግዚአብሔር በፈቃዳችሁ እንደራቃችሁ፥ አሁን ደግሞ እርሱን ለመፈለግ በአስር እጥፍ ተመለሱ።

29 እነዚህን መከራዎች በእናንተ ላይ ያመጣባችሁ እርሱ ዘላለማዊ ደስታን ከድኅነታችሁ ጋር ያመጣላችኋል።

30 ኢየሩሳሌም ሆይ ጽኚ፥ ስምሽን የሰጠሽ እሱ ያጽናናሻልና።

31 መከራ ያጸኑብሽና በውድቀትሽ የተደሰቱ ሰዎች ይጐሰቁላሉ።

32 ልጆችሽ ባርያዎች የሆኑባቸው ከተሞች ይጐሰቁላሉ፤ ልጆችሽን የተቀበሉ ከተሞች ይጐሰቁላሉ።

33 በውድቀትሽ እንደ ተደሰተች፥ በመጥፋትሽም ሐሤት እንደ አደረገች፥ በራሷ መጥፋት ታዝናለች።

34 ደስተኞች ሕዝቦቿን እነጥቃታለሁ፥ ትምክሕቷ ወደ ኀዘን ይለወጥል።

35 ከዘላለማዊው እሳት ለብዙ ቀኖች ይመጣባታልና፥ ለብዙ ዘመንም የአጋንንት መኖሪያ ትሆናለችና።

36 ኢየሩሳሌም ሆይ ወደ ምሥራቅ ተመልከቺ፥ ከእግዚአብሔር የሚመጣልሽንም ደስታ እዪ፤

37 እነሆ የላክሻቸው ልጆችሽ መጡ፤ በእግዚአብሔር ክብር እየተደሰቱ፥ በቅዱሱ ቃል ከምሥራቅና ከምዕራብ ተሰበሰቡ።”

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos