Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 40:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ጠላ​ቶ​ቼም በላዬ ክፋ​ትን ይና​ገ​ራሉ፦ “መቼ ይሞ​ታል? ስሙስ መቼ ይሻ​ራል?” ይላሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ ያደረግኸው ድንቅ ነገር ብዙ ነው፤ ለእኛ ያቀድኸውን፣ ሊዘረዝርልህ የሚችል ማንም የለም፤ ላውራው ልናገረው ብል፣ ስፍር ቍጥር አይኖረውም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጌታን የታመነ ወደ ትዕቢተኛና ወደ ሐሰተኛ ያልተመለከተ ሰው ብፁዕ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ብዙ አስደናቂ ነገሮችን አድርገህልናል፤ ከአንተ የሚወዳደር ማንም የለም፤ አንተ ለእኛ ያቀድክልንን መልካም ነገር ማንም ሊቈጥረው አይችልም፤ እኔ ስለ እነርሱ በዝርዝር ለመናገርና ለማውራት ብሞክር ቊጥራቸው እጅግ የበዛ ይሆንብኛል።

See the chapter Copy




መዝሙር 40:5
14 Cross References  

ለእ​ና​ንተ የማ​ስ​ባ​ትን አሳብ እኔ አው​ቃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ፍጻ​ሜና ተስፋ እሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ የሰ​ላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይ​ደ​ለም።


አቤቱ፦ በአ​ማ​ል​ክት መካ​ከል አን​ተን የሚ​መ​ስል ማን ነው? በቅ​ዱ​ሳ​ንም ዘንድ እንደ አንተ የከ​በረ ማን ነው? በም​ስ​ጋና የተ​ደ​ነ​ቅህ ነህ፤ ድን​ቅ​ንም የም​ታ​ደ​ርግ ነህ፤


እርሱ ይኖ​ራል፥ ከዓ​ረ​ብም ወር​ቅን ይሰ​ጡ​ታል፤ ሁል​ጊ​ዜም ስለ እርሱ ይጸ​ል​ያሉ፥ ዘወ​ት​ርም ይመ​ር​ቁ​ታል።


ምስ​ክ​ርህ እጅግ የታ​መነ ነው፤ አቤቱ፥ እስከ ረዥም ዘመን ድረስ ለቤ​ትህ ምስ​ጋና ይገ​ባል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዝማሬ በባ​ዕድ ምድር እን​ዴት እን​ዘ​ም​ራ​ለን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “አንተ አም​ላኬ ነህ፤ የል​መ​ና​ዬን ቃል፥ አቤቱ፥ አድ​ምጥ” አል​ሁት።


ታላ​ቁ​ንና የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን ነገር፥ እን​ዲ​ሁም የከ​በ​ረ​ው​ንና እጅግ መል​ካም የሆ​ነ​ውን የማ​ይ​ቈ​ጠ​ረ​ው​ንም ተአ​ም​ራት አደ​ረገ።


እርሱ የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን ታላቅ ነገ​ርና የማ​ይ​ቈ​ጠ​ረ​ውን የከ​በ​ረና ድንቅ ነገር ያደ​ር​ጋል።


እነሆ ይህ የመ​ን​ገዱ ክፍል ነው፤ የቀ​ሩ​ት​ንም ነገ​ሮ​ቹን እን​ሰ​ማ​ለን፤ በሚ​ያ​ደ​ር​ግ​በ​ትስ ጊዜ የነ​ጐ​ድ​ጓ​ዱን ኀይል የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው?”


እነ​ዚህ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ሁሉ፦ አንተ ውጣ፤ የሚ​ከ​ተ​ሉ​ህም ሕዝብ ሁሉ ከዚ​ያች ምድር ይውጡ እያሉ ወደ እኔ ይወ​ር​ዳሉ፤ ለእ​ኔም ይሰ​ግ​ዳሉ፤ ከዚ​ያም በኋላ እወ​ጣ​ለሁ።” ሙሴም በጽኑ ቍጣ ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ወጣ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements