Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 78:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አሕ​ዛብ፥ “አም​ላ​ካ​ቸው ወዴት ነው?” እን​ዳ​ይ​ሉን፥ የፈ​ሰ​ሰ​ውን የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህን ደም በቀል በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ችን ፊት አሕ​ዛብ ይዩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የእግዚአብሔርን ኪዳን አልጠበቁም፤ በሕጉም መሠረት ለመሄድ እንቢ አሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የእግዚአብሔርን ኪዳን አልጠበቁም፥ በሕጉም ለመመላለስ እንቢ አሉ፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤ ሕጉንም ለመፈጸም እምቢ አሉ።

See the chapter Copy




መዝሙር 78:10
9 Cross References  

ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ምድር ካገ​ባ​ኋ​ቸው በኋላ፥ ከበ​ሉም፥ ከጠ​ገ​ቡም በኋላ ይስ​ታሉ፤ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክ​ትም ወደ ማም​ለክ ይመ​ለ​ሳሉ፤ እኔ​ንም ያስ​ቈ​ጡ​ኛል፤ ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ያፈ​ር​ሳሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ ከአ​ባ​ቶ​ችህ ጋር ታን​ቀ​ላ​ፋ​ለህ፤ ይህም ሕዝብ ይነ​ሣል፤ ይቀ​መ​ጥ​ባ​ትም ዘንድ በሚ​ሄ​ድ​ባት ምድር መካ​ከል ያሉ​ትን ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ትሎ ያመ​ነ​ዝ​ራል፤ እኔ​ንም ይተ​ወ​ኛል፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን ያፈ​ር​ሳሉ።


ከግ​ብፅ ሀገር አወ​ጣ​ቸው ዘንድ እጃ​ቸ​ውን በያ​ዝ​ሁ​በት ቀን ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር እንደ ገባ​ሁት ያለ ቃል ኪዳን አይ​ደ​ለም፤ እነ​ርሱ በኪ​ዳኔ አል​ጸ​ኑ​ምና፥ እኔም ቸል አል​ኋ​ቸው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ትእ​ዛ​ዞ​ች​ንና ሕጎ​ችን ለመ​ስ​ማት እስከ መቼ እንቢ ትላ​ላ​ችሁ?


ለመ​ስ​ማ​ትም እንቢ አሉ፤ ያደ​ረ​ግ​ህ​ላ​ቸ​ው​ንም ተአ​ም​ራት አላ​ሰ​ቡም፤ አን​ገ​ታ​ቸ​ው​ንም አደ​ነ​ደኑ፤ ለባ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም ወደ ግብፅ ይመ​ለሱ ዘንድ አለ​ቃን ሾሙ፤ አንተ ግን መሓ​ሪና ይቅር ባይ አም​ላክ፥ ለቍ​ጣም የም​ት​ዘ​ገይ፥ ምሕ​ረ​ት​ንም የም​ታ​በዛ ነህ፤ አል​ተ​ው​ሃ​ቸ​ውም።


ልጆ​ቻ​ቸው ግን አማ​ረ​ሩኝ፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ፍር​ዴን ጠብ​ቀው አላ​ደ​ረ​ጉ​ትም፤ በሥ​ር​ዐ​ቴም አል​ሄ​ዱም፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አረ​ከሱ፤ በዚ​ህም ጊዜ፦ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬ​ንም በም​ድረ በዳ እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements