Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 18:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የአ​ን​ደ​በቴ ቃል ያማረ ይሁን፤ የልቤ ዐሳ​ብም ሁል​ጊዜ በፊቴ ነው አቤቱ ረድ​ኤቴ መድ​ኀ​ኒ​ቴም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ፍላጻውን ሰድዶ በተናቸው፤ ታላቅ መብረቆቹንም ልኮ አወካቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ጌታ ከሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ። በረዶና የእሳት ፍምም፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ፍላጻውን ከቀስቱ አስፈነጠረ፤ ጠላቶቹንም በተናቸው፤ በመብረቁም ብልጭታ አሳደዳቸው።

See the chapter Copy




መዝሙር 18:14
20 Cross References  

“ኀይ​ልህ ግሩም ነው” ይላሉ፥ ግር​ማ​ህ​ንም ይነ​ጋ​ገ​ራሉ፥ ብር​ታ​ት​ህ​ንም ያስ​ረ​ዳሉ።


ፍላጾችህ ከወጡበት ብርሃን የተነሣ፥ ከሚንቦገቦገውም ከጦርህ ፀዳል የተነሣ፥ ፀሐይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቆሙ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የድ​ም​ፁን ክብር ያሰ​ማል፤ የክ​ን​ዱ​ንም መፈ​ራት፥ በጽኑ ቍጣና በም​ት​በላ እሳት፥ በወ​ጀ​ብም፥ በዐ​ውሎ ነፋ​ስም፥ በበ​ረ​ዶም ድን​ጋይ ይገ​ል​ጣል።


ነገር ግን እር​ሱን መበ​ደ​ልን እን​ደ​ገና ደገሙ፥ ልዑ​ል​ንም በም​ድረ በዳ አስ​መ​ረ​ሩት።


እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍላጻ በሥ​ጋዬ ላይ ነው፤ መር​ዙም ደሜን ይመ​ጥ​ጣል። ለመ​ና​ገር ስጀ​ም​ርም ይወ​ጋ​ኛል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት አስ​ደ​ነ​ገ​ጣ​ቸው፤ በገ​ባ​ዖ​ንም ታላቅ መም​ታት መታ​ቸው።


ከተ​ወ​ጉት፥ ከተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ደም፥ ፍላ​ጻ​ዎ​ቼን በደም አሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ ከጠ​ላት አለ​ቆ​ችም ራስ ሰይፌ ሥጋን ትበ​ላ​ለች።


ለመ​ከራ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ፍላ​ጻ​ዎ​ች​ንም እጨ​ር​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ መርቶ አው​ጥ​ቶ​ታል፤ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ክብር አለው፤ ጠላ​ቶ​ቹን አሕ​ዛ​ብን ይበ​ላል፤ አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይሰ​ባ​ብ​ራል፤ በፍ​ላ​ጾ​ቹም ጠላ​ቱን ይወ​ጋ​ዋል።


ብዙ በሬ​ዎች ከበ​ቡኝ፥ የሰ​ቡ​ትም ፍሪ​ዳ​ዎች ያዙኝ፤


መብ​ረ​ቁን ትል​ከ​ዋ​ለ​ህን? እር​ሱስ ይሄ​ዳ​ልን? ደስ​ታ​ህስ ምን​ድን ነው ይል​ሃ​ልን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶ​ቹን ያደ​ክ​ማ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ ቅዱስ ነው፤ ጥበ​በኛ በጥ​በቡ አይ​መካ፤ ኀይ​ለ​ኛም በኀ​ይሉ አይ​መካ፤ ሀብ​ታ​ምም በሀ​ብቱ አይ​መካ፤ የሚ​መካ ግን በዚህ ይመካ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በማ​ወ​ቅና በማ​ስ​ተ​ዋል፤ በም​ድ​ርም መካ​ከል ፍር​ድ​ንና እው​ነ​ትን በማ​ድ​ረግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ሰማይ ወጣ፤ አን​ጐ​ደ​ጐ​ደም። ጻድቅ እርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈ​ር​ዳል፤ ለን​ጉ​ሦ​ቻ​ች​ንም ኀይ​ልን ይሰ​ጣል፤ የመ​ሲ​ሑ​ንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል።”


በስ​ተ​ኋ​ላው ድምፅ ይጮ​ኻል፤ በግ​ር​ማ​ውም ድምፅ ያን​ጐ​ደ​ጕ​ዳል፤ ድም​ፁም በተ​ሰማ ጊዜ ሰዎች እን​ዲ​ጠፉ አያ​ደ​ር​ግም።


ኀያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በድ​ምፁ ድንቅ አድ​ርጎ ያን​ጐ​ደ​ጕ​ዳል፤ ለእ​ን​ስ​ሳት በየ​ጊ​ዜው ምግ​ባ​ቸ​ውን ያዘ​ጋ​ጃል፥ የሚ​ተ​ኙ​በ​ት​ንም ጊዜ ያው​ቃሉ፤ በዚህ ሁሉ ልብህ አይ​ደ​ን​ግ​ጥ​ብህ፤ ሥጋ​ህም ልብ​ህም ከግ​ዘፉ አይ​ለ​ወ​ጥ​ብህ፤ እር​ሱም እኛ የማ​ና​ው​ቀ​ውን ታላቅ ነገር ያደ​ር​ጋል።


አቤቱ፥ ነፍ​ሴን ከሲ​ኦል አወ​ጣ​ሃት፥ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ር​ዱት ለይ​ተህ አዳ​ን​ኸኝ።


አቤቱ፥ በፈ​ቃ​ድህ ለሕ​ይ​ወቴ ኀይ​ልን ስጣት፤ ፊት​ህን መለ​ስህ፥ እኔም ደነ​ገ​ጥሁ።


ለነ​ፍ​ሳ​ቸው መብ​ልን ይፈ​ልጉ ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በል​ባ​ቸው ፈተ​ኑት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሠ​ራ​ዊቱ ፊት ድም​ፁን ይሰ​ጣል፤ ሰፈሩ እጅግ ብዙ ነውና፥ የቃ​ሉም ሥራ ጽኑዕ ነውና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀን ታላ​ቅና እጅግ የም​ታ​ስ​ፈራ ናትና፥ ፈጽማ ትገ​ለ​ጣ​ለች፥ መጠኗ ምን​ድን ነው? ማንስ ይች​ላ​ታል?


Follow us:

Advertisements


Advertisements