Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሩት 2:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሄደችም፥ ከአጫጆችም በኋላ በእርሻ ውስጥ ቃረመች፣ እንደ አጋጣሚውም የአቤሜሌክ ወገን ወደ ነበረው ወደ ቦዔዝ እርሻ ደረሰች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስለዚህ እርሷም ወጣች፤ ከዐጫጆች ኋላ ኋላ እየተከታተለችም ከአዝመራው ቦታ ትቃርም ጀመር፤ እንዳጋጣሚ ትቃርምበት የነበረው አዝመራ ከአሊሜሌክ ጐሣ የሆነው የቦዔዝ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ስለዚህም ሄደች፥ ከአጫጆችም በኋላ በእርሻ ውስጥ ቃረመች፥ እንደ አጋጣሚም የኤሊሜሌክ ወገን ወደነበረው ወደ ቦዔዝ እርሻ ደረሰች።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሩትም ወደ እርሻዎች ሄደች፤ ከአጫጆች ኋላ እየተከተለችም ከእጃቸው የወዳደቀውን ዛላ ትቃርም ጀመር፤ እንደ አጋጣሚ የምትቃርምበት ቦታ የአቤሜሌክ ዘመድ የሆነው የቦዔዝ እርሻ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሄደችም፤ ከአጫጆችም በኋላ በእርሻ ውስጥ ቃረመች፤ እንደ አጋጣሚውም የአቤሜሌክ ወገን ወደ ነበረው ወደ ቦዔዝ እርሻ ደረሰች።

See the chapter Copy




ሩት 2:3
10 Cross References  

እንደነዚህ ያሉትንም በጸጥታ እየሠሩ የገዛ እንጀራቸውን ይበሉ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን፤ እንመክራቸውማለን።


አንድ ካህ​ንም በዚ​ያች መን​ገድ ሲወ​ርድ ድን​ገት አገ​ኘው፤ አይ​ቶም አል​ፎት ሄደ።


ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም።


እር​ሱም የሞ​ተ​ውን ሕፃን እንደ አስ​ነሣ ለን​ጉሡ ሲና​ገር፥ እነሆ፥ ልጅ​ዋን ያስ​ነ​ሣ​ላት ያች ሴት መጥታ ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ወደ ንጉሥ ጮኸች፥ ግያ​ዝም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ሴቲቱ ይህች ናት፤ ኤል​ሳ​ዕም ያስ​ነ​ሣው ልጅዋ ይህ ነው፤” አለ።


ሞዓባዊቱም ሩት ኑኃሚንን፦ በፊቱ ሞገስ የማገኘውን ተከትዬ እህል እንድቃርም ወደ እርሻ ልሂድ አለቻት። እርስዋም፦ ልጄ ሆይ፥ ሂጂ አለቻት።


እነሆም፥ ቦዔዝ ከቤተ ልሔም መጣ፥ አጫጆችንም፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን አላቸው። እነርሱም፦ እግዚአብሔር ይባርክህ ብለው መለሱለት።


ወሬ​ውን ያመ​ጣ​ለት ጎል​ማ​ሳም አለ፥ “በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ተዋ​ግ​ተው ወደቁ፤ እነ​ሆም፥ ሳኦል በጦሩ ላይ ተኝቶ ነበር፤ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞ​ችም ተከ​ት​ለው ደረ​ሱ​በት።


በዚ​ያም አንድ ብን​ያ​ማዊ የቢ​ኮሪ ልጅ ስሙ ሳቡሄ የሚ​ባል የዐ​መፅ ልጅ የሆነ ሰው ነበረ፤ እር​ሱም፥ “ከዳ​ዊት ዘንድ እድል ፋንታ የለ​ንም፦ ከእ​ሴ​ይም ልጅ ዘንድ ርስት የለ​ንም፤ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እያ​ን​ዳ​ን​ድህ ወደ ድን​ኳ​ንህ ተመ​ለስ” ብሎ መለ​ከት ነፋ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements