Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 31:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ኀጢ​አ​ቴን ነገ​ርሁ፤ በደ​ሌ​ንም አል​ሸ​ሸ​ግ​ሁም፤ ስለ ኀጢ​አቴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሴን እከ​ስ​ሳ​ለሁ አልሁ፤ አን​ተም የል​ቤን ሽን​ገላ ተው​ልኝ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 መንፈሴን በእጅህ እሰጣለሁ፤ እግዚአብሔር የእውነት አምላክ ሆይ፤ አንተ ተቤዠኝ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አንተ መታመኛዬ ነህና ከደበቁብኝ ወጥመድ አውጣኝ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የእውነት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ነፍሴን ለአንተ እሰጣለሁና አድነኝ።

See the chapter Copy




መዝሙር 31:5
15 Cross References  

ያን​ጊ​ዜም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ፥ “አባት ሆይ፥ ነፍ​ሴን በአ​ንተ እጅ አደራ እሰ​ጣ​ለሁ” ብሎ ጮኸ፤ ይህ​ንም ብሎ ነፍ​ሱን ሰጠ።


እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስም፥ “ጌታዬ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ ነፍ​ሴን ተቀ​በል” እያለ ሲጸ​ልይ ይወ​ግ​ሩት ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሥ​ራው እው​ነ​ተኛ ነው፤ መን​ገ​ዱም ሁሉ የቀና ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መነ ነው፤ ክፋ​ትም የለ​በ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድ​ቅና ቸር ነው።


“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይ​ቻ​ልም፤ በእ​ርሱ ለተ​ማ​ፀን ተጠ​ብ​ቆ​ልን ባለ ተስ​ፋ​ች​ንም ማመ​ንን ላጸ​ናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


ስለዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ ተቀብዬአለሁ፤ ነገር ግን አላፍርበትም፤ ያመንሁትን አውቃለሁና፤ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል ተረድቼአለሁ።


እነሆ፥ መጣሁ፤ ሰውም አል​ነ​በ​ረም፤ ተጣ​ራሁ፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም፤ እጄ ለማ​ዳን ጠን​ካራ አይ​ደ​ለ​ምን? ወይስ ለማ​ዳን አል​ች​ል​ምን? እነሆ፥ በገ​ሠ​ጽሁ ጊዜ ባሕ​ርን አደ​ር​ቃ​ለሁ፤ ወን​ዞ​ች​ንም ምድረ በዳ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ውኃም በማ​ጣት ዐሣ​ዎ​ቻ​ቸው ይሞ​ታሉ፤ በጥ​ማ​ትም ያል​ቃሉ።


ከከፉ ነገር ሁሉ የአ​ዳ​ነኝ መል​አክ እርሱ እነ​ዚ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ይባ​ርክ፤ ስሜም፥ የአ​ባ​ቶች የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐ​ቅም ስም በእ​ነ​ርሱ ይጠራ፤ በም​ድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤”


ባናምነው፥ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።”


ከተ​ሸጠ በኋላ መቤ​ዠት ይች​ላል፤ ከወ​ን​ድ​ሞቹ አንዱ ይቤ​ዠው፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements