Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -


This book is not inspired by God and is not part of the Christian canon or the Jewish Tanakh. It is shown only for historical and study purposes. View full explanation

መጽሐፈ ባሮክ 2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “አም​ላ​ካ​ችን በእ​ኛና እስ​ራ​ኤ​ልን በገዙ መሳ​ፍ​ን​ቶ​ቻ​ችን ላይ፥ በነ​ገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ችን ላይና በመ​ኳ​ን​ን​ቶ​ቻ​ችን ላይ፥ በይ​ሁ​ዳና በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ላይ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃሉን አጸና።

2 በሙሴ ኦሪት እንደ ተጻ​ፈው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ አደ​ረ​ገው ከሰ​ማይ በታች ያል​ሆነ ክፉ ነገ​ርን በእኛ ላይ ያመጣ ዘንድ፥ ቃሉን አጸና።

3 በዚያ ወራት ሰው የወ​ን​ዶች ልጆ​ቹ​ንና የሴ​ቶች ልጆ​ቹን ሥጋ በላ።

4 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ር​ሱን በበ​ተ​ነ​በት በዙ​ሪ​አ​ችን በአሉ አሕ​ዛብ ዘንድ ለው​ር​ደ​ትና ለመ​ከራ ይሆኑ ዘንድ በዙ​ሪ​ያ​ችን በአሉ ነገ​ሥት ሁሉ እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።

5 ወራ​ዶች ሆንን፤ የከ​በ​ር​ንም አል​ሆ​ንም፤ ለቃሉ ሳን​ታ​ዘዝ አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በድ​ለ​ና​ልና።

6 ጽድቅ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ለእ​ኛና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ግን እንደ ዛሬው ዕለት የፊት ኀፍ​ረት ነው።

7 በእኛ ላይ የደ​ረ​ሰ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኛ ላይ ተና​ግሮ ነበ​ርና።

8 እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ንም ከክፉ ልባ​ችን መን​ገድ እን​መ​ለስ ዘንድ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አል​ጸ​ለ​ይ​ንም።

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ከራ ተጋ፤ በእ​ኛም ላይ አመ​ጣው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኛ ላይ ባዘ​ዘው ሥራው ሁሉ ጻድቅ ነውና።

10 በፊ​ታ​ችን በሰ​ጠን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ እን​ሄድ ዘንድ ቃሉን አል​ሰ​ማ​ንም።

11 “አሁ​ንም በጸ​ናች እጅ፥ በተ​አ​ም​ርና በድ​ንቅ ሥራ፤ በታ​ላቅ ኀይ​ልና በተ​ዘ​ጋ​ጀች ክንድ ሕዝ​ብ​ህን ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣህ፥ ዛሬም እንደ ሆነው ለራ​ስህ ታላቅ ስምን ያደ​ረ​ግህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ!

12 በደ​ልን፤ ክፉም አደ​ረ​ግን፤ አቤቱ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ! በሥ​ር​ዐ​ትህ ሁሉ ላይ የማ​ይ​ገባ ሥራን ሠራን።

13 ቍጣ​ህን ከእኛ አብ​ርድ፤ እኛን በዚያ በበ​ተ​ን​ህ​በት በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ጥቂት ቀር​ተ​ና​ልና።

14 ጌታ ሆይ! ልመ​ና​ች​ን​ንና ጸሎ​ታ​ች​ንን ስማ፤ ስለ ስም​ህም ስትል አድ​ነን፤ በማ​ረ​ኩ​ንም ሰዎች ፊት ሞገ​ስን እና​ገኝ ዘንድ ስጠን፤

15 ምድር ሁሉ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችን እንደ ሆንህ ታውቅ ዘንድ፥ ስምህ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይና በወ​ገኑ ላይ ተጠ​ር​ቶ​አ​ልና ።

16 አቤቱ ከቤተ መቅ​ደ​ስህ ሁነህ ተመ​ል​ከት፤ አቤቱ ጆሮ​ህን ወደ እኛ አዘ​ን​ብ​ለህ ስማን።

17 “ዐይ​ኖ​ች​ህን ገል​ጠህ ተመ​ል​ከት፤ አቤቱ ነፍ​ሳ​ቸው ከሥ​ጋ​ቸው የተ​ለ​የች በመ​ቃ​ብር የሚ​ኖሩ ሙታን የሚ​ያ​ከ​ብ​ሩ​ህና የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑህ አይ​ደ​ሉ​ምና።

18 ነገር ግን አዝ​ናና ተጨ​ንቃ የም​ት​ኖር፥ በብዙ መከ​ራም ያዘ​ነች ሰው​ነ​ትና የፈ​ዘዙ ዐይ​ኖች፥ የተ​ራ​በ​ችም ነፍስ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤ አቤቱ ለጽ​ድ​ቅ​ህም ይገ​ዛሉ።

19 አቤቱ አም​ላ​ካ​ችን በፊ​ትህ ምሕ​ረ​ትን የለ​መ​ን​ንህ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንና ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ችን ጽድቅ አይ​ደ​ለ​ምና።

20 በባ​ሪ​ያ​ዎ​ችህ በነ​ቢ​ያት እጅ እንደ ተና​ገ​ርህ መዓ​ት​ህ​ንና መቅ​ሠ​ፍ​ት​ህን በእኛ ላይ ሰድ​ደ​ሃ​ልና።

21 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትከ​ሻ​ች​ሁን ዝቅ አድ​ርጉ ለባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ተገዙ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ በሰ​ጠ​ኋት ምድ​ርም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤

22 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባት​ሰሙ፥ ለባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ባት​ገዙ፥

23 የደ​ስ​ታና የሐ​ሤት ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራና የሴት ሙሽራ ድምፅ ከይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውጭ ይጠ​ፋል፤ ምድ​ርም ሁሉ ከነ​ዋ​ሪ​ዎች ምድረ በዳ ይሆ​ናል።

24 ቃል​ህን አል​ሰ​ማ​ንም፤ ለባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ አል​ተ​ገ​ዛ​ንም፤ የን​ጉ​ሦ​ቻ​ችን ዐፅ​ሞ​ችና የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ዐፅ​ሞች ከቦ​ታ​ቸው እን​ደ​ሚ​ወጡ በባ​ሮ​ችህ ነቢ​ያት እጅ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውም ደረ​ሰ​ብን።

25 “እነሆ በቀን ሐሩ​ርና በሌ​ሊት ቍር ጣሏ​ቸው፤ ተማ​ረ​ክን፤ በቀ​ጠ​ናና በጦር፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ክፉ ሞትን ሞትን።

26 በእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ንና በይ​ሁዳ ወገን ኀጢ​አት ምክ​ን​ያት ስምህ የተ​ጠ​ራ​በ​ትን መቅ​ደስ እንደ ዛሬው ዕለት ጣልህ።

27 ነገር ግን አቤቱ አም​ላ​ካ​ችን! እንደ ቸር​ነ​ትህ ሁሉና እንደ ታላቁ ይቅ​ር​ታህ ሁሉ አደ​ረ​ግ​ህ​ልን፤

28 በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ሕግ​ህን ይጽፍ ዘንድ ባዘ​ዝ​ህ​ባት ዕለት በአ​ገ​ል​ጋ​ይህ በሙሴ እጅ እን​ዲህ ስትል እንደ ተና​ገ​ርህ፥

29 ቃሌን በእ​ው​ነት ባት​ሰሙ ይህች ብዛ​ታ​ችሁ እና​ን​ተን በበ​ተ​ን​ሁ​ባ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ወደ ጥቂ​ት​ነት ትመ​ለ​ሳ​ለች።

30 “እን​ደ​ማ​ይ​ሰ​ሙ​ኝም ዐወ​ቅ​ኋ​ቸው፤ አን​ገተ ደን​ዳና ሕዝብ ናቸ​ውና፤ በተ​ሰ​ደ​ዱ​በ​ትም ሀገር ወደ ፈቃ​ዳ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ።

31 እኔም አም​ላ​ካ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ። ልብን፥ ለመ​ስ​ማ​ትም ጆሮን እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።

32 ባስ​ማ​ረ​ክ​ኋ​ቸ​ውም ሀገር ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ኛል፤ ስሜ​ንም ያስ​ባሉ።

33 ከደ​ን​ዳና ልባ​ቸ​ውና ከክፉ ሥራ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የበ​ደሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም መን​ገድ ያስ​ባሉ።

34 ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ለአ​ብ​ር​ሃም፥ ለይ​ስ​ሐ​ቅና ለያ​ዕ​ቆ​ብም ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው ሀገር እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ይገ​ዙ​አ​ታ​ልም፤ እኔም አበ​ዛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም አያ​ን​ሱም።

35 አም​ላ​ካ​ቸው እሆ​ና​ቸው ዘንድ የዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳ​ንን እሠ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ሕዝቤ እስ​ራ​ኤ​ልን ከሰ​ጠ​ኋ​ቸው ሀገ​ራ​ቸው አላ​ወ​ጣ​ቸ​ውም።

Follow us:



Advertisements