Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -


This book is not inspired by God and is not part of the Christian canon or the Jewish Tanakh. It is shown only for historical and study purposes. View full explanation

መጽ​ሐፈ ዕዝራ ሱቱ​ኤል 13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ሰባ​ተ​ኛው ራእይ

1 በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን በዛፍ ሥር ተቀ​ምጬ ሳለሁ፦

2 ከዚ​ያች ዛፍ ፊት ለፊት ቃል መጣ፤ “ዕዝራ! ዕዝራ!” ብሎ ጠራኝ፤ እኔም፥ “እነ​ሆኝ ጌታ ሆይ፥” አልሁ፤ ተነ​ሥ​ቼም ቆምሁ፤

3 እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “ለሙሴ ፈጽሜ ታየ​ሁት፤ ወገ​ኖ​ችም ለግ​ብፅ በተ​ገዙ ጊዜ ጳጦስ በሚ​ባል እን​ጨት ሥር ተና​ገ​ር​ሁት።

4 ላክ​ሁ​ትም፤ ወገ​ኖ​ች​ንም ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኋ​ቸው፤ ሙሴ​ንም ወደ ደብረ ሲና ወሰ​ድ​ሁት፤ ብዙ ቀንም በእኔ ዘንድ አኖ​ር​ሁት።

5 ብዙ ድን​ቅን ነገ​ር​ሁት፤ የዘ​መ​ና​ት​ንም ምሥ​ጢር አሳ​የ​ሁት፤ ኋለ​ኛ​ው​ንም ዘመን ነገ​ር​ሁት።

6 ይህን ነገር ተና​ገር፤ ይህ​ንም ነገር ሰውር ብዬ አዘ​ዝ​ሁት።

7 አሁ​ንም ለአ​ንተ እል​ሃ​ለሁ፦

8 የነ​ገ​ር​ሁ​ህን ያን ነገር ታውቅ ዘንድ፥ ያየ​ኸው ሕል​ም​ህ​ንም፥ የሰ​ማ​ኸ​ውን ትር​ጓ​ሜ​ው​ንም በል​ቡ​ናህ ጠብ​ቀው።

9 ከሰው ለይ​ተው ይወ​ስ​ዱ​ሃ​ልና፥ ከዚ​ህም በኋላ ዓለም እስ​ኪ​ያ​ልፍ ድረስ እን​ዳ​ንተ ያሉት ባሉ​በት ቦታ ከል​ጆች ጋር ትኖ​ራ​ለህ።

10 የዓ​ለም የጐ​ል​ማ​ሳ​ነቱ ወራት አል​ፏ​ልና፥ ዘመ​ኑም አር​ጅ​ት​ዋ​ልና።

11 ዓለም ለዐ​ሥር ክፍል ተከ​ፍ​ሏ​ልና እስከ ዐሥ​ርም ድረስ ደር​ሷ​ልና።

12 የዐ​ሥ​ረ​ኛው እኩ​ሌታ ቀር​ት​ዋ​ልና።

13 አሁን ግን ቤት​ህን አዘ​ጋጅ፤ አዘ​ን​ተ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ደስ አሰ​ኛ​ቸው፤ ዐዋ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ልብ አስ​ደ​ር​ጋ​ቸው፤ እን​ግ​ዲህ የም​ታ​ልፍ ሕይ​ወ​ት​ንም ተዋት።

14 መዋቲ አሳ​ብን እን​ግ​ዲህ ተወው፤ የሰው ሸክ​ም​ንም ከላ​ይህ ጣል፤ የሚ​ሞት አሳ​ብ​ንም ተው፤ የማ​ይ​ሞ​ተ​ው​ንም ልበስ፤ እን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ከዚህ ዓለም ትሸ​ጋ​ገር ዘንድ አፍ​ጥን።

15 ይች ያየ​ሃት ክፋት ዛሬ ደር​ሳ​ለ​ችና፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ከእ​ርሷ የም​ት​ከፋ ዳግ​መኛ ትደ​ረ​ጋ​ለ​ችና።

16 ዓለም እያ​ረ​ጀና እየ​ደ​ከመ በሚ​ሄድ መጠን እን​ዲሁ በው​ስጡ የሚ​ኖሩ ክፋ​ታ​ቸው ትበ​ዛ​ለ​ችና።

17 እው​ነት ትጠ​ፋ​ለ​ችና፥ አሰ​ትም ትጸ​ና​ለ​ችና። ይህ ያየ​ኸ​ውም ንስር ይደ​ርስ ዘንድ ይቸ​ኵ​ላ​ልና።”

18 እኔም መለ​ስ​ሁ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አል​ሁት፥ “እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ በፊ​ትህ እና​ገ​ራ​ለሁ።

19 አቤቱ፥ እኔ እሄ​ዳ​ለ​ሁና፥ እንደ አዘ​ዝ​ኸ​ኝም ዛሬ ያሉ​ትን ሕዝብ አስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና። እን​ግ​ዲህ ወዲህ ዳግ​መኛ የሚ​ወ​ለ​ዱ​ትን ማን ያስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ዋል?

20 ዓለም በጨ​ለማ ውስጥ አለና፤ በው​ስጡ ለሚ​ኖ​ሩ​ትም ብር​ሃን የላ​ቸ​ውም።

21 ኦሪ​ትህ ተቃ​ጥ​ላ​ለ​ችና፥ የሠ​ራ​ኸ​ውን፥ ትሠ​ራ​ውም ዘንድ ያለ​ህን የሚ​ያ​ው​ቀው የለ​ምና።

22 በፊ​ት​ህስ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን ካገ​ኘሁ፥ ቅዱስ መን​ፈ​ስ​ህን ላክ​ልኝ፤ እኔም ሰው የሕ​ይ​ወት መን​ገ​ድን ማግ​ኘት ይችል ዘንድ፥ ሊኖሩ የሚ​ወ​ድዱ ሰዎ​ችም ይድኑ ዘንድ ከጥ​ንት ጀምሮ በዓ​ለም የሆ​ነ​ውን ሁሉና በኦ​ሪ​ትህ ውስጥ ተጽፎ ያለ​ውን እጽ​ፋ​ለሁ።”

23 እር​ሱም መለ​ሰ​ልኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ሄደህ ወገ​ኖ​ች​ህን ሰብ​ስ​ባ​ቸው፤ እስከ አርባ ቀንም ድረስ እን​ዳ​ይ​ፈ​ል​ጉህ ንገ​ራ​ቸው።

24 አንተ ግን ብዙ ብራና አዘ​ጋጅ፥ ከአ​ን​ተም ጋራ ሶር​ያን፥ ደር​ብ​ያን፥ ሰላ​ም​ያን፥ ኢቀ​ና​ን​ንና አሳ​ሄ​ልን እኒ​ህን አም​ስ​ቱን ሰዎች ውሰ​ዳ​ቸው። እነ​ርሱ በመ​ጻፍ ጠቢ​ባን ናቸ​ውና።

25 ወደ​ዚህ ና፤ በል​ቡ​ና​ህም የጥ​በብ መብ​ራ​ትን አበ​ራ​ለሁ፤ ትጽ​ፍም ዘንድ ያለ​ህን ሁሉ እስ​ክ​ት​ጨ​ርስ ድረስ እን​ግ​ዲህ አት​ጠ​ፋም።

26 በጨ​ረ​ስህ ጊዜ ግልጥ የም​ታ​ደ​ር​ገው አለ፤ የም​ት​ሠ​ው​ረ​ውም አለ፤ ለዐ​ዋ​ቂ​ዎ​ችም፥ ለጠ​ቢ​ባ​ንም ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ነገ በዚህ ሰዓት ትጽፍ ዘንድ ትጀ​ም​ራ​ለህ።”

27 እንደ አዘ​ዘ​ኝም ሄጄ ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰበ​ሰ​ብሁ።

28 እን​ዲ​ህም አል​ኋ​ቸው፥ “እስ​ራ​ኤል፥ ይህን ነገር ስሙ።

29 አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ቀድሞ በግ​ብጽ ምድር ኖሩ፤ ከዚ​ያም ተቤ​ዣ​ቸው።

30 የሕ​ይ​ወት ሕግ​ንም ተቀ​በሉ፤ ግን አል​ጠ​በ​ቁም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ያላ​ች​ሁት እና​ንተ ካዳ​ች​ሁት።

31 ምድረ ርስ​ትን ሰጠን፤ የጽ​ዮ​ን​ንም ምድር አወ​ረ​ሰን፤ እና​ን​ተም፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ካዳ​ች​ሁት፤ እር​ሱ​ንም መበ​ደል አል​ተ​ዋ​ች​ሁም፤ የአ​ዘ​ዛ​ችሁ የል​ዑል መን​ገ​ድን አል​ጠ​በ​ቃ​ች​ሁም።

32 እርሱ እው​ነት ፈራጅ ነውና በጊ​ዜው የሰ​ጣ​ች​ሁን ቀማ​ችሁ።

33 አሁ​ንም እና​ንተ በዚህ አላ​ችሁ፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ግን ከእ​ና​ንተ ተለ​ይ​ተው በው​ስጥ ናቸው።

34 ልቡ​ና​ች​ሁን ያስ​ገ​ዛ​ች​ሁት፥ ሕሊ​ና​ች​ሁ​ንም የገ​ሠ​ጻ​ች​ሁት እንደ ሆነ፥ ሕይ​ወ​ታ​ች​ሁ​ንም የጠ​በ​ቃ​ች​ሁት እንደ ሆነ አት​ሞ​ቱም።

35 ከሞት በኋላ ፍርድ ይመ​ጣ​ልና፥ እኛ​ንም በሕ​ይ​ወት አያ​ኖ​ረ​ን​ምና፥ ያን​ጊ​ዜም የጻ​ድ​ቃን ስማ​ቸው ይገ​ለ​ጣል፤ የኃ​ጥ​ኣ​ንም ሥራ​ቸው ይገ​ለ​ጣል።

36 ከእ​ና​ንተ ወደ እኔ የሚ​መጣ አይ​ኑር፤ እስከ አርባ ቀንም ድረስ አት​ፈ​ል​ጉኝ።”

37 እን​ዳ​ዘ​ዘ​ኝም እነ​ዚ​ያን አም​ስ​ቱን ሰዎች ይዤ ወደ ምድረ በዳው ሄድን፤ በዚ​ያም ተቀ​መ​ጥን።

38 በማ​ግ​ሥ​ቱም ቃል መጣ፥ “ዕዝራ! ዕዝራ!” ብሎ ጠርቶ እን​ዲህ አለኝ፥ “አፍ​ህን ክፈት እኔም የማ​ጠ​ጣ​ህን ጠጣ።”

39 አፌ​ንም በከ​ፈ​ትሁ ጊዜ ውኃ የተ​መላ፥ መልኩ እሳት የሚ​መ​ስል መጠ​ጥን አጠ​ጣኝ።

40 ተቀ​ብ​ዬም ጠጣ​ሁት፤ ልቡ​ና​ዬም ፈጽሞ ዕው​ቀ​ትን ተና​ገረ፤ ዕው​ቀ​ትም በል​ቡ​ናዬ በዛ፤ ነፍ​ሴም ትጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለች፤ ታስ​በ​ዋ​ለ​ችም።

41 አፌም ተከ​ፈተ፤ ከዚ​ያም ወዲያ ዝም አላ​ለም።

42 ልዑ​ልም ለእ​ነ​ዚያ ለአ​ም​ስቱ ሰዎች ጥበ​ብን ሰጣ​ቸው፤ የማ​ያ​ው​ቁ​ት​ንም ምል​ክት የሆ​ነ​ውን ይህን ሁሉ በማ​ከ​ታ​ተል ጻፉ፤ በዚ​ያም አርባ ቀን ተቀ​መጡ፤ እነ​ር​ሱም ቀን ቀን ይጽፉ ነበር፤ ማታ ማታም እህል ይመ​ገቡ ነበር፤

43 እኔ ግን ቀን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ሌሊ​ትም ዝም አል​ልም።

44 በእ​ነ​ዚያ በአ​ርባ ቀኖ​ችም ሃያ አራት መጻ​ሕ​ፍት ተጻፉ።

45 ከዚ​ህም በኋላ እነ​ዚያ አርባ ቀኖች በተ​ፈ​ጸሙ ጊዜ ልዑል ተና​ገ​ረኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “አስ​ቀ​ድሞ የጻ​ፋ​ች​ሁ​ትን ያን ግልጥ አድ​ር​ገው፤ የሚ​ገ​ባ​ውም የማ​ይ​ገ​ባ​ውም ሁሉ ያን​ብ​በው።

46 ይህን ግን ለጠ​ቢ​ባን ሕዝብ ትሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ጠብቅ።

47 በእ​ነ​ዚህ ውስጥ የማ​ስ​ተ​ዋል መብ​ራት፥ የጥ​በብ ምንጭ፥ የዕ​ው​ቀ​ትም ፈሳሽ አለና።”

48 እን​ዲ​ሁም አደ​ረ​ግሁ፤ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት፥ ከዓ​መ​ታቱ ሱባ​ዔ​ያት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ሱባዔ፥ ከፍ​ጥ​ረተ ዓለም በኋላ በአ​ም​ስት ሺህ ዓመ​ታት፥ ጨረቃ ሠርቅ ባደ​ረ​ገች በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን በሦ​ስ​ተ​ኛው ወር፥ በዘ​ጠና አንድ ቀናት።

49 ያን​ጊዜ ይህን ሁሉ ከጻፈ በኋላ ዕዝ​ራን ይዘው እንደ እርሱ ያሉ ሰዎች ወዳ​ሉ​በት ሀገር ወሰ​ዱት፤ እር​ሱም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ የል​ዑል የጥ​በቡ ጸሓፊ ተባለ። የዕ​ዝራ መጽ​ሐፍ ተፈ​ጸመ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይግ​ባው፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ አሜን።

Follow us:



Advertisements