Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -


This book is not inspired by God and is not part of the Christian canon or the Jewish Tanakh. It is shown only for historical and study purposes. View full explanation

መጽ​ሐፈ ጦቢት 3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የጦ​ቢት ጸሎት

1 ከዚ​ህም በኋላ በልብ ጭን​ቀት ተከ​ዝሁ፤ አል​ቅ​ሼም ጸለ​ይሁ።

2 እን​ዲ​ህም አልሁ፥ “አቤቱ በሥ​ራህ ሁሉ በቸ​ር​ነ​ትና በፍ​ርድ፥ በሚ​ገባ ጽድ​ቅም አንተ እው​ነ​ተኛ ነህ፤ አቤቱ አንተ በሚ​ገባ ዓለ​ምን ትገ​ዛ​ለህ።

3 አስ​በኝ፤ ተመ​ል​ከ​ተ​ኝም፤ በራሴ ኀጢ​አ​ትና አን​ተን በበ​ደሉ፥ ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንም ባል​ሰሙ በአ​ባ​ቶች ኀጢ​አት አት​በ​ቀ​ለኝ።

4 ለመ​በ​ር​በ​ርና ለመ​ማ​ረክ፥ ለመ​ገ​ደ​ልም አደ​ረ​ግ​ኸን፤ በዓ​ለሙ ሁሉና በው​ስ​ጣ​ቸው በተ​በ​ተ​ን​ባ​ቸው በአ​ሕ​ዛ​ብም ዘንድ መተ​ረ​ቻና መዘ​ባ​በቻ ሆንን።

5 አሁ​ንም እው​ነ​ተኛ ፍር​ድህ ብዙ ነው፤ የእኔ ኀጢ​አ​ትና የአ​ባ​ቶች ኀጢ​አ​ትም እን​ዲ​ሰ​ረይ አድ​ር​ግ​ልኝ፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህን አላ​ደ​ረ​ግ​ን​ምና፥ በፊ​ት​ህም በእ​ው​ነት አል​ሄ​ድ​ን​ምና።

6 አሁ​ንም በፊ​ትህ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን በእኔ አድ​ርግ፤ ከመ​ኖር መሞት ይሻ​ለ​ኛ​ልና በሞት እሰ​ና​በት ዘንድ፥ መሬ​ትም እሆን ዘንድ ነፍ​ሴን የሚ​ቀ​በ​ላ​ትን እዘ​ዝ​ልኝ። በሐ​ሰ​ትና በው​ር​ደት ተግ​ዳ​ሮ​ትን ሰም​ቻ​ለ​ሁና፥ ኀዘ​ንም በእኔ ላይ በዝ​ት​ዋ​ልና ከመ​ከ​ራዬ እሰ​ና​በት ዘንድ፥ ወደ ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ቦታም እሄድ ዘንድ እዘዝ፤ ፊት​ህ​ንም ከእኔ አት​መ​ልስ።”

7 በዚ​ያ​ችም ቀን በሜ​ዶን ክፍል በጣ​ኔስ የራ​ጉ​ኤል ልጅ ሣራን ከአ​ባ​ትዋ ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮች ተግ​ዳ​ሮት አገ​ኛት።

8 ለሰ​ባት ወን​ዶች አጋ​ብ​ተ​ዋት እንደ ወን​ድና ሴት ሳይ​ቃ​ረቡ አስ​ማ​ን​ድ​ዮስ የሚ​ባል ክፉ ጋኔን ገድ​ሏ​ቸ​ዋ​ልና፤ እን​ዲ​ህም አሏት፥ “ባሎ​ችሽ እየ​ታ​ነቁ እን​ደ​ሚ​ሞቱ አታ​ው​ቂ​ምን፦ እነሆ ሰባቱ አገ​ቡሽ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ ስንኳ አል​ተ​ከ​ተ​ለ​ሽም።

9 እን​ግ​ዲህ ስለ እነ​ርሱ ምን አሳ​ዘ​ነን? እነ​ርሱ ሞተ​ዋ​ልና ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሂጂ፤ ከአ​ንቺ ወንድ ወይም ሴት ልጅ እስከ ዘለ​ዓ​ለሙ ድረስ አንይ።”

10 ይህ​ንም በሰ​ማች ጊዜ ለመ​ታ​ነቅ እስ​ከ​ም​ት​መኝ ድረስ እጅግ አዘ​ነች። እን​ዲ​ህም አለች፥ “እኔ ለአ​ባ​ቴና ለእ​ናቴ አን​ዲት ነኝ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ባደ​ርግ ተግ​ዳ​ሮት እሆ​ን​በ​ታ​ለሁ፤ ሽም​ግ​ል​ና​ው​ንም፥ ሰው​ነ​ቱ​ንም በጭ​ንቅ ወደ መቃ​ብር አወ​ር​ዳ​ታ​ለሁ።”


የሣራ ጸሎት

11 በመ​ስ​ኮ​ቱም በኩል ጸለ​የች፤ እን​ዲ​ህም አለች፥ “አቤቱ አንተ ፈጣ​ሪዬ ቡሩክ ነህ፤ ቅዱ​ስና ክቡር ስም​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይመ​ስ​ገን፤ ሥራ​ህም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ክቡር ነው።

12 አቤቱ አሁ​ንም ዐይ​ኖ​ች​ንና ፊቴን ለአ​ንተ ሰጠሁ።

13 እን​ግ​ዲህ ወዲህ ተግ​ዳ​ሮ​ትን እን​ዳ​ል​ሰማ ከዚህ ዓለም አሰ​ና​ብ​ተኝ አል​ኹህ።

14 ከወ​ንድ ጋር ከሚ​ሠ​ራው ኀጢ​አት ሁሉ እኔ ንጽ​ሕት እንደ ሆንኹ አቤቱ አንተ ታው​ቃ​ለህ።

15 በተ​ማ​ረ​ክ​ሁ​በ​ትም ሀገር ስሜ​ንና ያባ​ቴን ስም አላ​ሳ​ደ​ፍ​ሁም፤ እኔም ለአ​ባቴ አን​ዲት ነኝ። ወን​ድም የለ​ኝም፤ ሚስት እሆ​ን​ለት ዘንድ የም​ጠ​ብ​ቀው የቅ​ርብ ዘመ​ድም የለ​ኝም፤ ሰባቱ ባሎች ሙተ​ው​ብ​ኛ​ልና እን​ግ​ዲህ ለምን እኖ​ራ​ለሁ? ልት​ገ​ድ​ለኝ ባት​ወድ ግን ወደ እኔ ተመ​ል​ክ​ተህ ራራ​ልኝ፤ ተግ​ዳ​ሮ​ት​ንም እን​ዳ​ል​ሰማ እዘ​ዝ​ልኝ።”

16 የሁ​ለ​ቱም ጸሎ​ታ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በገ​ነነ ጌት​ነቱ ፊት ተሰማ።

17 ሩፋ​ኤ​ል​ንም ላከው፤ ሁለ​ቱን ያድ​ና​ቸው ዘንድ፥ ከጦ​ቢ​ትም ዐይን ብል​ዙን ያጠ​ፋ​ለት ዘንድ፥ የራ​ጉ​ኤል ልጅ ሳራ​ንም ሚስት ልት​ሆ​ነው ለጦ​ቢት ልጅ ለጦ​ብያ ይሰ​ጣት ዘንድ፥ ክፉ ጋኔን አስ​ማ​ን​ድ​ዮ​ስ​ንም ይሽ​ረው ዘንድ፥ ጦብያ ይወ​ር​ሳ​ታ​ልና። በዚ​ያም ወራት ጦቢት ተመ​ልሶ ወደ ቤቱ ገባ፤ የራ​ጉ​ኤል ልጅ ሳራም ከሰ​ገ​ነቷ ወረ​ደች።

Follow us:



Advertisements