Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -


This book is not inspired by God and is not part of the Christian canon or the Jewish Tanakh. It is shown only for historical and study purposes. View full explanation

መጽ​ሐፈ ዕዝራ ካልእ 8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ዕዝራ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ መጣ

1 ከዚ​ህም በኋላ በፋ​ርስ ንጉሥ በአ​ር​ጤ​ክ​ስስ መን​ግ​ሥት ዕዝራ መጣ፤ እር​ሱም የሠ​ራያ ልጅ፥ የአ​ዛ​ር​ያስ ልጅ፥ የኬ​ል​ቅዩ ልጅ፥ የሴ​ሎም ልጅ፤

2 የሳ​ዶቅ ልጅ፥ የአ​ኪ​ጦብ ልጅ፥ የአ​ማ​ር​ትዩ ልጅ፥ የአ​ዝ​ያን ልጅ፥ የቡቂ ልጅ፥ የአ​ቢሱ ልጅ፥ የፊ​ን​ሐስ ልጅ፥ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ፥ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ካህን የአ​ሮን ልጅ፤

3 ይህም ዕዝራ ከባ​ቢ​ሎን መጣ፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሰ​ጠ​ውን የሙ​ሴን ኦሪት ሁሉ ያውቅ ነበረ፤ እር​ሱም ጸሓፊ ነበር።

4 ንጉ​ሡም ክብ​ርን ሰጠው፤ በፊቱ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን አግ​ኝ​ት​ዋ​ልና፥ በሁ​ሉም ላይ ሹሞ​ታ​ልና።

5 ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ ከካ​ህ​ና​ቱና ከሌ​ዋ​ው​ያኑ፥ ከመ​ዘ​ም​ራ​ኑና ከበ​ረ​ኞች፥ ከቤተ መቅ​ደስ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም፥ ዐያ​ሌ​ዎቹ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጡ።

6 በአ​ር​ጤ​ክ​ስስ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥቱ፥ በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር፥ በወሩ መባቻ ከባ​ቢ​ሎን ወጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን እን​ዳ​ቀ​ና​ላ​ቸው በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር መባቻ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ።

7 ዕዝ​ራም ብዙ ትም​ህ​ርት የሚ​ያ​ውቅ ነበረ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሥር​ዐ​ት​ንና ፍር​ድን ያስ​ተ​ምር ዘንድ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግና ትእ​ዛዝ የሚ​ጐ​ድ​ለው አል​ነ​በ​ረም።


ንጉሥ አር​ጤ​ክ​ስስ ለዕ​ዝራ የሚ​ፈ​ል​ገው ሁሉ እን​ዲ​ደ​ረ​ግ​ለት የሰ​ጠው ትእ​ዛዝ

8 ንጉሡ አር​ጤ​ክ​ስ​ስም ወደ ካህ​ኑና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ወደ​ሚ​ጽ​ፈው ወደ ዕዝራ ደብ​ዳቤ ላከ። ከአ​ር​ጤ​ክ​ስ​ስም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ወደ​ሚ​ጽ​ፈው ወደ ካህኑ ዕዝራ የተ​ላ​ከው ደብ​ዳቤ እን​ዲህ ይላል፦

9 “ከን​ጉሠ ነገ​ሥት ከአ​ር​ጤ​ክ​ስስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ጸሓፊ፥ ለካ​ህኑ ለዕ​ዝራ ሰላም ለአ​ንተ ይሁን፤

10 እኔ ሰውን በመ​ው​ደድ አስቤ ከአ​ይ​ሁድ ወገን በመ​ን​ግ​ሥቴ ካሉ ከካ​ህ​ና​ትና ከሌ​ዋ​ው​ያን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይሄዱ ዘንድ የሚ​ወ​ዱ​ትን ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ይሂዱ ብዬ አዝ​ዣ​ለሁ።

11 ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ይሄዱ ዘንድ የሚ​ወዱ ሁሉ ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን አይ​ተው ከእ​ና​ንተ ጋር ይተ​ባ​በሩ።

12 እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ሄደው ያደ​ርጉ ዘንድ እኔና ሰባቱ ባለ​ሟ​ሎች፥ አማ​ካ​ሪ​ዎ​ችም እን​ዲህ አዝ​ዘ​ናል።

13 እኔና ባለ​ሟ​ሎች የተ​ሳ​ል​ነ​ውን ቍር​ባን፥ በባ​ቢ​ሎን ሀገር የተ​ገ​ኘ​ው​ንም ወር​ቁ​ንና ብሩን ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ርቡ ዘንድ፥

14 ሕዝቡ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደስ ከሚ​ያ​ገ​ቡት ስእ​ለት ጋራ ወር​ቁ​ንና ብሩን፥ ለበ​ሬ​ዎች፥ ለፍ​የ​ሎ​ችና ለበ​ጎች መግዣ ይሰ​ብ​ስቡ፥

15 እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ መሥ​ዋ​ዕት ይሠዉ ዘንድ፥

16 ለሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ጋ​ቸው ሁሉ፥ ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ጋር ታደ​ር​ገው ዘንድ የም​ት​ወ​ደ​ውን ሁሉ በዚህ ወር​ቅና ብር እንደ አም​ላ​ክህ ፈቃድ አድ​ርግ።

17 በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላለ ለአ​ም​ላ​ክህ ቤተ መቅ​ደስ ግዳጅ የሚ​ሆ​ነ​ውን ንዋ​ያተ ቅድ​ሳት።

18 ለአ​ም​ላ​ክህ ቤተ መቅ​ደስ ግዳጅ የም​ት​ሻው ሌላም ቢኖር ከን​ጉሡ ዕቃ ቤት እሰ​ጣ​ለሁ።

19 “እኔ ንጉሥ አር​ጤ​ክ​ስስ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ የሚ​ጽፍ ካህኑ ዕዝራ የሚ​ጠ​ይ​ቀ​ውን ሁሉ በሶ​ር​ያና በፊ​ን​ቂስ ካለው ዕቃ ቤት እን​ዲ​ሰ​ጡት አዘ​ዝሁ። ስጡ፤ እን​ቢም አት​በሉ።

20 እስከ መቶ መክ​ሊት ብር፥ ዳግ​መ​ኛም እስከ መቶ የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ስንዴ፥ እስከ መቶም የኔ​ባል መስ​ፈ​ሪያ ወይን፥ ብዙ ጨውም ቢሆን ስጡ።

21 በን​ጉሥ መን​ግ​ሥ​ትና በል​ጆቹ ላይ መከራ እን​ዳ​ይ​መጣ በል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ይሥሩ።

22 ከካ​ህ​ና​ቱና ከሌ​ዋ​ው​ያኑ፥ ከመ​ዘ​ም​ራ​ኑና ከበ​ረ​ኞቹ ግብር አት​ቀ​በሉ። ከቤተ መቅ​ደ​ስም አገ​ል​ጋ​ዮች፥ ተቀ​ጥ​ረው ቤተ መቅ​ደ​ስን ከሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ሁሉ ምንም አት​ቀ​በሉ፥ አት​ግ​ዟ​ቸ​ውም።

23 “አን​ተም ዕዝራ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በገ​ለ​ጠ​ልህ ጥበብ የአ​ም​ላ​ክን ሕግ ከሚ​ያ​ውቁ ወገ​ኖች ውስጥ ሶር​ያ​ንና ፊን​ቂ​ስን የሚ​ገዙ መኳ​ን​ን​ቱ​ንና መሳ​ፍ​ን​ቱን ሹም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ የማ​ያ​ው​ቁ​ት​ንም አስ​ተ​ም​ራ​ቸው።

24 የአ​ም​ላ​ክ​ህን ሕግና የን​ጉ​ሡን ትእ​ዛዝ የሚ​ተ​ላ​ለ​ፈ​ው​ንም ሁሉ ቸል አት​በሉ፤ ቅጡ፤ በሞ​ትም ቢሆን፥ በግ​ር​ፋ​ትም ቢሆን፥ በባ​ር​ነ​ትም ቢሆን፥ በመ​ው​ረ​ስም ቢሆን፥ ሁሉ​ንም በየ​ኀ​ጢ​አቱ ቅጡት።”


ዕዝራ አም​ላ​ኩን እን​ዳ​መ​ሰ​ገነ

25 ዕዝ​ራም እን​ዲህ አለ፥ “በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ያከ​ብር ዘንድ ይህን ነገር በን​ጉሥ ልብ ያሳ​ደረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።

26 በነ​ገ​ሥ​ታ​ቱና በአ​ማ​ካ​ሪ​ዎቹ፥ በወ​ዳ​ጆ​ቹና በመ​ኳ​ን​ንቱ ሁሉ ፊት እኔን አክ​ብ​ሮ​ኛ​ልና።

27 ከዚ​ህም በኋላ በፈ​ጣ​ሪዬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ታመ​ንሁ። ከእ​ኔም ጋር ይወጡ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎ​ችን ወሰ​ድሁ።”


ከም​ርኮ የተ​መ​ለሱ

28 በን​ጉሡ በአ​ር​ጤ​ክ​ስስ መን​ግ​ሥት በየ​ሀ​ገ​ራ​ቸ​ውና በየ​አ​ው​ራ​ጃ​ቸው ግዛት ከእኔ ጋር ከባ​ቢ​ሎን የወጡ አለ​ቆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው።

29 ከፎ​ሮስ ልጆች ጣስ​ጣ​ሞስ፥ ከኢ​ዮ​ጥ​ማ​ሩም ልጆች ጋሜ​ሎስ፥ ከዳ​ዊ​ትም ልጆች የሴ​ኬ​ን​ያስ ልጅ አጡስ፥

30 ከፋ​ሬ​ስም ልጆች ዘካ​ር​ያስ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር መቶ አምሳ ሰዎች ተቈ​ጠሩ።

31 ከፎ​አት ሞዓ​ብም ልጆች የዛ​ርያ ልጅ ኤሊ​ዎ​ንያ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት መቶ ሰዎች።

32 ከዘ​ቶ​ይ​ስም ልጆች የኢ​ያ​ሐ​ቲሉ ልጅ ኢያ​ኬ​ን​ያስ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት መቶ ሰዎች፥ ከአ​ዲኑ ልጆች የዮ​ና​ታን ልጅ ኦቤድ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት መቶ አምሳ ሰዎች።

33 ከኤ​ላም ልጆች የጎ​ቶ​ልያ ልጅ ኢሴይ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሰባ ሰዎች።

34 ከሳ​ፋጢ ልጆች የሚ​ካ​ኤል ልጅ ዛር​ያስ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሰባ ሰዎች።

35 ከኢ​ዮ​አ​ብም ልጆች የኢ​ዝ​ኤል ልጅ ኦባ​ድያ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ሰዎች።

36 ከባኒ ልጆ​ችም የኢ​ዮ​ሳ​ፌይ ልጅ አስ​ሊ​ሞት፥ ከእ​ር​ሱም ጋር መቶ ስድሳ ሰዎች።

37 ከቤ​ዔር ልጆ​ችም የባቢ ልጅ ዘካ​ር​ያስ፥ ከር​ሱም ጋር ሃያ ስም​ንት ሰዎች።

38 ከአ​ሰ​ጣ​ያ​ትም ልጆች የአ​ዝ​ጋድ ልጅ ዮሐ​ንስ፥ ከር​ሱም ጋር መቶ ዐሥር ሰዎች።

39 ከአ​ዶ​ኒ​ቃም ልጆች የቀ​ሩት ሁሉ ስማ​ቸው ይህ ነው፦ ኤሊ​ፋሊ፥ ይዑ​ኤል፥ ሰሚ​ያስ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋራ ሰባ ሰዎች።

40 ከቤ​ኑ​ስም ልጆች የአ​ስ​ጣ​ስ​ቆሩ ልጅ ዑታይ ከእ​ር​ሱም ጋራ ሰባ ሰዎች ተቈ​ጠሩ።


ዕዝራ የቤተ መቅ​ደስ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያ​ንን እን​ዳ​ገኘ

41 ቴራን ወደ​ሚ​ባል ወን​ዝም ሰበ​ሰ​ብ​ኋ​ቸው፤ በዚ​ያም ሦስት ቀን አደ​ርን፤ አስ​ቈ​ጠ​ር​ኋ​ቸ​ውም።

42 ከው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ካህ​ና​ት​ንና ሌዋ​ው​ያ​ንን አላ​ገ​ኘ​ንም።

43 ወደ አል​ዓ​ዛ​ርም ላክሁ፤ ከእ​ኔም ጋር መአ​ስ​መ​ንን፥ አን​ዐ​ጣ​ንን፥ ሰም​ያ​ስን፥ ኢዮ​ሪ​ቦን፥ ናታ​ንን፥ አር​ጦ​ንን፥ ዘካ​ር​ያ​ስን፥ ሞሱ​ላ​ሞ​ስን ወሰ​ድሁ።

44 ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ከመ​ሳ​ፍ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ከዐ​ዋ​ቂ​ዎ​ቻ​ቸው ወሰ​ድሁ።

45 ወደ ዕቃ ቤቱም ሹም ወደ ያድ​ዮን ይሄዱ ዘንድ ነገ​ር​ኋ​ቸው።

46 ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ካህ​ና​ትን እን​ዲ​ል​ኩ​ልን ለያ​ድ​ዮ​ንና ለወ​ን​ድ​ሞቹ፥ በዚ​ያም ቦታ ለአሉ ሰዎች ይነ​ግ​ሯ​ቸው ዘንድ አዘ​ዝ​ኋ​ቸው።

47 ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጅ ከሌዊ ልጅ ከሞ​ሐሊ ልጆች ጠቢ​ባን ሰዎ​ችን አሲ​ብ​ያ​ንና ልጆ​ቹን፥ ዐሥራ ስም​ንት ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም አመ​ጡ​ልን፥

48 ከከ​ዓኑ ልጆ​ችና ከል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም ውስጥ የሆኑ ሃያ ሰዎች፥

49 ዳዊት የሠ​ራ​ቸው የቤተ መቅ​ደስ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችና አለ​ቆ​ቻ​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ሥራ የተ​ጨ​መሩ የካ​ህ​ናት ልጆች ሁለት መቶ ሃያ ናቸው፤ የሁ​ሉም ስማ​ቸው ተጻፈ።


ዕዝራ ጾምን እን​ዳ​ወጀ

50 በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ከል​ጆ​ቻ​ችን ጋራ በዚያ እን​ጾም ዘንድ ለል​ጆ​ቻ​ች​ንና ለከ​ብ​ቶ​ቻ​ች​ንም ይቅ​ር​ታን እን​ለ​ምን ዘንድ ተሳ​ልን።

51 ሀገ​ራ​ች​ንን የሚ​ያ​ጸ​ኑና ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን ጋራ የሚ​መ​ካ​ከቱ እግ​ረ​ኞ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን እን​ዲ​ሰ​ጠን ለን​ጉሡ እልክ ዘንድ አፍ​ሬ​አ​ለ​ሁና።

52 ሥራ​ውን ሁሉ ያቀ​ና​ላ​ቸው ዘንድ ከሚ​ፈ​ል​ጉት ሰዎች ጋራ የጌ​ታ​ችን ከሃ​ሊ​ነት እን​ደ​ሚ​ኖር ለን​ጉሡ ነግ​ረ​ነው ነበ​ርና።

53 ዳግ​መ​ኛም ስለ​ዚህ ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመን፤ እር​ሱም ይቅር አለን።


ለቤተ መቅ​ደስ ሥራ የቀ​ረበ መባእ

54 ከሕ​ዝ​ቡና ከካ​ህ​ናቱ ሹሞች ዐሥራ ሁለ​ቱን ሰዎች፥ ኤሴ​ር​ያ​ንና አሴ​ሚ​ያን፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል ዐሥር ሰዎ​ችን ለየሁ።

55 ንጉ​ሡና መኳ​ን​ንቱ፥ አማ​ካ​ሪ​ዎ​ቹም እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ የሰ​ጡ​ንን ወር​ቁ​ንና ብሩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ንዋየ ቅድ​ሳት መዝኜ ሰጠ​ኋ​ቸው።

56 ስድ​ስት መቶ አምሳ መክ​ሊት ብርም መዝኜ ሰጠ​ኋ​ቸው።

57 መቶ መክ​ሊት የብር ዕቃ፥ መቶ መክ​ሊ​ትም ወርቅ፥ ሃያ መክ​ሊ​ትም የወ​ርቅ ዕቃ፥ የሚ​ወ​ደድ እንደ ወር​ቅም የጠ​ራና የጠ​ነ​ከረ ዐሥራ ሁለት የናስ ዕቃ መዝኜ ሰጠ​ኋ​ቸው።

58 እን​ዲ​ህም አል​ኋ​ቸው፥ “እና​ን​ተም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተለዩ፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ፈጣሪ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት የሆ​ነ​ውን የብ​ሩ​ንና የወ​ር​ቁን ንዋየ ቅድ​ሳ​ትም ለዩ።

59 ለመ​ሳ​ፍ​ን​ቱና ለመ​ኳ​ን​ንቱ፥ ለካ​ህ​ናቱ አለ​ቆ​ችና ለሌ​ዋ​ው​ያኑ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገ​ሮች አለ​ቆች በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት አዳ​ራሽ ውስጥ እስ​ክ​ት​ሰ​ጧ​ቸው ድረስ ተግ​ታ​ችሁ ጠብቁ።”

60 ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም የተ​ቀ​በ​ሉ​ትን ወር​ቁ​ንና ብሩን፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ንዋየ ቅድ​ሳት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደስ አገቡ።


ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​መ​ለ​ሱት ሕዝብ

61 በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ቀን ቴራን ከሚ​ባል ሀገር ተነሡ፤ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን ሁሉ ባዳ​ነን፥ በፈ​ጣ​ሪ​ያ​ችን ከእኛ ጋር ባለች ጽን​ዕት እጅም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ።

62 በደ​ረሱ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ወር​ቁ​ንና ብሩን መዝ​ነ​ውና ቈጥ​ረው በቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለኦ​ርያ ልጅ ለካ​ህኑ ለመ​ር​ሞ​ቲ​ዮራ ሰጡት።

63 የሁ​ሉም ልኩ፥ ሚዛ​ኑም ያን​ጊዜ ተጻፈ።

64 ከእ​ር​ሱም ጋር የፊ​ን​ሐስ ልጅ አል​ዓ​ዛር ነበረ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሌዋ​ው​ያኑ የኢ​ያሱ ልጅ የዘ​ባ​ትና የብኑ ልጅ ሞኢ​ተስ ነበሩ።

65 ከም​ርኮ የተ​መ​ለ​ሱ​ትም ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ። ዐሥራ ሁለት ኮር​ማ​ዎ​ችን፥ ዘጠና ስድ​ስት በጎ​ችን፥

66 ስለ ድኅ​ነ​ትም ሰባ ስድ​ስት ሙክ​ቶ​ችን፥ ዐሥራ ሁለት የበግ ጠቦ​ቶ​ችን፥ ሁሉ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዉ።

67 ከዚ​ህም በኋላ ለን​ጉሡ ዕቃ ቤት ሹሞች፥ ለሶ​ር​ያና ለፊ​ንቂ ገዦ​ችም ከን​ጉሡ የመ​ጣ​ውን ደብ​ዳቤ ሰጧ​ቸው፤ ሕዝ​ቡ​ንና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መቅ​ደስ አከ​በሩ።


ዕዝራ ከአ​ሕ​ዛብ ጋር የተ​ደ​ረ​ገ​ውን ጋብቻ እንደ ተቃ​ወመ

68 ከዚ​ህም በኋላ ሹሞች መጥ​ተው የሠ​ሩ​ትን ነገ​ሩኝ።

69 እን​ዲ​ህም አሉኝ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች፥ መኳ​ን​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ ካህ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ከሌ​ሎች የም​ድር አሕ​ዛብ ከከ​ና​ኔ​ዎን፥ ከፌ​ሬ​ዜ​ዎን፥ ከኬ​ጤ​ዎ​ንም፥ ከኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎን፥ ከሞ​ዓ​ባ​ው​ያን፥ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንና ከኤ​ዶ​ሜ​ዎን ርኵ​ሰት አል​ተ​ለ​ዩም።

70 ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን አገቡ፤ እነ​ር​ሱና ልጆ​ቻ​ቸ​ውም የከ​በ​ረ​ውን ዘር ከባ​ዕ​ዳን የም​ድር አሕ​ዛብ ጋር ቀላ​ቀሉ፤ መሳ​ፍ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ውና መኳ​ን​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ሥራ​ቸው ጀምሮ በዚ​ያች ኀጢ​አት አንድ ሆኑ።”

71 ከዚ​ህም በኋላ ይህን በሰ​ማሁ ጊዜ ልብ​ሴ​ንና ልብሰ ተክ​ህ​ኖ​ዬን ቀደ​ድሁ፤ የራ​ሴን ጠጕ​ርና ጢሜ​ንም ነጨሁ፤ ተክ​ዤና አዝ​ኜም ተቀ​መ​ጥሁ።

72 እኔም በዚ​ያች ኀጢ​አት አዝ​ኜና ተክዤ ተቀ​ምጬ ሳለሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ፈጣሪ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ የሚ​ፈሩ ሁሉ ወደ እኔ ተሰ​በ​ሰቡ።

73 ከዚ​ህም በኋላ በሠ​ርኩ መሥ​ዋ​ዕት ጊዜ ጾመኛ እንደ ሆንሁ ልብ​ሴና የክ​ህ​ነት ልብሴ እንደ ተቀ​ደደ ሆኖ ተነ​ሣሁ፤ በጉ​ል​በ​ቴም ተን​በ​ረ​ከ​ክሁ፤ እጆ​ች​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘረ​ጋሁ።

74 እን​ዲ​ህም አልሁ፥ “አቤቱ ጌታዬ ከፊ​ትህ የተ​ነሣ አፍ​ራ​ለሁ፤ እፈ​ራ​ለ​ሁም።

75 ኀጢ​አ​ታ​ችን በዝ​ት​ዋ​ልና፥ ከራ​ሳ​ች​ንም ከፍ ከፍ ብሏ​ልና፥ አለ​ማ​ወ​ቃ​ች​ንም እስከ ሰማይ ደር​ሷ​ልና።

76 ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በታ​ላቅ ኀጢ​አት ላይ ኖረ​ናል።

77 በእኛ ኀጢ​አ​ትና በአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ኀጢ​አት የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንና ከን​ጉ​ሦ​ቻ​ችን፥ ከካ​ህ​ኖ​ቻ​ች​ንም ጋር ማረ​ኩን፤ በጦ​ራ​ቸ​ውም ዘረ​ፉን፤ እስከ ዛሬም ድረስ አፈ​ርን።

78 አሁን ግን በዚ​ያች በተ​ቀ​ደ​ሰ​ችው ቦታህ ሥር​ንና ስምን ትተ​ው​ልን ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ ቸር​ነ​ትህ በእኛ ላይ በዝታ ተደ​ረ​ገ​ች​ልን።

79 በአ​ን​ተም በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት ብር​ሃን ተገ​ለ​ጠ​ልን፤ ተገ​ዥ​ዎ​ችም በሆ​ንን ጊዜ ምግ​ባ​ች​ንን ሰጠ​ኸን።

80 በተ​ገ​ዛ​ንም ጊዜ አንተ አም​ላ​ካ​ችን አል​ተ​ው​ኸ​ንም፤ በፋ​ርስ ነገ​ሥ​ታ​ትም ፊት ሞገ​ስን ሰጠ​ኸን፤ ምግ​ባ​ች​ንን ይሰ​ጡን ዘንድ፥

81 ቤተ መቅ​ደ​ሳ​ች​ን​ንም ያከ​ብሩ ዘንድ፥ የጽ​ዮ​ን​ንም ፍራ​ሿን ይሠሩ ዘንድ፥ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ኀይ​ልን ይሰ​ጡን ዘንድ አል​ተ​ው​ኸ​ንም።

82 “አቤቱ፥ አሁ​ንስ ይህ በእኛ ላይ ሳለ ምን እን​ላ​ለን? በባ​ሮ​ችህ በነ​ቢ​ያ​ትም እጅ እን​ዲህ ስትል የሰ​ጠ​ኸ​ውን ትእ​ዛ​ዝ​ህን ካድን።

83 ትወ​ር​ሷት ዘንድ ወደ እርሷ ትገ​ባ​ላ​ችሁ ያል​ሃ​ቸው ያች ምድር በም​ድር አሕ​ዛብ ርኵ​ሰት የተ​ዳ​ደ​ፈች ምድር ናት፤ ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ው​ንም መሏት።

84 ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው አታ​ጋቡ፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ችሁ አታ​ጋቡ፤

85 ድል ትነ​ሷ​ቸው ዘንድ፥ የም​ድ​ር​ንም በረ​ከት ትበሉ ዘንድ፥ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ታወ​ር​ሷት ዘንድ በዘ​መ​ና​ችሁ ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ ጋር አት​ስ​ማሙ።

86 ይህ​ችም ያገ​ኘ​ችን ሁሉ ስለ ሥራ​ችን ክፋ​ትና ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ብዛት ነው።

87 አቤቱ አንተ ግን ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን ታገ​ሥህ፤ እን​መ​ለ​ስም ዘንድ ሥርን ሰጠ​ኸን፤ ዳግ​መ​ኛም ሕግ​ህን አፍ​ር​ሰን ከም​ድር አሕ​ዛብ ርኩ​ሰት ጋር አንድ እን​ሆን ዘንድ ይገ​ባ​ና​ልን?

88 ብት​ቈ​ጣ​ንስ ሥር​ንና ዘርን፥ ስማ​ች​ን​ንም እስ​ከ​ማ​ታ​ስ​ቀር ድረስ ባጠ​ፋ​ኸን ነበር።

89 አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አንተ፥ እው​ነ​ተኛ ነህ፥ ዛሬ ሥርን ትተ​ህ​ል​ና​ልና።

90 አሁ​ንም በፊ​ትህ በኀ​ጢ​አ​ታ​ችን አለን። ስለ​ዚህ በፊ​ትህ እን​ቆም ዘንድ አይ​ገ​ባ​ንም።”

91 ዕዝ​ራም በቤተ መቅ​ደሱ አን​ጻር ተን​በ​ር​ክኮ እያ​ለ​ቀሰ በጸ​ለ​የና በተ​ና​ዘዘ ጊዜ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያሉ ብዙ ሰዎች ሴቶ​ችና ወን​ዶች፥ ቆነ​ጃ​ጅ​ቱም ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ በሁ​ሉም ላይ ታላቅ ልቅሶ ሆነ።

92 ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ውስጥ የኢ​ያ​ኤል ልጅ ኢኮ​ን​ያስ ዕዝ​ራን ጠርቶ እን​ዲህ አለው፥ “ልዩ ከሚ​ሆኑ ከም​ድር አሕ​ዛብ ወገን ሚስት ያገ​ባን እኛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በድ​ለ​ናል፤ አሁ​ንም ይህ ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አለ።

93 ነገር ግን እንደ ፍር​ድህ ልዩ ከሚ​ሆኑ ከም​ድር አሕ​ዛብ ወገን ያገ​ባ​ና​ቸ​ውን ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ንን ሁሉ ከል​ጆ​ቻ​ቸው ጋራ ከእኛ እና​ስ​ወ​ጣ​ቸው ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እን​ማ​ማል።

94 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ የሚ​ወዱ ሰዎ​ች​ንም ሁሉ ተነ​ሥ​ተህ አም​ላ​ቸው።

95 ይህ ሥራ ባንተ ላይ ነውና፥ እኛም ካንተ ጋር ነንና፥ እን​ረ​ዳ​ሃ​ለ​ን​ምና።”

96 ዕዝ​ራም ተነ​ሥቶ የሕ​ዝ​ቡን ሹሞ​ችና ካህ​ና​ቱን፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሁሉ እን​ዲሁ ያደ​ርጉ ዘንድ አማ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ማሉ።

Follow us:



Advertisements