መዝሙር 28:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 የእግዚአብሔር ቃል ዋሊያዎችን ያጠነክራቸዋል፥ ዛፎችንም ይገልጣል፤ ሁሉም በመቅደሱ፦ ምስጋና ይላል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ሕዝብህን አድን፤ ርስትህንም ባርክ፤ እረኛ ሁናቸው፤ ለዘላለሙም ዐቅፈህ ያዛቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ሕዝብህን አድን፥ ርስትህንም ባርክ፥ ጠብቃቸው፥ ለዘለዓለሙም ከፍ ከፍ አድርጋቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 አምላክ ሆይ! ሕዝብህን አድን፤ የአንተ የሆኑትንም ባርክ፤ እረኛቸውም ሁን፤ ለዘለዓለምም ተንከባከባቸው። See the chapter |
ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ! አባቶቻችንን ከግብፅ ባወጣህ ጊዜ በባሪያህ በሙሴ እጅ እንደ ተናገርህ ርስት ይሆኑህ ዘንድ ከምድር አሕዛብ ሁሉ ለይተሃቸዋልና።” ያንጊዜም ሰሎሞን ሥራውን በጨረሰ ጊዜ ስለዚያ ቤት እንዲህ ሲል ተናገረ። “እግዚአብሔር በሰማይ ፀሐይን አሳየ፤ እግዚአብሔር በጨለማ ውስጥ እንደሚኖር ተናገረ፤ ቤቴን ሥራ፤ በመታደስም ለመኖር ለራስህ ጥሩ ቤትን ሥራ፤” ይህችስ በመሐልይ መጽሐፍ የተጻፈች አይደለምን?