Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 144:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቃሉ ሁሉ የታ​መነ ነው፥ በሥ​ራ​ውም ሁሉ ጻድቅ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ፍ​ገ​መ​ገ​ሙ​ትን ሁሉ ይደ​ግ​ፋ​ቸ​ዋል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የወ​ደ​ቁ​ትን ያነ​ሣ​ቸ​ዋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከብቶቻችን ይክበዱ፤ አይጨንግፉ፤ አይጥፉም። እኛም በምርኮ አንወሰድ፤ በአደባባዮቻችንም ዋይታ አይሰማ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ላሞቻቸንም የሰቡ ይሁኑ፥ ቅጥራቸውም መፍረሻና መውጫ አይኑረው፥ በአደባባዮቻችንም ዋይታ አይኑር፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከብቶቻችን የሰቡ ይሁኑ፤ ሳይጨነግፉም በመርባት ይብዙ፤ በመንገዶቻችን የሐዘን ጩኸት ከቶ አይሰማ።

See the chapter Copy




መዝሙር 144:14
16 Cross References  

“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ግ​ርህ በታች ይወ​ድቁ ዘንድ የሚ​ቃ​ወ​ሙ​ህን ጠላ​ቶ​ች​ህን በእ​ጅህ ይጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ በአ​ንድ መን​ገድ ይመ​ጡ​ብ​ሃል፤ በሰ​ባ​ትም መን​ገድ ከፊ​ትህ ይሸ​ሻሉ።


ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ በሰ​ይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተ​ማም ብገባ፥ እነሆ በራብ የከሱ አሉ፤ ነቢ​ዩና ካህኑ ወደ​ማ​ያ​ው​ቋት ሀገር ሄደ​ዋ​ልና።”


ይሁዳ አለ​ቀ​ሰች፤ ደጆ​ች​ዋም ባዶ ሆኑ፤ በም​ድ​ርም ላይ ጨለሙ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ጩኸት ከፍ ከፍ ብሎ​አል።


ስለ ወይ​ኑም ጠጅ በአ​ደ​ባ​ባይ አል​ቅሱ፤ የም​ድር ደስታ ሁሉ ጨል​ሞ​አ​ልና፥ የም​ድ​ርም ሐሤት ፈል​ሶ​አ​ልና።


በሸ​ለ​ቆ​ውም ማዶና በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የነ​በሩ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች እንደ ሸሹ፥ ሳኦ​ልና ልጆ​ቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተ​ሞ​ቹን ለቅ​ቀው ሸሹ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም መጥ​ተው ተቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው።


ከም​ድ​ያ​ምም ፊት የተ​ነሣ እስ​ራ​ኤል እጅግ ተቸ​ገሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘር በዘሩ ጊዜ ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንና አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን ይዘ​ም​ቱ​ባ​ቸው ነበር፥ በም​ሥ​ራ​ቅም የሚ​ኖሩ ልጆች አብ​ረው ይዘ​ም​ቱ​ባ​ቸው ነበር፤


አዲ​ሶች አማ​ል​ክ​ትን መረጡ፤ በዚያ ጊዜ ሰልፍ በበ​ሮች ሆነ፤ በአ​ርባ ሺህ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ጦርና ጋሻ አል​ታ​ዩም።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ፊት የተ​መ​ታህ ያደ​ር​ግ​ሃል፤ በአ​ንድ መን​ገድ ትወ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በሰ​ባት መን​ገ​ድም ከእ​ነ​ርሱ ትሸ​ሻ​ለህ፤ በም​ድ​ርም መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ የተ​በ​ተ​ንህ ትሆ​ና​ለህ።


በም​ድ​ራ​ች​ሁም ላይ ሰላ​ምን እሰ​ጣ​ለሁ፤ ትተ​ኛ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ች​ሁም የለም፤ ክፉ​ዎ​ች​ንም አራ​ዊት ከም​ድ​ራ​ችሁ አጠ​ፋ​ለሁ።


ጕል​በ​ቱስ ብርቱ ስለ​ሆነ ትታ​መ​ነ​ዋ​ለ​ህን? ተግ​ባ​ር​ህ​ንስ ለእ​ርሱ ትተ​ዋ​ለ​ህን?


እኔም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሐሤ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በሕ​ዝ​ቤም ደስ ይለ​ኛል፤ ከዚ​ያም ወዲያ የል​ቅሶ ድም​ፅና የዋ​ይታ ድምፅ በው​ስ​ጥዋ አይ​ሰ​ማም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements