Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 67:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አቤቱ፥ በሕ​ዝ​ብህ ፊት በወ​ጣህ ጊዜ፥ በም​ድረ በዳም ባለ​ፍህ ጊዜ፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እግዚአብሔር ይባርከናል፤ የምድርም ዳርቻዎች ሁሉ እርሱን ይፈሩታል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ምድር ፍሬዋን ሰጠች፥ እግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔር ስለሚባርከንም በምድር ዳርቻ ያሉ ሁሉ ይፈሩታል።

See the chapter Copy




መዝሙር 67:7
23 Cross References  

እና​ንተ በም​ድር ዳርቻ ያላ​ችሁ ሁሉ፥ እኔ አም​ላክ ነኝና፥ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለ​ምና ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ ትድ​ኑ​ማ​ላ​ችሁ።


“እና​ንተ ከአ​ብ​ር​ሃም ወገን የተ​ወ​ለ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የም​ት​ፈሩ፥ ይህ የሕ​ይ​ወት ቃል ለእ​ና​ንተ ተል​ኮ​አል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ታዩ ዘንድ ኑ። ምክሩ ከሰው ልጆች ይልቅ ግሩም ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ እስከ ምድር ዳርቻ ላሉት ሁሉ መድ​ኀ​ኒት ትሆን ዘንድ ለአ​ሕ​ዛብ ብር​ሃን አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ” ብሎ አዝ​ዞ​ና​ልና።


የሕ​ይ​ወ​ትን መን​ገድ አሳ​የ​ኸኝ፤ ከፊ​ትህ ጋራ ደስ​ታን አጠ​ገ​ብ​ኸኝ።


ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ልቅ​ሶ​ዬን መል​ሰህ ደስ አሰ​ኘ​ኸኝ። ማቄን ቀድ​ደህ ደስ​ታን አስ​ታ​ጠ​ቅ​ኸኝ።


አሁ​ንም የሚ​ያ​ምኑ ከአ​መ​ነው ከአ​ብ​ር​ሃም ጋር ይባ​ረ​ካሉ።


ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፣ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።


ሰረገላውንም ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም አጠፋለሁ የሰልፉም ቀስት ይሰበራል፥ ለአሕዛብም ሰላምን ይናገራል፣ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፥ ከወንዙም እስከ ምድር ዳርቻ ድርስ ይሆናል።


እርሱም ይቆማል፥ በእግዚአብሔርም ኃይል በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ግርማ መንጋውን ይጠብቃል፥ እነርሱም ይኖራሉ፥ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ይሆናልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ክን​ዱን በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ፊት ገል​ጦ​አል፤ በም​ድር ዳርቻ የሚ​ኖ​ሩ​ትም ሁሉ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ማዳን ያያሉ።


ሰሜ​ንን፦ መል​ሰህ አምጣ፤ ደቡ​ብ​ምን፦ አት​ከ​ል​ክል፤ ወን​ዶች ልጆ​ችን ከሩቅ፥ ሴቶች ልጆ​ች​ንም ከም​ድር ዳርቻ፥


ሁሉ ታላቅ ስም​ህን ያመ​ሰ​ግ​ናል፥ ግሩ​ምና ቅዱስ ነውና።


ፍጻ​ሜ​አ​ቸ​ውን አውቅ ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ እስ​ክ​ገባ ድረስ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ፥ ዕወ​ቁም፤ በእ​ርሱ የሚ​ታ​መን ሰው ብፁዕ ነው።


እኛ በክ​ር​ስ​ቶስ አም​ነን የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ተስፋ እን​ድ​ና​ገኝ የአ​ብ​ር​ሃም በረ​ከት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ወደ አሕ​ዛብ ይመ​ለስ ዘንድ።


ዝና​ሙን በወ​ቅቱ አዘ​ን​ማ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም እህ​ል​ዋን ትሰ​ጣ​ለች፤ የሜ​ዳው ዛፎ​ችም ፍሬ​ያ​ቸ​ውን ይሰ​ጣሉ።


በም​ድ​ርም ለተ​ዘ​ራው ዘርህ ዝናም ይዘ​ን​ማል፤ ከም​ድ​ርም ፍሬ የሚ​ወጣ እን​ጀራ ወፍ​ራ​ምና ብዙ ይሆ​ናል። በዚ​ያም ቀን ከብ​ቶ​ችህ በሰ​ፊና በለ​መ​ለመ መስክ ይሰ​ማ​ራሉ፤


ነገር ግን ሰላምን እዘራለሁ፣ ወይኑ ፍሬውን ይሰጣል፥ ምድርም አዝመራዋን ታወጣለች፥ ሰማያትም ጠላቸውን ይሰጣሉ፣ ለዚህም ሕዝብ ቅሬታ ይህን ነገር ሁሉ አወርሳለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements