Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሮሜ 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 መጽ​ሐ​ፍስ ምን ይላል? አብ​ር​ሃም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አመነ፤ ጽድ​ቅም ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 መጽሐፍስ ምን ይላል? “አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 መጽሐፉስ ምን አለና? “አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ቅዱስ መጽሐፍ “አብርሃም በእግዚአብሔር አመነ፤ እምነቱም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት” ይላል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቍኦጠረለት።

See the chapter Copy




ሮሜ 4:3
16 Cross References  

አብ​ራ​ምም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አመነ፤ ጽድ​ቅም ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት።


መጽሐፍም “አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት፤” ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።


እን​ግ​ዲህ ይህ ብፅ​ዕና ስለ መገ​ዘር ተነ​ገ​ረን? ወይስ ስለ አለ​መ​ገ​ዘር? እም​ነቱ ለአ​ብ​ር​ሃም ጽድቅ ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት እን​ላ​ለ​ንና።


ለማ​ይ​ሠራ ግን ኀጢ​አ​ተ​ና​ውን በሚ​ያ​ጸ​ድ​ቀው ካመነ እም​ነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈ​ጠ​ር​ለ​ታል።


ሳይ​ገ​ዘር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ር​ሃ​ምን በእ​ም​ነት እንደ አጸ​ደ​ቀው በእ​ርሱ ላይ ይታ​ወቅ ዘንድ ግዝ​ረ​ትን የጽ​ድቅ ማኅ​ተም ትሆ​ነው ዘንድ ምል​ክት አድ​ርጎ ሰጠው። ሳይ​ገ​ዘሩ ለሚ​ያ​ምኑ ሁሉ አባት ሊሆን፥ አብ​ር​ሃም በእ​ም​ነት እንደ ከበረ እነ​ር​ሱም በእ​ም​ነት እን​ደ​ሚ​ከ​ብሩ ያውቁ ዘንድ ሰጠው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረ​ቱን ለሰው ልጆ​ችም ድን​ቁን ንገሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ያወ​ቃ​ቸ​ውን ሕዝ​ቡን አል​ጣ​ላ​ቸ​ውም፤ ኤል​ያስ እስ​ራ​ኤ​ልን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል በከ​ሰ​ሳ​ቸው ጊዜ መጽ​ሐፍ ያለ​ውን አታ​ው​ቁ​ምን?


መጽ​ሐፍ፥ “የሚ​ያ​ም​ን​በት ሁሉ አያ​ፍ​ርም” ብሎ​አል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለፈ​ር​ዖን በመ​ጽ​ሐፍ እን​ዲህ አለው፥ “ኀይ​ሌን በአ​ንተ ላይ እገ​ልጥ ዘንድ፥ ስሜም በም​ድር ሁሉ ይሰማ ዘንድ ስለ​ዚህ አስ​ነ​ሣ​ሁህ።”


‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው።’ የሚለውን ይህን መጽሐፍ አላነበባችሁምን?”


ወይስ መጽሐፍ “በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል፤” ያለው በከንቱ እንደ ተናገረ ይመስላችኋልን?


ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም ይሉ ዘንድ፥ ለእ​ር​ሱም ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሕግን ለር​ዳታ ሰጥ​ቶ​አ​ልና።


በአሥራ አንደኛው ሰዓትም የገቡ መጥተው እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements