Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -


This book is not inspired by God and is not part of the Christian canon or the Jewish Tanakh. It is shown only for historical and study purposes. View full explanation

መጽ​ሐፈ ጦቢት 1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከን​ፍ​ታ​ሌም ነገድ ከአ​ሳ​ሄል ወገን የገ​ባ​ኤል ልጅ የጦ​ብ​ኤል ልጅ የጦ​ቢት የነ​ገሩ መጽ​ሓፍ ይህ ነው።

2 እር​ሱም፦ ከአ​ሴር በላይ ካለች ከገ​ሊላ ንፍ​ታ​ሌም ክፍል ከቄ​ዴ​ዎስ በስ​ተ​ቀኝ ካለ​ችው ከታ​ስቢ በአ​ሦር ንጉሥ በአ​ሜ​ኔ​ሴር ዘመን የተ​ማ​ረ​ከው ነው።


የጦ​ቢት መል​ካም ሕይ​ወት

3 እኔ ጦቢት በሕ​ይ​ወቴ ዘመን በጽ​ድ​ቅና በቅ​ን​ነት መን​ገድ ሄድሁ፤ ወደ አሶር ከተማ ወደ ነነዌ ከእኔ ጋር ለመጡ ወን​ድ​ሞ​ችና ወገ​ኖች ብዙ ምጽ​ዋ​ትን አደ​ረ​ግሁ።

4 እኔም ሕፃን ሆኜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር በሀ​ገሬ ሳለሁ የአ​ባቴ የን​ፍ​ታ​ሌም ወገ​ኖች ሁሉ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በእ​ርሷ ይሠዉ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ከመ​ረ​ጣት የል​ዑል ቤተ መቅ​ደስ ለት​ው​ልድ ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ከታ​ነ​ጸ​ባ​ትና ከተ​ቀ​ደ​ሰ​ባት ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወጥ​ተው ካዱ።

5 የካዱ ሰዎ​ችም ሁሉ ደማሊ ለሚ​ባል ጣዖት ሠዉ፤ የአ​ባ​ቴም የን​ፍ​ታ​ሌም ወገ​ኖች ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ተባ​በሩ።

6 እኔ ግን በዘ​ለ​ዓ​ለ​ማዊ ትእ​ዛዝ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ እንደ ተጻፈ በበ​ዓ​ላት ቀን ብቻ​ዬን ብዙ ጊዜ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እሄድ ነበር፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያም ከሸ​ለ​ት​ሁት ከበ​ጎች ፀጕር ለአ​ሮን ልጆች ለካ​ህ​ናቱ ወደ መሠ​ዊ​ያው እወ​ስ​ድ​ላ​ቸው ነበር።

7 እህ​ሉ​ንና መጀ​መ​ሪ​ያ​ውን ዐሥ​ራት ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ለአ​ሮን ልጆች እሰ​ጣ​ቸው ነበር፤ ሁለ​ተ​ኛ​ውን እጅ ዐሥ​ራት ግን እሸ​ጠው ነበር፤ ምጽ​ዋ​ቱ​ንም አው​ጣ​ጥቼ በየ​ዓ​መቱ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እሄድ ነበር።

8 ሦስ​ተ​ኛ​ው​ንም እጅ ዐሥ​ራት የአ​ባቴ እናት ዲቦራ እን​ዳ​ዘ​ዘች ለድ​ሆች እሰጥ ነበር። አባ​ቴና እናቴ በድ​ኃ​አ​ደ​ግ​ነት ትተ​ው​ኛ​ልና፤

9 አካለ መጠን ባደ​ረ​ስ​ሁም ጊዜ ከዘ​መ​ዶች ዘር ሚስት አገ​ባሁ፤ ከር​ስ​ዋም ጦብ​ያን ወለ​ድሁ።


የጦ​ቢት ወደ ነነዌ መማ​ረክ

10 ወን​ድ​ሞ​ችና ዘመ​ዶች ሁሉ ወደ ነነዌ በተ​ማ​ረኩ ጊዜ ከአ​ሕ​ዛብ እህል በሉ።

11 እኔ ግን የአ​ሕ​ዛ​ብን እህል እን​ዳ​ል​በላ ሰው​ነ​ቴን ጠበ​ቅሁ፤

12 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ጹም ልቡ​ናዬ አስ​በ​ዋ​ለ​ሁና።

13 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሜ​ኔ​ሴር ፊት ክብ​ር​ንና ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን ሰጠኝ፤ እር​ሱም መጋቢ አድ​ርጎ ሾመኝ።

14 ወደ ምድ​ያ​ምም ሄድሁ፤ በም​ድ​ያም ክፍል በራ​ጊስ ያለ የጋ​ብ​ር​ያስ ወን​ድም ገባ​ኤ​ል​ንም ዐሥር መክ​ሊት አደራ አስ​ጠ​በ​ቅ​ሁት።

15 አሚ​ኔ​ሴ​ርም በሞተ ጊዜ በእ​ርሱ ፋንታ ልጁ ሰና​ክ​ሬም ነገሠ፤ ሥራ​ውም ክፉ ነበር፤ ከሹ​መ​ቴም ሻረኝ፤ እን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ወደ ምድ​ያም መሄ​ድን አል​ቻ​ል​ሁም።


የጦ​ቢት መል​ካም ሥራ

16 በአ​ሚ​ኔ​ሴ​ርም ዘመን ለወ​ን​ድ​ሞች ብዙ ምጽ​ዋ​ትን አደ​ረ​ግሁ።

17 እህ​ሌ​ንም ለተ​ራቡ፥ ልብ​ሴ​ንም ለተ​ራ​ቆቱ ሰጠሁ። ከወ​ገ​ኖ​ችም የሞተ ሰውን በነ​ነዌ ግንብ ሥር ወድቆ ባየሁ ጊዜ እቀ​ብ​ረው ነበር።

18 ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም ከይ​ሁዳ ሸሽቶ በተ​መ​ለሰ ጊዜ የገ​ደ​ላ​ቸ​ውን ሰዎች እኔ በስ​ውር እቀ​ብ​ራ​ቸው ነበር። እርሱ ተቈ​ጥቶ ብዙ​ዎ​ችን ገድሎ ነበ​ርና። ንጉ​ሡም ሬሳ​ቸ​ውን አስ​ፈ​ለገ፥ አላ​ገ​ኘ​ምም።

19 ከነ​ነዌ ሰዎ​ችም አንዱ ሰው ሄዶ እንደ ቀበ​ር​ኋ​ቸው ነገር ሠርቶ ከን​ጉሡ ጋር አጣ​ላኝ፤ እኔም ተሰ​ወ​ርሁ፤ ሊገ​ድ​ሉኝ እን​ደ​ሚ​ፈ​ል​ጉ​ኝም ባወ​ቅሁ ጊዜ ፈርቼ ገለል አልሁ።

20 ባጡ​ኝም ጊዜ ገን​ዘ​ቤን ሁሉ ዘረ​ፉኝ፤ ከሚ​ስቴ ሐናና ከልጄ ጦብያ በቀር ያስ​ቀ​ሩ​ልኝ የለም።

21 ሁለቱ ልጆቹ እስ​ኪ​ገ​ድ​ሉት ድረስ፥ ሸሽ​ተ​ውም ወደ አራ​ራት ተራራ እስ​ኪ​ሄዱ ድረስ አምሳ አም​ስት ቀን ከቤቴ አል​ወ​ጣ​ሁም። ልጁ አስ​ራ​ዶ​ንም በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ፤ የወ​ን​ድሜ ልጅ የአ​ና​ሔል ልጅ አኪ​አ​ኪ​ሮ​ስ​ንም በአ​ባቱ ቤት ሁሉና በሥ​ራ​ታ​ቸው ሁሉ ላይ ሾመው።

22 አኪ​አ​ኪ​ሮ​ስም ማለ​ደ​ልኝ፤ ወደ ነነ​ዌም መለ​ሰኝ። አኪ​አ​ኪ​ሮ​ስም የማ​ኅ​ተ​ምና የቤቱ ንብ​ረት ጠባቂ ነበር። አስ​ራ​ዶ​ንም ዳግ​መኛ ሾመው።

Follow us:



Advertisements