Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሶፎንያስ 3:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አሕዛብን አጥፍቻለሁ፣ ግንቦቻቸው ሁሉ ፈርሰዋል፣ መንገዳቸውን ማንም እንዳያልፍባት ምድረ በዳ አድርጌአለሁ፥ ከተሞቻቸውም ማንም እንዳይኖርባቸው፥ አንድስ እንኳ እንዳይቀመጥባቸው ፈርሰዋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ሕዝቦችን አጥፍቻለሁ፤ ምሽጋቸው ተደምስሷል፤ ማንም እንዳያልፍባቸው፣ መንገዳቸውን ባድማ አደረግሁ፤ ከተሞቻቸው ተደምስሰዋል፤ አንድም ሰው የለም፤ ነዋሪም ከቶ አይገኝባቸውም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 መንግሥታትን አጥፍቻለሁ፥ ግንቦቻቸው ሁሉ ፈርሰዋል፥ መንገዶቻቸውን ማንም የማይተላለፍባቸው ባዶ ሆነዋል፥ ከተሞቻቸውም አንድም ሰው እንዳይገኝባቸው፥ ማንም የማይኖርባቸው ሆነዋል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአሕዛብ “መንግሥታትን አጠፋሁ፤ ምሽጎቻቸውን አፈራረስኩ፤ መንገዶቻቸውን ማንም የማይተላለፍባቸው ባዶ አድርጌአቸዋለሁ፤ ከተሞቻቸውን ሕዝብ የሌለባቸው፥ ማንም የማይኖርባቸው ባድማ አድርጌአቸዋለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 አሕዛብን አጥፍቻለሁ፥ ግንቦቻቸው ሁሉ ፈርሰዋል፥ መንገዳቸውን ማንም እንዳያልፍባት ምድረ በዳ አድርጌአለሁ፥ ከተሞቻቸውም ማንም እንዳይኖርባቸው፥ አንድስ እንኳ እንዳይቀመጥባቸው ፈርሰዋል።

See the chapter Copy




ሶፎንያስ 3:6
19 Cross References  

እነ​ርሱ እንደ ተመኙ እኛ ደግሞ ክፉ እን​ዳ​ን​መኝ እነ​ርሱ ለእኛ ምሳሌ ሆኑ​ልን።


እነ​ር​ሱን ያገ​ኛ​ቸው ይህ ሁሉ ነገር በኋላ ዘመን ለም​ን​ነ​ሣው ለእኛ ትም​ህ​ር​ትና ምክር ሊሆ​ነን ምሳሌ ሆኖ ተጻፈ።


በባሕር ዳር ለሚኖሩ ለከሊታውያን ሕዝብ ወዮላቸው! የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፥ የእግዚአብሔር ቃል በአንተ ላይ ነው፥ የሚቀመጥብህም ሰው እንዳይኖር አጠፋሃለሁ።


ወደ ማያውቁአቸውም አሕዛብ ሁሉ በዐውሎ ነፋስ በተንኋቸው። እንዲሁ ከእነርሱ በኋላ ምድሪቱ ባድማ ሆናለች፥ የሚተላለፍባትና የሚመላለስባትም አልነበረም፣ ያማረችውንም ምድር ባድማ አደረጉአት።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወጣ፤ ከአ​ሦ​ራ​ው​ያ​ንም ሰፈር መቶ ሰማ​ንያ አም​ስት ሺህ ሰዎ​ችን ገደለ፤ ማለ​ዳም በተ​ነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉም በድ​ኖች ሆነው አገ​ኙ​አ​ቸው።


ከተ​ሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም ባድማ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ መቅ​ደ​ሶ​ቻ​ች​ሁ​ንም አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንም መዓዛ አላ​ሸ​ት​ትም።


እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል።


እኔም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አልሁ። እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አለኝ፥ “ከተ​ሞች የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸ​ውን አጥ​ተው እስ​ኪ​ፈ​ርሱ ድረስ፥ ቤቶ​ችም ሰው አልቦ እስ​ኪ​ሆኑ፥ ምድ​ርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስ​ክ​ት​ቀር ድረስ ነው፤”


በም​ድር ሁሉ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሰ​በው ዐሳብ ይህ ነው፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ የተ​ዘ​ረ​ጋች እጅ ይህች ናት።


ይህን የሚ​ያ​ስ​ተ​ውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ያወ​ራስ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ለማን ተና​ገረ? ሰው እን​ዳ​ያ​ል​ፍ​ባት ምድ​ርስ ስለ ምን ጠፋች፤ እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተቃ​ጠ​ለች?


እነሆ እኔ ካጠ​ፋ​ኋ​ቸው አሕ​ዛብ ሁሉ ጋር ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ጀምሮ በፀ​ሐይ መግ​ቢያ እስ​ካ​ለው እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ለነ​ገ​ዶ​ቻ​ችሁ ርስት እን​ዲ​ሆኑ የቀ​ሩ​ትን እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ በዕጣ ከፈ​ል​ሁ​ላ​ችሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements