Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሶፎንያስ 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በዚያም ቀን በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን፥ የጌታቸውን ቤት ዓመፃንና ሽንገላን የሚሞሉትን እቀጣለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በዚያ ቀን፣ በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን ሁሉ፣ የአማልክታቸውን ቤት፣ በዐመፅና በማጭበርበር የሚሞሉትን እቀጣለሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በዚያን ቀን በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን፥ የጌታቸውን ቤት በዓመፅና በማታለል የሚሞሉትን እቀጣለሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በዚያን ቀን በአሕዛብ የአምልኮ ሥርዓት በቤተ መቅደሱ መድረክ ላይ እየዘለሉ የሚያመልኩትንና የጌታቸውን ቤት በዓመፅና በማታለል በተገኙ ዕቃዎች የሚሞሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በዚያም ቀን በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን፥ የጌታቸውን ቤት ዓመፃንና ሽንገላን የሚሞሉትን እቀጣለሁ።

See the chapter Copy




ሶፎንያስ 1:9
11 Cross References  

ስለ​ዚ​ህም የዳ​ጎን ካህ​ናት፥ ወደ ዳጎን ቤት የሚ​ገ​ቡ​ትም ሁሉ በአ​ዛ​ጦን ያለ​ውን የዳ​ጎ​ንን መድ​ረክ እስከ ዛሬ ድረስ አይ​ረ​ግ​ጡም፤ ይራ​መ​ዱት ነበር እንጂ።


“በፊቷ የሚ​መ​ጣ​ባ​ትን አላ​ወ​ቀ​ችም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በሀ​ገ​ራ​ቸው ቅሚ​ያ​ንና ግፍን የሚ​ያ​ከ​ማቹ ናቸው።”


ጌቶ​ች​ዋም የም​ታ​ገ​ባ​ላ​ቸው የጥ​ቅ​ማ​ቸው ተስፋ እንደ ቀረ ባዩ ጊዜ ጳው​ሎ​ስ​ንና ሲላ​ስን ይዘው በገ​በያ እየ​ጐ​ተቱ ወደ ገዢ​ዎች ወሰ​ዱ​አ​ቸው።


ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው የነ​በ​ሩት አለ​ቆች ግን በሕ​ዝቡ ላይ አክ​ብ​ደው ነበር፤ ስለ እን​ጀ​ራ​ውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወ​ስዱ ነበር፤ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ በሕ​ዝቡ ላይ ይሰ​ለ​ጥኑ ነበር። እኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ፈራሁ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ግ​ሁም።


ጌታ​ዋም ማለዳ ተነሣ፤ የቤ​ቱ​ንም ደጅ ከፈተ፤ መን​ገ​ዱ​ንም ለመ​ሄድ ወጣ፤ እነ​ሆም፥ ዕቅ​ብቱ ሴት በቤቱ ደጃፍ ላይ ወድቃ፥ እጆ​ች​ዋም በመ​ድ​ረኩ ላይ ወድ​ቀው አገ​ኛት።


ቀፎ ወፎ​ችን እን​ደ​ሚ​ሞላ፥ እን​ዲሁ ቤታ​ቸው ሽን​ገ​ላን ሞል​ታ​ለች፤ በዚ​ህም ከብ​ረ​ዋል ባለ​ጸ​ጎ​ችም ሆነ​ዋል።


ባለ ጠጎችዋን ግፍ ሞልቶባቸዋል፥ በእርስዋም የሚኖሩ በሐሰት ተናግረዋል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ተንኰለኛ ነው።


እኔም፦ ምንድር ናት? አልሁ። እርሱም፦ ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ ናት አለኝ። ደግሞም፦ በምድር ሁሉ ላይ ያለ በደላቸው ይህ ነው አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements