Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 8:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 የሚሰማኝ ሰው ብፁዕ ነው፥ መንገዴን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው፥ ዕለት ዕለት በቤቴ መግቢያ የሚተጋ፥ የደጄንም መድረክ የሚጠብቅ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ብፁዕ ነው፤ በየዕለቱ ደጃፌ ላይ የሚጠብቅ፣ በበራፌ ላይ የሚጠባበቅ፣ የሚያዳምጠኝ ሰው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 የሚሰማኝ ሰው ምስጉን ነው ዕለት ዕለት በቤቴ መግቢያ የሚተጋ፥ የደጄንም መድረክ የሚጠብቅ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 እኔን የሚያዳምጥ፥ በየቀኑ በደጃፌ ላይ ተግቶ የሚገኝ፥ በቤቴ መግቢያ አጠገብ የሚጠባበቀኝ ሰው የተባረከ ነው።

See the chapter Copy




ምሳሌ 8:34
17 Cross References  

እር​ሱም፥ “ብፁ​ዓ​ንስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰም​ተው የሚ​ጠ​ብቁ ናቸው” አላት።


“ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል።


ጥበብን የሚያገኝ፥ ማስተዋልንም የሚያውቅ መዋቲ ሰው ብፁዕ ነው።


በሐ​ዋ​ር​ያት ትም​ህ​ር​ትና በአ​ን​ድ​ነት ማዕ​ድን በመ​ባ​ረክ፥ በጸ​ሎ​ትም ጸን​ተው ይኖሩ ነበር።


ማር​ያም የም​ት​ባል እኅ​ትም ነበ​ረ​ቻት፤ እር​ስ​ዋም ከጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ እግር አጠ​ገብ ተቀ​ምጣ ትም​ህ​ር​ቱን ትሰማ ነበር።


እርስዋ ለሚመረኰዛት ሁሉ የሕይወት ዛፍ ናት፥ የሚታመኑባትም በእግዚአብሔር እንደ ጸና ሰው ናቸው።


ይቅ​ር​ታና ቅን​ነት ተገ​ናኙ፤ ጽድ​ቅና ሰላም ተስ​ማሙ።


እንደ ሥራ​ቸ​ውና እንደ ዐሳ​ባ​ቸው ክፋት ስጣ​ቸው፤ እንደ እጃ​ቸ​ውም ሥራ ክፈ​ላ​ቸው፤ ፍዳ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ መልስ።


ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድ​ቃን ነበሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐ​ትና በት​እ​ዛ​ዙም ሁሉ ያለ ነውር የሚ​ሄዱ ነበሩ።


በግንብ ድምድማት ትሰብካለች፥ በኀያላን በሮች ታገለግላለች። በከተማ በሮች በድፍረት እንዲህ ትላለች፦


ከደ​ሙም ወስ​ደው በሚ​በ​ሉ​በት ቤት ሁለ​ቱን መቃ​ንና ጉበ​ኑን ይቅ​ቡት።


ሚስ​ቶ​ችህ የተ​መ​ሰ​ገኑ ናቸው፤ በፊ​ትህ ሁል​ጊዜ የሚ​ቆሙ፥ ጥበ​ብ​ህን የሚ​ሰሙ እነ​ዚህ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም ምስ​ጉ​ኖች ናቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements