Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሩት 4:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የቅርብ ዘመዱም፦ የራሴን ርስት እንዳላበላሽ መቤዠት አልችልም፣ እኔ መቤዠቱን አልችልምና አንተ ከእኔ መቤዠቱን ውሰደው አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ያም ቅርብ የሥጋ ዘመድ፣ “እንዲህ ከሆነማ የራሴን ርስት አደጋ ላይ ልጥል ስለምችል፣ እኔ ልቤዠው አልችልም፤ አንተው ራስህ ተቤዠው” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የቅርብ ዘመዱም፦ “የራሴን ርስት እንዳላበላሽ መውሰድ አልችልም፥ እኔ የራሴ ላደርገው አልችልምና አንተ እንድትወስደው ፈቅጄልሃለሁ” አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ሰውየውም “ይህን ብወስድ የራሴን ድርሻ የሚጐዳ ስለ ሆነ እኔ ልወስደው አልፈልግምና አንተ እንድትወስደው ፈቅጄልሃለሁ” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የቅርብ ዘመዱም “የራሴን ርስት እንዳላበላሽ መቤዠት አልችልም፤ እኔ መቤዠቱን አልችልምና አንተ ከእኔ መቤዠቱን ውሰደው፤” አለ።

See the chapter Copy




ሩት 4:6
8 Cross References  

ዛሬ ሌሊት እደሪ፣ ነገም እርሱ ዋርሳ መሆን ቢወድድ መልካም ነው፥ ዋርሳ ይሁን፣ ዋርሳ ሊሆን ባይወድድ ግን፥ ሕያው እግዚአብሔርን እኔ ዋርሳ እሆንሻለሁ፣ እስኪነጋ ድረስ ተኚ።


ወን​ድ​ም​ህም ቢደ​ኸይ፥ ከር​ስ​ቱም ቢሸጥ፥ ለእ​ርሱ የቀ​ረበ ዘመዱ መጥቶ ወን​ድሙ የሸ​ጠ​ውን ይቤ​ዠ​ዋል።


ያም ሰው የወ​ን​ድ​ሙን ሚስት ማግ​ባት ባይ​ወ​ድድ፥ ዋር​ሳ​ዪቱ በበሩ አደ​ባ​ባይ ወደ​ሚ​ቀ​መጡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሄዳ፦ ‘ዋር​ሳዬ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ለወ​ን​ድሙ ስም ማቆም እንቢ አለ፤ ከእ​ኔም ጋር ሊኖር አል​ወ​ደ​ደም’ ትበ​ላ​ቸው።


ይሁ​ዳም አው​ና​ንን፥ “ወደ ወን​ድ​ምህ ሚስት ግባ፤ አግ​ባ​ትም፤ ለወ​ን​ድ​ም​ህም ዘርን አቁ​ም​ለት” አለው።


የከ​ተ​ማ​ውም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጠር​ተው ይጠ​ይ​ቁት፤ እር​ሱም በዚያ ቆሞ፦ ‘አገ​ባት ዘንድ አል​ወ​ድ​ድም’ ቢል፥


ዋር​ሳ​ዪቱ በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፦ ‘የወ​ን​ድ​ሙን ቤት በማ​ይ​ሠራ ሰው ላይ እን​ዲህ ይደ​ረ​ግ​በ​ታል’ ስትል የአ​ንድ እግ​ሩን ጫማ ታውጣ፤ በፊ​ቱም እን​ትፍ ትበ​ል​በት።


ኑኃሚንም ምራትዋን፦ ቸርነቱን በሕያዋንና በሙታን ላይ አልተወምና በእግዚአብሔር የተባረከ ይሁን አለቻት። ኑኃሚንም ደግሞ፦ ይህ ሰው የቅርብ ዘመዳችን ነው፥ እርሱም ሊቤዡን ከሚችሉት አንዱ ነው አለቻት።


እርሱም፦ ማን ነሽ? አለ። እርስዋም፦ እኔ ባሪያህ ሩት ነኝ፣ ዋርሳዬ ነህና ልብስህን በባሪያህ ላይ ዘርጋ አለችው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements