Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 118:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 የእ​ው​ነ​ት​ህን መን​ገድ እን​ዳ​ስ​ተ​ውል አድ​ር​ገኝ፥ ተአ​ም​ራ​ት​ህ​ንም አሰ​ላ​ስ​ላ​ለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ ብርሃኑንም በላያችን አበራ፤ እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ በመውጣት፣ ዝንጣፊ ይዛችሁ በዓሉን ከሚያከብሩት ጋራ ተቀላቀሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ጌታ አምላክ ነው፥ ለእኛም አበራልን፥ እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ፥ ቅርንጫፎች ይዘን፥ ለበዓሉ ዑደት እናድርግ

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ ብርሃንን ሰጥቶናል፤ ለምለም የሆኑ ቅርንጫፎችን ይዘን በዓል ለማክበር ወደ መሠዊያው እንሂድ።

See the chapter Copy




መዝሙር 118:27
17 Cross References  

ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ “የዓ​ለም ብር​ሃን እኔ ነኝ፤ የሚ​ከ​ተ​ለኝ የሕ​ይ​ወት ብር​ሃ​ንን ያገ​ኛል እንጂ በጨ​ለማ ውስጥ አይ​መ​ላ​ለ​ስም” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ብር​ሃ​ንሽ መጥ​ቶ​አ​ልና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃን በአ​ንቺ ላይ ወጥ​ቶ​አ​ልና አብሪ፤ አብሪ።


በጨ​ለማ የሄደ ሕዝብ ታላቅ ብር​ሃን አየ፤ በሞት ጥላና በጨ​ለማ ሀገ​ርም ለነ​በሩ ብር​ሃን ወጣ​ላ​ቸው።


እጅግ ጐሰ​ቈ​ልሁ፥ ጐበ​ጥ​ሁም፥ ሁል​ጊ​ዜም በት​ካዜ እመ​ላ​ለ​ሳ​ለሁ፤


ሕዝ​ቡም ሁሉ ያን ባዩ ጊዜ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደ​ፍ​ተው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ው​ነት እርሱ አም​ላክ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላክ ነው” አሉ።


ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፣ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።


ኤል​ያ​ስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፥ “እስከ መቼ በሁ​ለት አሳብ ታነ​ክ​ሳ​ላ​ችሁ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ፤ በዓ​ልም አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ” አለ። ሕዝ​ቡም አን​ዲት ቃል አል​መ​ለ​ሱ​ለ​ትም።


ቀን​ዶ​ቹ​ንም በአ​ራቱ ማዕ​ዘን አደ​ረ​ገ​በት፤ ቀን​ዶ​ቹም ከእ​ርሱ ጋር ሥረ-ወጥ ነበሩ፤ በና​ስም ለበ​ጠው።


በአ​ራ​ቱም ማዕ​ዘን ቀን​ዶ​ችን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ቀን​ዶቹ ሥረ-ወጥ ይሁኑ፤ በና​ስም ለብ​ጣ​ቸው።


በውኑ እን​ግ​ዲህ በስሙ እና​ምን ዘንድ የከ​ን​ፈ​ሮ​ቻ​ችን ፍሬ የሚ​ሆን የም​ስ​ጋና መሥ​ዋ​ዕ​ትን በየ​ጊ​ዜው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልና​ቀ​ርብ አይ​ገ​ባ​ን​ምን?


በነ​ጋ​ውም ዳዊት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረበ፤ አንድ ሺህ ወይ​ፈን፥ አንድ ሺህም አውራ በጎች፥ አንድ ሺህም የበግ ጠቦ​ቶች፥ የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንም፥ ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ብዙ መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ።


በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን ለእኔ እስኪያደርግ ድረስ ቍጣውን እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቅንም አያለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements