Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -


This book is not inspired by God and is not part of the Christian canon or the Jewish Tanakh. It is shown only for historical and study purposes. View full explanation

መጽሐፈ ባሮክ 1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የኬ​ል​ቅዩ ልጅ የአ​ሳ​ድዩ ልጅ የሴ​ዴ​ቅ​ያስ ልጅ የማ​ሴው ልጅ የኔ​ርዩ ልጅ ባሮክ ወደ ባቢ​ሎን የጻ​ፈው ነገር ይህ ነው፤

2 በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ዓመት ከወሩ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ከለ​ዳ​ው​ያን ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን በያ​ዙ​አ​ትና በእ​ሳት በአ​ቃ​ጠ​ሏት ጊዜ፥

3 ባሮክ ይህን መጽ​ሐፍ በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​አ​ቄም ልጅ በኢ​ኮ​ን​ያን ጆሮና መጽ​ሐ​ፉን ለመ​ስ​ማት ከሕ​ዝቡ ዘንድ ወደ እርሱ በመ​ጣው ሕዝብ ሁሉ ጆሮ፥

4 በኀ​ያ​ላ​ኑና በል​ዑ​ላኑ ጆሮ፥ በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ጆሮና ከታ​ላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ በባ​ቢ​ሎን በሶዲ ወንዝ አጠ​ገብ በሚ​ኖሩ ሕዝብ ሁሉ ጆሮ አነ​በበ።

5 እነ​ር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አለ​ቀሱ፤ ጾሙ፤ ጸለ​ዩም።

6 እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም እንደ እየ​ች​ሎ​ታ​ቸው ገን​ዘብ ሰበ​ሰቡ፤

7 እር​ሱ​ንም ወደ ሰሉም ልጅ ወደ ኬል​ቅያ ልጅ ወደ ካህኑ ኢዮ​አ​ቄም፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከእ​ርሱ ጋር ወደ ነበ​ሩት ካህ​ና​ትና ወደ ሕዝቡ ሁሉ ላኩት።

8 ከቤተ መቅ​ደስ የተ​ወ​ሰ​ደ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ ወደ ይሁዳ ምድር ይመ​ልሱ ዘንድ በሲ​ባን ወር በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን በወ​ሰዱ ጊዜ ይህም ዕቃ የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ ሴዴ​ቅ​ያስ ያሠ​ራው የብር ዕቃ ነበር።

9 ይኸ​ውም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ኢኮ​ን​ያ​ን​ንና መኳ​ን​ን​ቱን፥ ምር​ኮ​ኞ​ቹ​ንና ኀያ​ላ​ኑን የሀ​ገ​ሩ​ንም ሕዝብ ይዞ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን ከወ​ሰ​ዳ​ቸው በኋላ ነበር።


ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ጻፈ ደብ​ዳቤ

10 እን​ዲ​ህም አሉ፥ “እነሆ ገን​ዘብ ልከ​ን​ላ​ች​ኋል፤ በእ​ር​ሱም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፤ ዕጣ​ንም ግዙ​በት፤ ኅብ​ስ​ትም አዘ​ጋጁ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊ​ያም አቅ​ርቡ።

11 ዘመ​ና​ቸው በም​ድር ላይ እንደ ሰማይ ዘመን ይሆን ዘንድ ስለ ባቢ​ሎን ንጉሥ ስለ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ሕይ​ወ​ትና ስለ ልጁ ስለ ብል​ጣ​ሶር ሕይ​ወት ጸልዩ።

12 ለእ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይ​ልን ይሰ​ጠን ዘንድ፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ን​ንም ያበ​ራ​ልን ዘንድ፥ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ጥላ ሥርና በልጁ በብ​ል​ጣ​ሶር ጥላ ሥር በሕ​ይ​ወት እን​ኖር ዘንድ፥ ለብዙ ዘመ​ንም እን​ገ​ዛ​ላ​ቸው ዘንድ፥ በፊ​ታ​ቸ​ውም ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን እና​ገኝ ዘንድ ጸልዩ።

13 አም​ላ​ካ​ች​ንን በድ​ለ​ና​ልና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መዓቱ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ ከእኛ አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ች​ምና ለእ​ኛም ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልን።

14 ወደ እና​ንተ የላ​ክ​ና​ትን ይህ​ች​ንም ደብ​ዳቤ አን​ብ​ቡ​አት፤ በበ​ዓል ቀንና በተ​ወ​ደ​ደ​ውም ዕለት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ተና​ዘዙ።


የኀ​ጢ​አት ኑዛዜ

15 “እን​ዲ​ህም በሉ፤ ጽድቅ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ለእኛ ግን ለፊ​ታ​ችን ኀፍ​ረት ነው፤ ይህች ቀን ለይ​ሁዳ ሰዎ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለሚ​ኖሩ፥

16 ለን​ጉ​ሦ​ቻ​ች​ንና ለአ​ለ​ቆ​ቻ​ችን፥ ለካ​ህ​ኖ​ቻ​ች​ንና ለነ​ቢ​ያ​ቶ​ቻ​ችን፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ኀፍ​ረት እንደ ሆነች።

17 በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በድ​ለ​ና​ልና፤

18 አል​ታ​ዘ​ዝ​ነ​ው​ምና የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል አል​ሰ​ማ​ን​ምና፤ በሰ​ጠን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ አል​ሄ​ድ​ን​ምና፤

19 አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን ከግ​ብፅ ምድር ከአ​ወ​ጣ​በት ጊዜ ጀምሮ እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ታ​ዘ​ዝ​ነ​ውም፤ ቃሉ​ንም እን​ዳ​ን​ሰማ ከእ​ርሱ ራቅን።

20 ወተ​ትና መዓር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ይሰ​ጠን ዘንድ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን ከግ​ብፅ ምድር በአ​ወ​ጣ​በት ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለባ​ሪ​ያው ለሙሴ ያዘ​ዘው ይህ ክፉ ነገ​ርና መር​ገም እንደ ዛሬው ዕለት አገ​ኘን።

21 ወደ እኛ እንደ ላካ​ቸው እንደ ነቢ​ያት ቃል የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ንም።

22 በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ እና​ደ​ርግ ዘንድ ለባ​ዕ​ዳን አማ​ል​ክት እየ​ተ​ገ​ዛን እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችን በክፉ ልባ​ችን ፈቃድ ሄድን።

Follow us:



Advertisements