Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 79:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የኀ​ያ​ላን አም​ላክ፥ መል​ሰን፥ ፊት​ህ​ንም አብራ፥ እኛም እን​ድ​ና​ለን።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ፣ እንደ ውሃ አፈሰሱ፤ የሚቀብራቸውም አልተገኘም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ፥ የሚቀብራቸውም አጡ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ደማቸውንም እንደ ውሃ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ አፈሰሱ፤ የሞቱትንም የሚቀብር አንድ ሰው እንኳ አልነበረም።

See the chapter Copy




መዝሙር 79:3
15 Cross References  

“በክፉ ሞት ይሞ​ታሉ፤ አይ​ለ​ቀ​ስ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ቀ​በ​ሩ​ምም፤ ነገር ግን በመ​ሬት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ፤ በሰ​ይ​ፍም ይወ​ድ​ቃሉ፤ በራ​ብም ይጠ​ፋሉ፤ ሬሳ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለዱር አራ​ዊት መብል ይሆ​ናሉ።”


ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ቸ​ውም ሰዎች ከራ​ብና ከሰ​ይፍ የተ​ነሣ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መን​ገ​ዶች ይበ​ተ​ናሉ፤ ክፋ​ታ​ቸ​ው​ንም አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና እነ​ር​ሱ​ንና ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም የሚ​ቀ​ብ​ራ​ቸው አይ​ገ​ኝም።


ከወገኖችና ከነገዶችም ከቋንቋዎችም ከአሕዛብም የሆኑ ሰዎች ሦስት ቀን ተኵል በድናቸውን ይመለከታሉ፤ በድናቸውም ወደ መቃብር ሊገባ አይፈቅዱም።


በእርስዋም ውስጥ የነቢያትና የቅዱሳን ደም በምድርም የታረዱ ሁሉ ደም ተገኘባት።


ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ታላቅ ድንቅ አደነቅሁ።


የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፤ የሚገባቸው ነውና፤” ብሎ ሲናገር ሰማሁ።


መጽ​ሐፍ እን​ዳለ፥ “ስለ አንተ ዘወ​ትር ይገ​ድ​ሉ​ናል፤ እን​ደ​ሚ​ታ​ረዱ በጎ​ችም ሆነ​ናል።”


ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችኋል።


ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ፥ ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም ለሚ​ሹ​አት እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ሬሳ​ቸ​ውም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት መብል ይሆ​ናል።


በዚ​ያም ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግዳ​ዮች ከም​ድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆ​ናሉ፤ አይ​ለ​ቀ​ስ​ላ​ቸ​ውም፤ በም​ድር ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ እንጂ አይ​ሰ​በ​ሰ​ቡም፤ አይ​ቀ​በ​ሩ​ምም።


ሰይ​ፍን ለመ​ግ​ደል፥ ውሾ​ች​ንም ለመ​ጐ​ተት፥ የሰ​ማ​ያ​ት​ንም ወፎች፥ የም​ድ​ር​ንም አራ​ዊት ለመ​ብ​ላ​ትና ለማ​ጥ​ፋት፥ አራ​ቱን ዓይ​ነት ጥፋት አዝ​ዝ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አቤቱ፥ ስም​ህን አመ​ሰ​ግን ዘንድ ሰው​ነ​ቴን ከእ​ሥ​ራት አው​ጣት፤ ዋጋ​ዬን እስ​ክ​ት​ሰ​ጠኝ ድረስ ጻድ​ቃን እኔን ይጠ​ብ​ቃሉ።


ጥላዋ ተራ​ሮ​ችን ከደነ፥ ጫፎ​ች​ዋም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዝግባ ሆኑ።


በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ሠርተዋልና እንደ ዕውር እስኪሄዱ ድረስ ሰዎችን አስጨንቃለሁ፣ ደማቸውም እንደ ትቢያ፥ ሥጋቸውም እንደ ጕድፍ ይፈስሳል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements