Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 19:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አቤቱ፥ ንጉ​ሥን አድ​ነው፥ በም​ን​ጠ​ራ​ህም ቀን ስማን።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እግዚአብሔርን መፍራት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። የእግዚአብሔር ፍርድ የታመነ፣ ሁለንተናውም ጻድቅ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የጌታ ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል፥ የጌታ ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እግዚአብሔርን መፍራት ለዘለዓለም የሚኖር ንጽሕና ነው፤ የእግዚአብሔር ፍርዶች ሁሉ እያንዳንዳቸው እውነትና ጽድቅ ናቸው።

See the chapter Copy




መዝሙር 19:9
36 Cross References  

ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩ፤ ያደ​ረ​ገ​ላ​ች​ሁ​ንም ታላቅ ነገር አይ​ታ​ች​ኋ​ልና በፍ​ጹም ልባ​ችሁ በእ​ው​ነት አም​ል​ኩት፤


አቤቱ፥ በተ​ጨ​ነ​ቅሁ ጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ሰማ​ኸ​ኝም።


“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ! የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፤ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ፤” እያሉ የእግዚአብሔርን ባሪያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።


ኀጢ​አ​ተ​ኛም አይቶ ይቈ​ጣል፥ ጥር​ሱ​ንም ያፋ​ጫል፥ ይቀ​ል​ጣ​ልም፤ የኃ​ጥ​ኣ​ንም ምኞት ትጠ​ፋ​ለች።


እኔም ከአ​ንተ ጥቂት ራቅ ስል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ አን​ሥቶ ወደ​ማ​ላ​ው​ቀው ስፍራ ይወ​ስ​ድ​ሃል፤ እኔም ገብቼ ለአ​ክ​ዓብ ስና​ገር፥ ባያ​ገ​ኝህ ይገ​ድ​ለ​ኛል፤ እኔም ባሪ​ያህ ከት​ን​ሽ​ነቴ ጀምሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እፈራ ነበር።


ዛሬ በፊ​ታ​ችሁ እን​ደ​ማ​ኖ​ራት እን​ደ​ዚ​ህች ሕግ ሁሉ ጽድቅ የሆ​ነች ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ያለው ታላቅ ሕዝብ ማን ነው?


በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ዮሴፍ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ትድኑ ዘንድ ይህን አድ​ርጉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እፈ​ራ​ለ​ሁና።


ከመሰዊያውም “አዎን፤ ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ፍርዶችህ እውነትና ጽድቅ ናቸው፤” ብሎ ሲናገር ሰማሁ።


ይህም እን​ደ​ዚህ በሚ​ያ​ደ​ርጉ ሰዎች ላይ ቅጣት የሚ​ያ​መጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርዱ እው​ነት እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገድ የቀና ነው፤ በቅ​ዱስ ስሙም ታመን፤ ነፍ​ሳ​ችን የተ​መ​ኘ​ች​ው​ንም አገ​ኘን።


እኔ ሰላ​ማዊ ስሆን በተ​ና​ገ​ር​ኋ​ቸው ጊዜ በከ​ንቱ ይጠ​ሉ​ኛል።


ጽድ​ቅ​ህን እንደ ብር​ሃን፥ ፍር​ድ​ህ​ንም እንደ ቀትር ያመ​ጣ​ታል።


በክ​ፉ​ዎች ላይ አት​ቅና፥ ዐመ​ፃ​ንም በሚ​ያ​ደ​ርጉ ላይ አት​ቅና፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድ​ቁ​ንና ኃጥ​ኡን ይመ​ረ​ም​ራል፤ ዐመ​ፃን የወ​ደ​ዳት ግን ነፍ​ሱን ጠል​ቶ​አል።


ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው የነ​በ​ሩት አለ​ቆች ግን በሕ​ዝቡ ላይ አክ​ብ​ደው ነበር፤ ስለ እን​ጀ​ራ​ውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወ​ስዱ ነበር፤ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ በሕ​ዝቡ ላይ ይሰ​ለ​ጥኑ ነበር። እኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ፈራሁ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ግ​ሁም።


“በፊ​ታ​ቸው የም​ታ​ደ​ር​ገው ሥር​ዐት ይህ ነው።


እር​ሱም፥ “በብ​ላ​ቴ​ናው ላይ እጅ​ህን አት​ዘ​ርጋ፤ አን​ዳ​ችም አታ​ድ​ር​ግ​በት፤ ለም​ት​ው​ድ​ደው ልጅህ ከእኔ አል​ራ​ራ​ህ​ለ​ት​ምና አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈራ እን​ደ​ሆ​ንህ አሁን ዐው​ቄ​አ​ለሁ” አለው።


እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ርኅ​ራ​ኄ​ው​ንና ጭካ​ኔ​ውን አስ​ተ​ውል፤ የወ​ደ​ቁ​ትን ቀጣ​ቸው፤ አን​ተን ግን ይቅር እን​ዳ​ለህ ብት​ኖር ማረህ፤ ያለ​ዚያ ግን አን​ተም ትቈ​ረ​ጣ​ለህ።


እነ​ር​ሱም፥ “የመቶ አለቃ ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ጻድቅ ሰው ነው፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ወገ​ኖች ሁሉ የተ​መ​ሰ​ከ​ረ​ለት ነው፤ ቅዱስ መል​አክ ተገ​ልጦ አን​ተን ወደ ቤቱ እን​ዲ​ጠ​ራህ የም​ታ​ስ​ተ​ም​ረ​ው​ንም እን​ዲ​ሰማ አዝ​ዞ​ታል፤” አሉት።


እግዚአብሔርን የሚፈራ ዐመፃን ይጠላል፤ ጥልንና ትዕቢትን፥ ክፉ መንገድንም ይጠላል። የክፉ ሰዎችንም ጠማማ መንገድ ጠላሁ።


በስ​ውር ወይም በጨ​ለማ ስፍራ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁም፤ ለያ​ዕ​ቆብ ዘር፦ በከ​ንቱ ፈል​ጉኝ አላ​ል​ሁም፤ ጽድ​ቅን የም​ና​ገር፥ ቅን ነገ​ር​ንም የም​ና​ገር እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements