Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -


This book is not inspired by God and is not part of the Christian canon or the Jewish Tanakh. It is shown only for historical and study purposes. View full explanation

መጽ​ሐፈ ዕዝራ ካልእ 9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ዕዝ​ራም ከቤተ መቅ​ደሱ አደ​ባ​ባይ ተነ​ሥቶ ወደ ናሴሩ ልጅ ወደ ዮሐ​ናን ቤት ሄደ።

2 በዚ​ያም ተቀ​ምጦ ስለ ታላ​ላ​ቆ​ችና ብዙ​ዎች ኀጢ​አ​ቶ​ቻ​ቸው እያ​ለ​ቀሰ እህ​ልን አል​በ​ላም፤ ውኃ​ንም አል​ጠ​ጣም።

3 ከዚህ በኋላ ከም​ርኮ ለተ​መ​ለሱ ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይገኙ ዘንድ፥

4 እስከ ሁለ​ትና እስከ ሦስት ቀን ድረስ ያል​ተ​ገ​ኙና ያል​ደ​ረሱ ሁሉ እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው በአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸው ቅጣት ይቀጡ ዘንድ፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ይወ​ረሱ ዘንድ፥ እነ​ር​ሱም ከወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይለዩ ዘንድ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዐዋጅ ነገ​ረ​ላ​ቸው።

5 የይ​ሁ​ዳና የብ​ን​ያም ወገ​ኖ​ችም በዘ​ጠ​ነ​ኛው ወር በሃ​ያ​ኛው ቀን በሦ​ስት ቀን ውስጥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተሰ​በ​ሰቡ።

6 ሁሉም በቤተ መቅ​ደሱ አደ​ባ​ባይ ተቀ​መጡ፤ ክረ​ምት ነበ​ርና ስለ ውርጩ ጽናት ይን​ቀ​ጠ​ቀጡ ነበር።

7 ዕዝ​ራም ተነ​ሥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከአ​ሕ​ዛብ ወገን ሚስት ያገ​ባ​ችሁ እና​ንተ በደ​ላ​ችሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ኀጢ​አ​ትን ጨመ​ራ​ችሁ።

8 አሁ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ዘዙ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ን​ንም አም​ላክ አመ​ስ​ግ​ኑት።

9 ፈቃ​ዱ​ንም ፈጽሙ፤ ከም​ድር አሕ​ዛ​ብና ከባ​ዕ​ዳት ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ተለዩ።”

10 ሁሉም በሙሉ በታ​ላቅ ድምፅ ጮኸው እን​ዲህ አሉት፥ “እሺ አንተ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኸን እና​ደ​ር​ጋ​ለን።

11 ነገር ግን ሰዉ ብዙ ነው፤ ጊዜ​ውም ክረ​ምት ነው፤ ፈጥ​ነ​ንም እና​ደ​ር​ገው ዘንድ አን​ች​ልም፤ ሥራ​ውም የአ​ንድ ቀን ወይም የሁ​ለት ቀን ሥራ አይ​ደ​ለም፤ በዚህ ፈጽ​መን በድ​ለ​ና​ልና።

12 አሁ​ንም ከልዩ ወገን ሚስት ያገቡ መሳ​ፍ​ንት ሁሉና መን​ደ​ረ​ተ​ኞ​ችም ተሰ​ብ​ስ​በው ይምጡ።

13 በዚህ ሥራ ያገ​ኘን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ከእኛ ይርቅ ዘንድ መን​ደ​ረ​ተ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይቅ​ጠ​ሯ​ቸው።”

14 የአ​ዛ​ሄል ልጅ ዮና​ታን፥ የታ​ቃኑ ልጅ ኢያ​ዝ​ያ​ስም መጡ፤ ሞሶ​ላ​ሞስ፥ ሌዊ፥ ሳባ​ጢ​ዎስ፥ እነ​ር​ሱም እን​ዲህ ተባ​በሩ።

15 ከም​ርኮ የተ​መ​ለ​ሱ​ትም ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።

16 ካህኑ ዕዝ​ራም ካገ​ሮ​ቻ​ቸው ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ በያ​ገ​ራ​ቸ​ውም ከሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ስማ​ቸው ልዩ ልዩ የሆነ ሰዎ​ችን መረጠ፤ እን​ዲ​ህም ያደ​ርጉ ዘንድ እስከ ዐሥ​ረ​ኛው ወር መባቻ ድረስ ተቃ​ጠሩ።

17 ከልዩ ወገን ሚስት ያገቡ እነ​ዚ​ያም ሰዎች ሁሉ “እስከ መጀ​መ​ሪ​ያው ወር መባቻ እን​ፈ​ታ​ለን” ብለው ነገ​ራ​ቸ​ውን ጨረሱ።

18 ከካ​ህ​ና​ቱም ውስጥ ከባ​ዕድ ወገን ሚስት ያገቡ ተገኙ።

19 እነ​ር​ሱም የኢ​ዮ​ሴ​ዴቅ ልጅ የኢ​ያሱ ልጆ​ችና ወን​ድ​ሞቹ፥ ማቴ​ላስ፥ አል​ዓ​ዛር፥ ዮሬ​ቦ​ስና ዮአ​ዳ​ኖ​ስም ናቸው።

20 ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ፈት​ተው ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው መሥ​ዋ​ዕት ይሠዉ ዘንድ ጀመሩ።

21 ከኤ​ሞ​ርም ልጆች ሐና​ንያ፥ ዘብ​ዴ​ዎስ፥ ሜኑስ፥ ሴሜ​ዎስ፥ ኢያ​ር​ማ​የ​ልና አዛ​ርያ ናቸው።

22 ከፌ​ት​ር​ኤ​ልም ልጆች ኢል​ዮ​ኒስ፥ ማስ​ያስ፥ አስ​ማ​ኤ​ሎስ፥ ናት​ና​አ​ሎስ፥ ዎቅ​ዲ​ሎ​ስና አል​ታሳ ናቸው።

23 ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ወገን ዮዛ​ባ​ዶስ፥ ሳም​ያስ፥ ቃሊ​ጣስ የሚ​ሉት ቆዮስ፥ ፋት​ያስ፥ ይሁ​ዳና ዮናስ ናቸው።

24 ከመ​ዘ​ም​ራ​ንም ወገን ኤል​ያ​ሳ​ቦ​ስና ባካ​ሮስ ናቸው።

25 ከበ​ረ​ኞ​ችም ወገን ሴሎ​ምና ጦል​ባ​ኒስ ናቸው።

26 ከእ​ስ​ራ​ኤል ከፎ​ሮስ ልጆች ወገ​ንም ኢየ​ር​ማስ፥ ኤዝ​ያስ፥ ሚል​ክ​ያስ፥ ሚያ​ኤ​ሎስ፥ አል​ዓ​ዛር፥ አስ​ብ​ያስ፥ ባኒ​ያስ ናቸው።

27 ከኤላ ልጆች ወገን ማጣ​ን​ያስ፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ኢያ​ዚ​ሬ​ሎስ፥ አብ​ድ​ዮስ፥ ኢያ​ሬ​ሞ​ትና ኤዲ​ያስ ናቸው።

28 ከዛ​ሞ​ትም ልጆች ወገን ኤሊ​ያ​ዳስ፥ ኤሊ​ያ​ሲ​ሞስ፥ ኦቶ​ን​ያስ፥ ኢያ​ሪ​ሞስ፥ ሳባ​ቶስ፥ ዘራ​ሊ​ያስ ናቸው።

29 ከቤ​ባ​ይም ልጆች ወገን ዮሐ​ንስ፥ ሐና​ንያ፥ ዮዛ​ብ​ዴ​ዎስ፥ አሜ​ቴ​ዎስ ናቸው።

30 ከማኒ ልጆ​ችም ወገን ኦላ​ሞስ፥ ማም​ኮስ፥ ኢያ​ዴ​ዎስ፥ ኢያ​ሶ​ቦስ፥ አስ​ሔ​ሎስ፥ ኢያ​ር​ሞት ናቸው።

31 ከዓዲ ልጆ​ችም ናሐ​ቶስ፥ ሞሐ​ስ​ያስ፥ ለቁ​ናስ፥ ኒዶስ፥ ቢስ​ቀስ-ጰስ​ሚስ ሲአ​ቱል ባል​ኑስ፥ ሜና​ስ​ያስ ናቸው፥

32 ከሐ​ና​ንያ ልጆ​ችም ኢሊ​ዮ​ሳስ፥ አስ​ያስ፥ ሚል​ክ​ያስ፥ ስብ​ያስ፥ ስም​ዖን፥ ኮሳ​ሜ​ዎስ ናቸው።

33 ከአ​ሶም ልጆ​ችም መል​ጠ​ኒ​ዎስ፥ መጣ​ቲ​ያስ፥ ሳባ​ኔ​ዎስ፥ ኤሌ​ፍ​ላት፥ ምናሴ፥ ሴሜይ ናቸው።

34 ከባኒ ልጆ​ችም ኤር​ም​ያስ፥ ሞም​ዲስ፥ ስማ​ኤል፥ ኢዮ​ኤል፥ መምዲ፥ ጴዴ​ያስ፥ አናስ፥ ቀሪ​ባ​ሶን፥ አና​ሲ​ቦስ፥ መን​ጠ​ኒ​ሞስ፥ አል​ያ​ሲስ፥ በኑስ፥ ኤል​ያሊ፥ ሰማ​ይስ፥ ሰላ​ም​ያስ፥ ናታ​ን​ያስ ናቸው። ከኤ​ዛ​ር​ያስ ልጆ​ችም ሴሲስ፥ ኤዝ​ርል፥ አዛ​ኤል፥ ሳማ​ጢስ፥ ዘም​በሪ፥ ኢዮ​ሶ​ፎስ ናቸው።

35 ከነ​ሐማ ልጆ​ችም ማዚ​ጢ​ያስ፥ ዘቢ​ዲ​ያስ፥ ኤዴስ፥ ኢዮ​ኤል፥ በኒ​ያስ ናቸው።

36 ከባ​ዕ​ዳን ከአ​ሕ​ዛብ ወገን ሚስት ያገ​ቡት ሰዎች ሁሉ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ውን ሁሉ ከል​ጆ​ቻ​ቸው ጋር አስ​ወ​ጧ​ቸው።

37 ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያ​ንም፥ ብዙ​ዎች እስ​ራ​ኤ​ልም በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር መባቻ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በያ​ገ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በየ​አ​ው​ራ​ጃ​ቸው ተመ​ለሱ።

38 በቤተ መቅ​ደሱ በር በም​ሥ​ራ​ቃ​ዊው አደ​ባ​ባይ ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​በ​ሰቡ።

39 ካህ​ኑ​ንና ጸሓ​ፊ​ዉን ዕዝ​ራ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠ​ውን የሙ​ሴን ሕግ ያመጣ ዘንድ ነገ​ሩት።

40 የካ​ህ​ናት አለቃ ዕዝ​ራም በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር መባቻ ለሕ​ዝቡ፥ ለወ​ን​ዶ​ችም፥ ለሴ​ቶ​ችም ለካ​ህ​ና​ቱም ሁሉ ሕጉን ይሰሙ ዘንድ አነ​በ​በ​ላ​ቸው።

41 በቤተ መቅ​ደ​ሱም በር ባለው አደ​ባ​ባይ በወ​ን​ዶ​ቹና በሴ​ቶቹ ፊት ከነ​ግህ ጀምሮ እስከ ቀትር ድረስ አነ​በ​በ​ላ​ቸው፤ ሁሉም በፍ​ጹም ልባ​ቸው ሕጉን አደ​መጡ።

42 ካህ​ኑና የሕጉ ጸሓፊ ዕዝ​ራም ከእ​ን​ጨት በተ​ሠራ መረ​ባ​ርብ ላይ ቆመ።

43 ከእ​ር​ሱም ጋር፦ መተ​ጢ​ያ​ስን፥ ሳሙ​ስን፥ ሐና​ን​ያን፥ አዛ​ር​ያን፥ ኡር​ያ​ስን፥ ሕዝ​ቅ​ያ​ስን፥ በአ​ል​ስ​ሞ​ስ​ንም በቀኙ አቆ​ማ​ቸው።

44 በግ​ራ​ውም በኩል ፈሐ​ል​ዴ​ዎ​ስን፥ ሚሳ​ኤ​ልን፥ ሚል​ክ​ያ​ስን፥ ሎታ​ሳ​ብ​ስን፥ ናባ​ሪ​ያ​ንና ዘካ​ር​ያ​ስን አቆመ።

45 ዕዝ​ራም ያን መጽ​ሐፍ ይዞ በሕ​ዝቡ ፊት ተቀ​መጠ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ያከ​ብ​ሩት ነበር።

46 የሕ​ጉ​ንም መጽ​ሐፍ በገ​ለጠ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ተነ​ሥ​ተው ቆሙ፤ አዛ​ር​ያም ሁሉን የሚ​ገዛ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ነው።

47 ሁሉም በሙሉ፥ “አሜን፥ አሜን” ብለው መለ​ሱ​ለት፤ እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወደ ላይ አን​ሥ​ተው በም​ድር ወድ​ቀው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገዱ።

48 ሌዋ​ው​ያ​ኑም ኢያሱ፥ አኑሲ፥ ሰራ​ቢ​ያስ፥ ኢያ​ዲ​ኖስ፥ ኢያ​ቆ​ብስ፥ ሳብ​ጣ​ያስ፥ አው​ጥ​ያስ፥ ሚሐና፥ ቀሊ​ጦስ፥ አዛ​ርያ፥ ጠዛ​ብ​ዶስ፥ ሐኒ​ያስ፥ ፈል​ጣስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ አስ​ተ​ማ​ሯ​ቸው።

49 ባነ​በ​በ​ላ​ቸ​ውም ጊዜ ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት ሆነው ሰሙ።

50 አጠ​ራ​ጢም የካ​ህ​ና​ቱን አለ​ቃና ጸሓ​ፊ​ውን ዕዝ​ራን፥ ለሁሉ የሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፦

51 “ይቺ ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ሰች ናት፥” ሁሉም ሕጉን በሰሙ ጊዜ አለ​ቀሱ።

52 እን​ዲ​ህም ተባ​ባሉ፥ “ሂዱና ምሳ​ች​ሁን ብሉ፤ ጠጡም፤ ለሌ​ላ​ቸ​ውም ሰዎች ምጽ​ዋ​ትን ላኩ። ይቺ ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ሰች ናትና፥ አት​ዘ​ኑም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ጥ​ላ​ች​ሁ​ምና።”

53 ሌዋ​ው​ያ​ንም ሕዝ​ቡን ሁሉ እን​ዲህ ብለው አዘዙ “ይቺ ቀን የተ​ቀ​ደ​ሰች ናትና አት​ዘኑ።”

54 ሁሉም ሊበ​ሉና ሊጠጡ፥ ደስ​ታም ሊያ​ደ​ርጉ፥ ለሌ​ላ​ቸ​ውም ሰዎች ምጽ​ዋ​ትን ሊሰጡ ሄዱ።

55 በተ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት ቦታም ያስ​ተ​ማ​ሯ​ቸ​ውን ቃል በሰሙ ጊዜ ታላቅ ደስ​ታን አደ​ረጉ።

Follow us:



Advertisements