Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 147:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በረ​ዶ​ውን እንደ ባዘቶ ይሰ​ጣል፤ ጉሙን እንደ አመድ ይበ​ት​ነ​ዋል፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ጌታችን ታላቅ ነው፤ እጅግ ኀያልም ነው፤ ለጥበቡም ወሰን የለውም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጌታችን ታላቅ ነው፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ ለጥበቡም ቍጥር ስፍር የለውም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 አምላካችን ታላቅና ኀያል ነው፤ ለዕውቀቱም ወሰን የለውም።

See the chapter Copy




መዝሙር 147:5
17 Cross References  

አሁ​ንም አላ​ወ​ቅ​ህ​ምን? አል​ሰ​ማ​ህ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዘ​ለ​ዓ​ለም አም​ላክ፥ የም​ድ​ር​ንም ዳርቻ የፈ​ጠረ አም​ላክ ነው፤ አይ​ራ​ብም፤ አይ​ጠ​ማም፤ አይ​ደ​ክ​ምም፤ ማስ​ተ​ዋ​ሉም አይ​መ​ረ​መ​ርም።


መብ​ረ​ቆቹ ለዓ​ለም አበሩ፤ ምድር ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች ተና​ወ​ጠ​ችም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባለ​ጠ​ግ​ነት፥ ጥበ​ብና ዕው​ቀት እን​ዴት ጥልቅ ነው! ለመ​ን​ገ​ዱም ፍለጋ የለ​ውም፤ ፍር​ዱ​ንም የሚ​ያ​ው​ቀው የለም።


እግዚአብሔር ትዕግሥተኛ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ በደለኛውንም፦ ንጹሕ ነህ አይልም፣ እግዚአብሔር በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው፥ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው።


አሕ​ዛብ ሁላ​ችሁ፥ ይህን ስሙ፤ በዓ​ለም የም​ት​ኖ​ሩም ሁላ​ችሁ፥ አድ​ምጡ፤


ጠላ​ቶ​ቼም በላዬ ክፋ​ትን ይና​ገ​ራሉ፦ “መቼ ይሞ​ታል? ስሙስ መቼ ይሻ​ራል?” ይላሉ።


አቤቱ! እንደ አንተ ያለ የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ ስም​ህም በኀ​ይል ታላቅ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ፥ ምስ​ጋ​ና​ውም ብዙ ነውና፤ በአ​ማ​ል​ክ​ትም ሁሉ ላይ የተ​ፈራ ነው።


“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ! የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፤ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ፤” እያሉ የእግዚአብሔርን ባሪያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።


ማዳን በማ​ይ​ችሉ በአ​ለ​ቆ​ችና በሰው ልጆች አት​ታ​መኑ።


በደ​ስ​ታም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ፥ በሐ​ሤ​ትም ወደ ፊቱ ግቡ።


ሰማ​ያ​ትን በጥ​በቡ የሠራ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


“በጥ​በብ ብር​ቱና ኀያል የሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ የዋ​ሁን ሰው እን​ደ​ማ​ይ​ጥ​ለው ዕወቅ።


የአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ሆይ! በአ​ሕ​ዛብ ጥበ​በ​ኞች ሁሉ መካ​ከል፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለ​ሌለ፥ ለአ​ንተ ክብር ይገ​ባ​ልና አን​ተን የማ​ይ​ፈራ ማን ነው?


Follow us:

Advertisements


Advertisements