Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሩት 1:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሁለቱም እስከ ቤተ ልሔም ድረስ ሄዱ። ወደ ቤተ ልሔምም በደረሱ ጊዜ የከተማይቱ ሰዎች ሁሉ ስለ እነርሱ፦ ይህች ኑኃሚን ናትን? እያሉ ተንጫጩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከዚያም ሁለቱ ሴቶች እስከ ቤተ ልሔም ድረስ ተጓዙ፤ ቤተ ልሔም እንደ ደረሱም፣ በእነርሱ ምክንያት ከተማው በሙሉ ተተረማመሰ፤ ሴቶቹም፣ “ይህች ኑኃሚን ናትን?” በማለት ተገረሙ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ስለዚህ ሁለቱም እስከ ቤተልሔም ድረስ ሄዱ። ወደ ቤተልሔምም በደረሱ ጊዜ፥ ያገሩ ሰዎች ሁሉ ታወኩ ስለ እነርሱ፥ ሴቶቹም፦ “ይህች ናዖሚን ናትን?” አሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ስለዚህ ሁለቱም አብረው ወደ ቤተልሔም ተጓዙ፤ ቤተልሔም ሲደርሱም የከተማው ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፤ እዚያም ያሉ ሴቶች በመደነቅ “በእርግጥ ይህች ናዖሚ ናትን?” አሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ሁለቱም እስከ ቤተ ልሔም ድረስ ሄዱ። ወደ ቤተ ልሔምም በደረሱ ጊዜ የከተማይቱ ሰዎች ሁሉ ስለ እነርሱ “ይህች ኑኃሚን ናትን?” እያሉ ተንጫጩ።

See the chapter Copy




ሩት 1:19
6 Cross References  

ወደ ኢየሩሳሌምም በገባ ጊዜ መላው ከተማ “ይህ ማን ነው?” ብሎ ተናወጠ።


ሳም​ኬት። መን​ገድ ዐላ​ፊ​ዎች ሁሉ እጃ​ቸ​ውን ያጨ​በ​ጭ​ቡ​ብ​ሻል፦ “በውኑ የም​ድር ሁሉ ደስታ፥ አክ​ሊ​ልና ክብር የሚ​ሉ​አት ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍ​ዋ​ጫሉ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ይነ​ቀ​ን​ቃሉ።


ተማ​ር​ካ​ችሁ ሂዱ እንጂ ይህች ዕረ​ፍት የእ​ና​ንተ አይ​ደ​ለ​ችም።


እርስዋም፦ ሁሉን የሚችል አምላክ አስመርሮኛልና ማራ በሉኝ እንጂ ኑኃሚን አትበሉኝ።


የአጫጆቹም አዛዥ፦ ይህችማ ከሞዓብ ምድር ከኑኃሚን ጋር የመጣች ሞዓባዊቱ ቆንጆ ናት፣


የቤተ ልሔም አባት ሰል​ሞን፥ የቤት ጋዲር አባት ኦሪ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements