Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -


This book is not inspired by God and is not part of the Christian canon or the Jewish Tanakh. It is shown only for historical and study purposes. View full explanation

መጽሐፈ ሲራክ 51 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የሲ​ራክ ልጅ የኢ​ያሱ ጸሎት

1 አቤቱ ንጉሥ ሆይ! እገ​ዛ​ል​ሃ​ለሁ፤ አቤቱ! አም​ላ​ኬና መድ​ኀ​ኒቴ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤ በስ​ም​ህም እታ​መ​ና​ለሁ፤

2 ረድ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥ ሰው​ረ​ኸ​ኝ​ማ​ልና፥ ሰው​ነ​ቴ​ንም ከሞት አድ​ነ​ኸ​ዋ​ልና፥ ከአ​ን​ደ​በት የነ​ገር ሥራ ወጥ​መ​ድም አድ​ነ​ኸ​ኛ​ልና፥ ሐሰ​ት​ንም ከሚ​ሠ​ሩ​አት ከብዙ ሰዎች ምላስ አድ​ነ​ኸ​ኛ​ልና፥ በጠ​ላ​ት​ነ​ትም ከተ​ነ​ሡ​ብኝ ሰዎች ፊት የም​ት​ረ​ዳ​ኝና የም​ት​ሰ​ው​ረኝ ሆነ​ሃ​ልና።

3 እንደ ቸር​ነ​ትህ ብዛት መጠን፥ ስለ ስም​ህም አዳ​ን​ኸኝ፥ ይበሉ ዘንድ ያዘ​ጋ​ጁ​ትን እን​ደ​ሚ​ያ​መ​ሰኩ እን​ደ​ዚሁ ባገ​ኘ​ችኝ በመ​ከ​ራዬ ብዛት ሰው​ነ​ቴን ፈለ​ጓት።

4 ቋያ እንደ ከበ​በው፥ በእ​ሳት መካ​ከ​ልም እን​ደ​ማ​ይ​ቃ​ጠል፥

5 ከታ​ችም ከመ​ቃ​ብር ሆድ፥ ከረ​ከሰ አን​ደ​በ​ትም፥ ከሐ​ሰት ቃልም፥ አዳ​ን​ኸኝ፤

6 ወደ ንጉሥ በሚ​ያ​ጣላ ዐመ​ፀኛ አን​ደ​በት፥ ሰው​ነቴ ወደ ሞት ደረ​ሰች፤ ሕይ​ወ​ቴም ለመ​ቃ​ብር ደረ​ሰች።

7 በዙ​ሪ​ያ​ዬም ከበ​ቡኝ፤ የሚ​ረ​ዳ​ኝም አጣሁ፤ የሚ​ያ​ድ​ነኝ ሰው እን​ዳለ ብዬ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፥ ግን ማንም አል​ነ​በ​ረም።

8 አቤቱ ይቅ​ር​ታ​ህን ዐሰ​ብሁ፥ ዓለም ከተ​ፈ​ጠረ ጀምሮ የነ​በረ ሥራ​ህን ዐሰ​ብሁ፤ አን​ተን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሰዎች፥ ከጠ​ላ​ታ​ቸ​ውም የም​ታ​ድ​ና​ቸው ብፁ​ዓን ናቸ​ውና።

9 ልመ​ና​ዬ​ንም ከም​ድር ወደ ላይ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ግሁ፤ ከሞ​ትም እድን ዘንድ ጸለ​ይሁ።

10 አባ​ቴና ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ ረዳት በሌ​ለ​በት፥ ትዕ​ቢ​ተ​ኞች በተ​ነ​ሡ​በት ወራት በመ​ከ​ራዬ ጊዜ አት​ለ​የኝ አል​ሁት።

11 ስም​ህ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፤ እገ​ዛ​ል​ሃ​ለሁ፤ ምስ​ጋ​ና​ህ​ንም እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ልመ​ና​ዬ​ንም ሰማ​ኸኝ።

12 ከሞ​ትም አዳ​ን​ኸኝ፤ መከራ ከሚ​መ​ጣ​በት ቀንም አዳ​ን​ኸኝ፥ ስለ​ዚህ ነገር እገ​ዛ​ል​ሃ​ለሁ፥ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለ​ሁም። አቤቱ ስም​ህ​ንም አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ።

13 እኔ ሕፃን ሳለሁ ሳል​ሳ​ሳት ጥበ​ብን መረ​መ​ር​ኋት፤ በጸ​ሎ​ቴም መረ​ጥ​ኋት።

14 በቤተ መቅ​ደ​ስም ስለ እር​ስዋ ለመ​ንሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም እመ​ረ​ም​ራ​ታ​ለሁ።

15 ፍሬ​ዋም እንደ ተክል ፍሬ በዛ፤ ልቡ​ና​ዬም በእ​ር​ስዋ ደስ አለው፤ እግ​ሬም በእ​ው​ነት ቆመች፤ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ቴም ጀምሬ ፍለ​ጋ​ዋን ተከ​ተ​ልሁ።

16 በጆ​ሮ​ዬም ፈጽሜ አደ​መ​ጥ​ኋት፤ መረ​ጥ​ኋ​ትም፤ እኔም ብዙ ጥበ​ብን አገ​ኘሁ።

17 በእ​ር​ሷም ከፍ ከፍ አልሁ፤ ጥበ​ብን የሰ​ጠ​ኝን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ።

18 አደ​ር​ጋ​ትም ዘንድ ዐሰ​ብሁ፤ ለበጎ ነገ​ርም ቀናሁ፤ አላ​ፍ​ር​ምም።

19 ሰው​ነ​ቴም በእ​ርሷ ተበ​ረ​ታ​ታች፤ በሥ​ራ​ዬም ተራ​ቀ​ቅሁ፤ እጆ​ች​ንም ወደ ላይ አነ​ሣሁ፤ ለድ​ን​ቁ​ር​ና​ዬም አለ​ቀ​ስ​ሁ​ላት።

20 ሰው​ነ​ቴ​ንም ወደ እርሷ አቀ​ናሁ፤ በን​ጽ​ሕ​ናም አገ​ኘ​ኋት፤ ልቡ​ና​ዬ​ንም ከመ​ጀ​መ​ሪያ ጀምሮ ከእ​ር​ስዋ ጋራ አጸ​ናሁ፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ጣ​ለ​ኝም።

21 ሰው​ነ​ቴም ለእ​ር​ስዋ ታወ​ከች፤ መረ​መ​ረ​ቻ​ትም፤ ስለ​ዚ​ህም መል​ካም ሀብ​ትን ገን​ዘብ አደ​ረ​ግሁ።

22 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ደ​በ​ትን ዋጋ አድ​ርጎ ሰጠኝ፤ በእ​ር​ስ​ዋም አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ።

23 እና​ንት አላ​ዋ​ቂ​ዎች፥ ወደ እኔ ቅረቡ፤ በጥ​በብ ቤትም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።

24 እን​ዴት አጣ​ች​ኋት? እስኪ ንገ​ሩኝ! ሰው​ነ​ታ​ች​ሁስ ፈጽማ እንደ ምን ተጠ​ማች?

25 አፌን ከፍቼ፥ “ያለ ዋጋ ገን​ዘብ አድ​ር​ጓት” ብዬ ተና​ገ​ርሁ።

26 አን​ገ​ታ​ች​ሁን ዝቅ አድ​ርጉ፤ ቀን​በ​ሯ​ንም ተሸ​ከሙ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም ጥበ​ብን ትቀ​በል፤ እር​ስ​ዋን ማግ​ኘት ቅርብ ነውና።

27 እነሆ፥ ጥቂት ደክሜ በእ​ርሷ ብዙ ዕረ​ፍ​ትን እን​ዳ​ገ​ኘሁ፥ በዐ​ይ​ና​ችሁ ተመ​ል​ከቱ።

28 ከብዙ ብር ይልቅ ጥበ​ብን ምረ​ጧት፤ ቍጥር ከሌ​ለው ከወ​ር​ቅም ይልቅ ገን​ዘብ አድ​ር​ጓት።

29 ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በቸ​ር​ነቱ ደስ ይበ​ላት፤ እር​ሱ​ንም ማመ​ስ​ገ​ንን አት​ፈሩ።

30 በጊ​ዜው ዋጋ​ች​ሁን ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ፥ ጊዜው ሳይ​ደ​ርስ ሥራ​ች​ሁን ሥሩ። የሲ​ራክ ጥበብ ተፈ​ጸመ።

Follow us:



Advertisements