Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 102:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አባት ለል​ጆቹ እን​ደ​ሚ​ራራ፥ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ፈ​ሩት ይራ​ራ​ላ​ቸ​ዋል፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ትነሣለህ፤ ጽዮንንም በርኅራኄ ዐይን ታያለህ፤ ለርሷ በጎነትህን የምታሳይበት ዘመን ነውና፤ የተወሰነውም ጊዜ ደርሷል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ለዘለዓለም ትኖራለህ፥ መታሰቢያህም ለልጅ ልጅ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ለጽዮን ምሕረት የምታደርግላት ጊዜ ስለ ተቃረበና ጊዜውም አሁን ስለ ሆነ አንተ ትነሣለህ፤ ለእርስዋም ትራራለህ።

See the chapter Copy




መዝሙር 102:13
26 Cross References  

ነገር ግን ቀጠ​ሮው በደ​ረሰ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን ላከ፤ ከሴ​ትም ተወ​ለደ፤ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ፈጸመ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ብር​ሃ​ንሽ መጥ​ቶ​አ​ልና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃን በአ​ንቺ ላይ ወጥ​ቶ​አ​ልና አብሪ፤ አብሪ።


ካህ​ናት ሆይ፥ ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ልቧ የሚ​ገባ ነገ​ርን ተና​ገሩ፤ ውር​ደቷ እንደ ተፈ​ጸመ፥ ኀጢ​አ​ቷም እንደ ተሰ​ረየ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ስለ ኀጢ​አቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀ​በ​ለች አጽ​ና​ኑ​አት።


እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ! በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።


እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አብ በገዛ ሥል​ጣኑ የወ​ሰ​ነ​ውን ቀኑ​ንና ዘመ​ኑን ልታ​ውቁ አል​ተ​ፈ​ቀ​ደ​ላ​ች​ሁም።


አቤቱ፥ በመ​ዓ​ትህ ተነሥ፤ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ ተነ​ሣ​ባ​ቸው፤ አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ ባዘ​ዝ​ኸው ሥር​ዐት ተነሥ።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ምር​ኮ​አ​ቸ​ውን በመ​ለ​ስሁ ጊዜ በይ​ሁዳ ሀገር በከ​ተ​ሞ​ችዋ፦ የጽ​ድቅ ማደ​ሪያ ሆይ! የቅ​ድ​ስና ተራራ ሆይ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ር​ክህ የሚል ነገ​ርን እንደ ገና ይና​ገ​ራሉ።


የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት ምን ይመ​ል​ሳሉ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን መሠ​ረ​ታት፤ ትሑ​ታን የሆ​ኑ​ት​ንም ሕዝብ አዳ​ና​ቸው።


በሀ​ገ​ሩም በሰ​ላም ኖረ፥ ማደ​ሪ​ያ​ውም በጽ​ዮን ነው፤


ዳግ​መ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን አለው፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ትላ​ለህ፦ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ እና​ንተ ላከኝ፤ ይህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ስሜ ነው፤ እስከ ልጅ ልጅ ድረ​ስም መታ​ሰ​ቢ​ያዬ ይህ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “አንተ መጠ​ጊ​ያ​ዬና አም​ባዬ ነህ፤ አም​ላ​ኬና ረዳቴ ነው፥ በእ​ር​ሱም እታ​መ​ና​ለሁ” ይለ​ዋል።


የኤ​ር​ት​ራን ባሕር ፈጽሞ የከ​ፈለ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements