Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 72:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እነሆ፥ እነ​ዚህ ኃጥ​ኣን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ሁል​ጊ​ዜም ባለ​ጠ​ግ​ነ​ታ​ቸ​ውን ያጸ​ኗ​ታል፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ድኻው በጮኸ ጊዜ፣ ችግረኛውና ረዳት የሌለውን ይታደገዋል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ችግረኛውን ከቀማኛው እጅ፥ ረዳት የሌለውንም ምስኪን ያድነዋልና።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ወደ እርሱ የሚጮኹትን ድኾች፥ ችግረኞችንና የተጨቈኑትን ሰዎች ነጻ ያወጣል።

See the chapter Copy




መዝሙር 72:12
19 Cross References  

ድሃ​ውን ከሚ​ጨ​ቁ​ነው እጅ አድ​ኛ​ለ​ሁና። ረዳት የሌ​ለ​ውን ደሃ​አ​ደ​ጉ​ንም ረድ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታው ግን ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም በሚ​ፈ​ሩት ላይ፥ ጽድ​ቁም በልጅ ልጆች ላይ ነው፤


ዘወ​ትር በእ​ርሱ በኩል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​ቡ​ትን ሊያ​ድ​ና​ቸው ይቻ​ለ​ዋል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ሕያው ነውና ያስ​ታ​ር​ቃ​ቸ​ዋል።


እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ እነ​ሆም፥ የተ​ገ​ፉት ሰዎች እንባ ነበረ፤ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ቸ​ውም አል​ነ​በ​ረም፤ በሚ​ገ​ፉ​አ​ቸ​ውም እጅ ኀይል ነበረ። እነ​ር​ሱን ግን የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ቸው አል​ነ​በ​ረም።


የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ቸር​ነ​ቱን ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ በእ​ርሱ ድህ​ነት እና​ንተ ባለ​ጸ​ጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ባለ​ጸጋ ሲሆን፥ ስለ እና​ንተ ራሱን ድሃ አደ​ረገ።


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በላዬ ነው፤ ስለ​ዚህ ቀብቶ ለድ​ሆች የም​ሥ​ራ​ችን እነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ፥ ለተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ነጻ​ነ​ትን እሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ፥ ያዘ​ኑ​ት​ንም ደስ አሰ​ኛ​ቸው ዘንድ፥ ዕው​ሮ​ችም ያዩ ዘንድ፥ የተ​ገ​ፉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ የታ​ሰ​ሩ​ት​ንም እፈ​ታ​ቸው ዘንድ፥ የቈ​ሰ​ሉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥


ድሆ​ችና ምስ​ኪ​ኖች ውኃ ይሻሉ፤ አያ​ገ​ኙ​ምም፤ ምላ​ሳ​ቸ​ውም በጥ​ማት ደር​ቋል፤ እኔ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ማ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እኔ አል​ተ​ዋ​ቸ​ውም።


ለሞ​ታ​ቸው እረ​ፍት የለ​ው​ምና፤ ለመ​ቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸ​ውም ኀይል የለ​ው​ምና፤


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሄዳ​ችሁ ያያ​ች​ሁ​ት​ንና የሰ​ማ​ች​ሁ​ትን ለዮ​ሐ​ንስ ንገ​ሩት፤ ዕው​ሮች ያያሉ፤ አን​ካ​ሶ​ችም ይሄ​ዳሉ፤ ለም​ጻ​ሞ​ችም ይነ​ጻሉ፤ ደን​ቆ​ሮ​ችም ይሰ​ማሉ፤ ሙታ​ንም ይነ​ሣሉ፤ ለድ​ሆ​ችም ወን​ጌል ይሰ​በ​ካል።


ቃሉን የም​ት​ፈ​ጽሙ፥ ብር​ቱ​ዎ​ችና ኀያ​ላን፥ የቃ​ሉ​ንም ድምፅ የም​ት​ሰሙ መላ​እ​ክቱ ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤


የተ​ጨ​ነ​ቀም ሁሉ፥ ዕዳም ያለ​በት ሁሉ፥ የተ​ከ​ፋም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​ባ​ሰበ፤ እር​ሱም በላ​ያ​ቸው አለቃ ሆነ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ።


እኔ​ንና ልጄን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ያር​ቀን ዘንድ ከሚሻ ሰው እጅ ያድን ዘንድ ንጉሡ አገ​ል​ጋ​ዩን ይሰ​ማል አልሁ።”


የተ​ቸ​ገ​ረ​ው​ንና ረዳት የሌ​ለ​ውን አስ​ጨ​ን​ቀ​ዋ​ልና፥ የየ​ዋ​ሃ​ን​ንም ፍርድ ለው​ጠ​ዋ​ልና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements