Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 43:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አቤቱ፥ በጆ​ሮ​አ​ችን ሰማን፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም በዘ​መ​ና​ቸው በቀ​ድሞ ዘመን የሠ​ራ​ኸ​ውን ሥራ ነገ​ሩን።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 አምላክ ሆይ፤ ፍረድልኝ፤ ካልታመኑህ ሕዝብ ጋራ ተሟገትልኝ፤ ከአታላዮችና ከክፉዎች ሰዎችም አድነኝ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 አቤቱ፥ ፍረድልኝ፥ ከጽድቅ በራቁም ሕዝብ ዘንድ ተሟገትልኝ፥ ከሸንጋይና ከግፈኛ ሰው አድነኝ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 አምላክ ሆይ! ፍረድልኝ፤ በአንተ ከማያምኑ አሕዛብ ፊት ስለ እኔ ተከራከርልኝ፤ ከአታላዮችና ከክፉ ሰዎችም እጅ አድነኝ።

See the chapter Copy




መዝሙር 43:1
21 Cross References  

ኀጢ​አ​ተኛ ራሱን የሚ​ያ​ስ​ት​በ​ትን ነገር ይና​ገ​ራል፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍር​ሀት በዐ​ይ​ኖቹ ፊት የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያበ​ራ​ል​ኛል፥ ያድ​ነ​ኛ​ልም፤ ምን ያስ​ፈ​ራ​ኛል? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሕ​ይ​ወቴ መታ​መ​ኛዋ ነው፤ ምን ያስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ኛል?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝብ ላይ ይፈ​ር​ዳል፤ አቤቱ አም​ላኬ፥ እንደ ጽድ​ቅህ ፍረ​ድ​ልኝ፤ እንደ የዋ​ህ​ነ​ቴም ይሁ​ን​ልኝ።


አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ማንን ለማ​ሳ​ደድ ወጥ​ተ​ሀል? አን​ተስ ማንን ታሳ​ድ​ዳ​ለህ? የሞተ ውሻን ታሳ​ድ​ዳ​ለ​ህን? ወይስ ቍን​ጫን ታሳ​ድ​ዳ​ለህ?


ለድ​ሆች ሕዝ​ብህ በጽ​ድቅ ፍረድ፥ የድ​ሆ​ች​ንም ልጆች አድ​ና​ቸው። ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ው​ንም አዋ​ር​ደው።


ሐሰ​ትን የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ሁሉ ትጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ደም አፍ​ሳ​ሹ​ንና ሸን​ጋ​ዩን ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​የ​ፋል።


በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን ለእኔ እስኪያደርግ ድረስ ቍጣውን እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቅንም አያለሁ።


ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤


የሚ​ያ​ጠ​ራ​ጥ​ረ​ኝና ትዝ የሚ​ለኝ ነገር የለም፤ በዚ​ህም ራሴን አላ​መ​ጻ​ድ​ቅም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ረ​ም​ረ​ኛ​ልና።


ታዳጊአቸው እግዚአብሔር ጽኑ ነውና፥ እርሱም ፍርዳቸውን ከአንተ ጋር ይፋረዳልና።


እግዚአብሔር ፍርዱን ይፈርድለታልና። አንተም ነፍስህን በሰላም ታድናለህ።


አንተ ግን፥ ግሩም ነህ፤ ቍጣ​ህን ማን ይቃ​ወ​ማል?


አቤ​ሴ​ሎ​ምም አኪ​ጦ​ፌ​ልን፦ ምን እን​ደ​ም​ና​ደ​ርግ ምከሩ አለው።


አኪ​ጦ​ፌል ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ጋር በሴራ አንድ ነው ብለው ለዳ​ዊት ነገ​ሩት፤ ዳዊ​ትም፥ “አቤቱ የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር ለውጥ” አለ።


ከዚ​ያም ጦሩ በሀ​ገሩ ሁሉ ፊት ተበ​ተነ፤ በዚ​ያም ቀን በሰ​ይፍ ከተ​ገ​ደ​ሉት ሕዝብ ይልቅ በበ​ረሓ የሞቱ ይበ​ዛሉ።


የአ​ሕ​ዛ​ብም ጉባኤ ይከ​ብ​ብ​ሃል፤ ስለ​ዚ​ህም ወደ አር​ያም ተመ​ለስ።


የኃ​ጥ​ኣን ክፋት ያል​ቃል፥ ጻድ​ቃ​ንን ግን ታቃ​ና​ቸ​ዋ​ለህ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ​ና​ንና ኵላ​ሊ​ትን ይመ​ረ​ም​ራል።


ከጠ​ላት ድምፅ፥ ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኛም ማሠ​ቃ​የት የተ​ነሣ፥ ዐመ​ፃን በላዬ መል​ሰ​ው​ብ​ኛ​ልና፥ ሊያ​ጠ​ፉ​ኝም ተነ​ሥ​ተ​ው​ብ​ኛ​ልና።


በጽ​ድቅ ገሥ​ጸኝ፥ በም​ሕ​ረ​ትም ዝለ​ፈኝ፥ የኀ​ጢ​አ​ተኛ ዘይ​ትን ግን ራሴን አል​ቀ​ባም፤ ዳግ​መ​ኛም ጸሎቴ ይቅር እን​ዳ​ት​ላ​ቸው ነውና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements