Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -


This book is not inspired by God and is not part of the Christian canon or the Jewish Tanakh. It is shown only for historical and study purposes. View full explanation

መጽሐፈ ባሮክ 5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ኢየሩሳሌም ሆይ የኀዘንና የመከራ ልብስሽን አውልቂ፥ ለዘለዓለም ከእግዚአብሔር ክብር የሚወጣውን ውብት ልበሺ።

2 ከእግዚአብሔር የሚመጣውን የጽድቅ ካባ ደርቢ፤ የዘላለማዊውን የክብር አክሊል በራስሽ ላይ ድፊ።

3 እግዚአብሔር የብርሃንሽን ነጸብራቅ ከሰማይ በታች ላሉ ሁሉ ያሳያልና፤

4 ስምሽ ከእግዚአብሔር ዘንድለዘለዓለም “ሰላም፥ ጽድቅና እግዚአብሔርን የመፍራት ክብር” ተብሎ ይጠራል።

5 ኢየሩሳሌም ሆይ ተነሺ! በከፍታ ላይ ቁሚ፤ ወደ ምሥራቅም ተመልከቺ፥ እግዚአብሔር ስላሰባቸው በመደሰት በቅዱሱ ቃል ከምሥራቅና ከምዕራብ የተሰበሰቡትን ልጆችሽን እዪ፤

6 በጠላቶቻቸው ከአንቺ ሲወሰዱ በእግር ነበር፤ እግዚአብሔር ግን እንደ ንጉሥ ዙፋን በክብር ወደ አንቺ ይመልሳቸል።

7 እስራኤል በሰላም በእግዚአብሔር ክብር እንዲሄድ፥ እግዚአብሔር ረጃጅም ተራሮች ሁሉና ኮረብታዎች ዝቅእንዲሉ፥ ሸለቆዎች እንዲሞሉ፥ መሬትም እንዲስተካከል አዟልና።

8 በእግዚአብሔር ትእዛዝ ጫካዎችና መልካም መዓዛ ያለው ዛፍ ሁሉ እስራኤልን በጥላቸው ጋረዱ።

9 እግዚአብሔር እስራኤልን በደስታ፥ በክብሩ ብርሃን፥ ከእርሱ በሚመጣ በምሕረቱና በጽድቁ ይመራቸዋልና።

Follow us:



Advertisements