Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 118:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አቤቱ፥ አንተ ቡሩክ ነህ፤ ሥር​ዐ​ት​ህ​ንም አስ​ተ​ም​ረኝ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እንደ ንብ መንጋ ከበቡኝ፤ ነገር ግን እንደሚነድድ እሾኽ ከሰሙ፤ በርግጥም በእግዚአብሔር ስም አስወግዳቸዋለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ንብ ማርን እንዲከብብ ከበቡኝ፥ እሳትም በእሾህ ውስጥ እንደሚነድድ ነደዱ፥ በጌታ ስም አጠፋኋቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ዙሪያዬን እንደ ንብ ከበቡኝ፤ ነገር ግን እሾኽ በእሳት እንደሚቃጠል በፍጥነት ተቃጠሉ፤ በእግዚአብሔርም ኀይል ደመሰስኳቸው።

See the chapter Copy




መዝሙር 118:12
18 Cross References  

በዚ​ያም ተራ​ራማ አገር ይኖሩ የነ​በሩ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ወጥ​ተው ተጋ​ጠ​ሙ​አ​ችሁ፤ ንብ እን​ደ​ም​ት​ነ​ድ​ፍም ነደ​ፉ​አ​ችሁ፤ አሳ​ደ​ዱ​አ​ች​ሁም፤ ከሴ​ይር እስከ ሔር​ማም ድረስ መቱ​አ​ችሁ።


ዳዊ​ትም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን አለው፥ “አንተ ሰይ​ፍና ጦር፥ ጋሻም ይዘህ ትመ​ጣ​ብ​ኛ​ለህ፤ እኔ ግን ዛሬ በተ​ገ​ዳ​ደ​ር​ኸው በእ​ስ​ራ​ኤል ጭፍ​ሮች አም​ላክ ስም በሰ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ።


በማ​ዳ​ንህ ክብሩ ታላቅ ነው፤ ክብ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን ጨመ​ር​ህ​ለት።


ከድ​ስት በታች እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል እሾህ ድምፅ የሰ​ነፍ ሣቅ እን​ዲሁ ነው፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።


አቤቱ፥ በኀ​ይ​ልህ ንጉሥ ደስ ይለ​ዋል፤ በማ​ዳ​ን​ህም እጅግ ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋል።


ኀይ​ሌን ወደ አንተ አስ​ጠ​ጋ​ለሁ፥ አንተ አም​ላ​ኬና መጠ​ጊ​ያዬ ነህና።


አቤቱ፥ ጌታ​ችን፥ ስምህ በም​ድር ሁሉ እጅግ ተመ​ሰ​ገነ።


እነ​ዚህ ሁሉ ግን ሰው በእጁ እን​ደ​ማ​ይ​ዘው፥ እንደ ተጣለ እሾህ ናቸው።


እርስ በእርሳቸው እንደ ተመሰቃቀለ እሾህ ቢሆኑ፥ በመጠጣቸውም ቢሰክሩ እንደ ደረቅ ገለባ ፈጽመው ይጠፋሉ።


ስለ ጠቡ በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለው ዘንድ ቀር​ቃ​ሃና ሣርን ማን በሰ​ጠኝ! አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ዛሬ አደ​ረገ፤ እነ​ርሱ ተቃ​ጥ​ለ​ዋ​ልና።


አሕ​ዛ​ብም በእ​ርሻ ውስጥ ተቈ​ርጦ እንደ ተጣ​ለና በእ​ሳት እንደ ተቃ​ጠለ እሾህ የተ​ቃ​ጠሉ ይሆ​ናሉ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements