Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 68:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በደጅ የሚ​ቀ​መጡ በእኔ ይጫ​ወ​ታሉ፤ ወይን የሚ​ጠ​ጡም በእኔ ይዘ​ፍ​ናሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “የሰራዊት ነገሥታት ፈጥነው ይሸሻሉ፤ በሰፈር የዋሉ ሴቶችም ምርኮን ተካፈሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጌታ ትእዛዙን ሰጠ፥ የሚያበሥሩት ብዙ ሠራዊት ናቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እንዲህም አሉ፦ “ነገሥታት ከነሠራዊታቸው ወደ ኋላቸው ሸሹ! በቤት የቀሩ ሴቶችም ምርኮን ተካፈሉ፤

See the chapter Copy




መዝሙር 68:12
12 Cross References  

እነ​ዚ​ህም አም​ስት ነገ​ሥት ሸሽ​ተው በመ​ቄዳ ዋሻ ተሸ​ሸጉ።


ነገ​ሥ​ታት መጡ፤ ተዋ​ጉም፤ በዚያ ጊዜ በመ​ጌዶ ውኆች አጠ​ገብ በቶ​ናሕ የከ​ነ​ዓን ነገ​ሥ​ታት ተዋጉ፤ በቅ​ሚ​ያም ብርን አል​ወ​ሰ​ዱም።


ይህ​ንስ ነገር ማን ይሰ​ማ​ች​ኋል? እና​ንተ ከእ​ነ​ርሱ አት​በ​ል​ጡ​ምና ወደ ጦር​ነት በሄ​ዱት ድርሻ ልክ ጓዝ የጠ​በቁ ሰዎች ድርሻ እን​ዲሁ ነው።”


የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኀይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዐለቶች ተሰወሩ፤


ምር​ኮ​ውን ሲካ​ፈል፥ በኀ​ያ​ላ​ኑም ቸብ​ቸቦ ላይ ወዳ​ጆ​ችን ሲወ​ዳጅ ያገ​ኙት አይ​ደ​ለ​ምን? የሲ​ሣራ ምርኮ በየ​ኅ​ብሩ ነበረ፤ የኅ​ብ​ሩም ቀለም የተ​ለ​ያየ ነበረ፤ የማ​ረ​ከ​ውም ወርቀ ዘቦ ግምጃ በአ​ን​ገቱ ላይ ነበረ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ስለ ተዋ​ጋ​ላ​ቸው ኢያሱ እነ​ዚ​ህን ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም በአ​ንድ ጊዜ ያዘ።


ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም ወር​ቁን ከሻ​ለ​ቆ​ችና ከመቶ አለ​ቆች ወሰዱ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን አገ​ቡት።


ምር​ኮ​ው​ንም በተ​ዋ​ጉ​ትና ወደ ሰልፍ በወ​ጡት፥ በማ​ኅ​በ​ሩም ሁሉ መካ​ከል ትከ​ፍ​ላ​ላ​ችሁ።


የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም መን​ኰ​ራ​ኵር አሰረ፤ ወደ ጭን​ቅም አገ​ባ​ቸው፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ ይዋ​ጋ​ላ​ቸ​ዋ​ልና ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት እን​ሽሽ” አሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements