Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 51:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ልብህ ኀጢ​አ​ትን ያስ​ባል፤ እንደ ተሳለ ምላጭ ሽን​ገ​ላን አደ​ረ​ግህ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በደሌን ፈጽሞ ዕጠብልኝ፤ ከኀጢአቴም አንጻኝ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ወደ ቤርሳቤህ ከገባ በኋላ ነቢዩ ናታን ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በደሌን ሁሉ አጥበህ አስወግድልኝ፤ ከኃጢአቴም አንጻኝ።

See the chapter Copy




መዝሙር 51:2
17 Cross References  

“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረዳቱ ያላ​ደ​ረገ፥ በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ቱም ብዛት የታ​መነ፥ በከ​ንቱ ነገ​ርም የበ​ረታ ያ ሰው እነሆ።”


ጥሩ ውኃ​ንም እረ​ጭ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ከር​ኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ትነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ አነ​ጻ​ች​ኋ​ለሁ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! ትድኚ ዘንድ ልብ​ሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። ክፉ አሳብ የሚ​ኖ​ር​ብሽ እስከ መቼ ነው?


እን​ግ​ዲህ እና​ንተ እን​ዲህ ስት​ሆኑ እነ​ማን ናችሁ? ነገር ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም መን​ፈስ ታጥ​ባ​ች​ኋል፤ ተቀ​ድ​ሳ​ች​ኋል፤ ጸድ​ቃ​ች​ኋ​ልም።


አሁ​ንም የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ልን​ገ​ርህ፦ ተነሥ ስሙን እየ​ጠ​ራህ ተጠ​መቅ፤ ከኀ​ጢ​አ​ት​ህም ታጠብ።’


ታጠቡ፤ ንጹ​ሓ​ንም ሁኑ፤ የሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁን ክፋት ከዐ​ይ​ኖች ፊት አስ​ወ​ግዱ፤ ክፉ ማድ​ረ​ግ​ንም ተዉ፤


እኔም “ጌታ ሆይ! አንተ ታውቃለህ፤” አልሁት። አለኝም “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።


በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ከኃጢአትና ከርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።


ልብሱ ወይም ድሩ ወይም ማጉ ወይም ከቆዳ የተ​ደ​ረ​ገው ነገር ከታ​ጠበ በኋላ ደዌው ቢለ​ቅ​ቀው ሁለ​ተኛ ጊዜ ይታ​ጠ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል።


ዳዊ​ትም መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልኮ አስ​መ​ጣት፤ ወደ እር​ሱም ገባች፤ ከር​ኵ​ሰ​ቷም ነጽታ ነበ​ርና ከእ​ር​ስዋ ጋር ተኛ፤ ወደ ቤቷም ተመ​ለ​ሰች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነቢዩ ናታ​ንን ወደ ዳዊት ላከ፤ ወደ እር​ሱም መጥቶ አለው፥ “በአ​ንድ ከተማ አንዱ ባለ​ጠጋ፥ አን​ዱም ድሃ የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም፥ “አቤቱ፥ እን​ኪ​ያስ የም​ታ​ጥ​በኝ እጆ​ች​ንና ራሴ​ንም እንጂ እግ​ሮ​ችን ብቻ አይ​ደ​ለም፤” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements