Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 73:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የም​ት​ገ​ዛ​ል​ህን ነፍስ ለአ​ራ​ዊት አት​ስ​ጣት፤ የድ​ሆ​ች​ህ​ንም ነፍስ ለዘ​ወ​ትር አት​ርሳ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እንዴት ፈጥነው በቅጽበት ጠፉ! በድንጋጤ ፈጽመው ወደሙ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ፥ በድንጋጤ ጠፉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በቅጽበት ተደመሰሱ፤ መጨረሻቸውም አስደንጋጭ ሆነ።

See the chapter Copy




መዝሙር 73:19
18 Cross References  

ስለ​ዚህ ምክ​ን​ያት ጥፋት ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ ጥል​ቀ​ቱን አታ​ው​ቂም፤ በው​ስ​ጡም ትወ​ድ​ቂ​ያ​ለሽ፤ ጕስ​ቁ​ልና ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ ማም​ለ​ጥም አይ​ቻ​ል​ሽም፤ ሞት ድን​ገት ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ አታ​ው​ቂ​ምም።


የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ደስታ ታላቅ ሰልፍ ነው፥ የዝ​ን​ጉ​ዎ​ችም ደስታ ጥፋት ነው።


የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግጥ ድም​ፅም በጆ​ሮው ነው፤ በደ​ኅ​ን​ነ​ትም ይኖር ዘንድ ተስፋ በሚ​ያ​ደ​ር​ግ​በት ጊዜ ጥፋት ይመ​ጣ​በ​ታል።


ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ! ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን! ወዮልሽ! ወዮልሽ! በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና፤” እያሉ ይናገራሉ።


ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ከቶም አያመልጡም።


እር​ሱ​ንም በተ​ወ​ሰ​ነው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክ​ርና በቀ​ደ​መው ዕው​ቀቱ እና​ንተ አሳ​ል​ፋ​ችሁ በኃ​ጥ​ኣን እጅ ሰጣ​ች​ሁት፤ ሰቅ​ላ​ች​ሁም ገደ​ላ​ች​ሁት።


ስለ​ዚህ ይህ በደል አዘ​ብ​ዝቦ ለመ​ፍ​ረስ እንደ ቀረበ፥ አፈ​ራ​ረ​ሱም ፈጥኖ ድን​ገት እን​ደ​ሚ​መጣ እንደ ከተማ ቅጥር ይሆ​ን​ባ​ች​ኋል።


ኀይ​ሌን ወደ አንተ አስ​ጠ​ጋ​ለሁ፥ አንተ አም​ላ​ኬና መጠ​ጊ​ያዬ ነህና።


መከራ በዙ​ሪ​ያው ታጠ​ፋ​ዋ​ለች፤ ብዙ ጠላ​ቶ​ችም ከእ​ግሩ በታች ይመ​ጣሉ።


ሳኦ​ልም በዚያ ጊዜ በቁ​መቱ ሙሉ በም​ድር ላይ ወደቀ፤ ከሳ​ሙ​ኤ​ልም ቃል የተ​ነሣ እጅግ ፈራ። በዚ​ያም ቀን ሁሉ፥ በዚ​ያም ሌሊት ሁሉ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ምና ኀይል አል​ቀ​ረ​ለ​ትም።


“ሁሉን በቅ​ጽ​በት አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ከዚህ ማኅ​በር መካ​ከል ፈቀቅ በሉ።”


ከዐ​ሥር ቀንም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናባ​ልን ቀሠ​ፈው፤ እር​ሱም ሞተ።


ሰውም ጊዜ​ውን አያ​ው​ቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠ​መዱ ዓሣ​ዎች ፥ በወ​ጥ​መ​ድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እን​ዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድ​ን​ገት ሲወ​ድ​ቅ​ባ​ቸው ይጠ​መ​ዳሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements