Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 6:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 የአመንዝራ ሴት ክብር እስከ አንዲት እንጀራ ነው፤ አመንዝራ ሴትም የተከበሩ ወንዶች ነፍስን ታጠምዳለች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ጋለሞታ ሴት ቍራሽ እንጀራ ታሳጣሃለችና፤ አመንዝራዪቱም በሕይወትህ በራሱ ላይ ትሸምቃለች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 የሴተኛ ዐዳሪዋ ዋጋ እስከ አንዲት እንጀራ ነው፥ አመንዝራም ሴት የሰውን ሕይወት ታጠምዳለች።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 አንድ ወንድ ሴትኛ ዐዳሪዋን በአንድ እንጀራ ዋጋ ሊያገኛት ይችላል፤ ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ማመንዘር ግን የሕይወት ዋጋ ያስከፍላል።

See the chapter Copy




ምሳሌ 6:26
14 Cross References  

ከአ​መ​ን​ዝ​ሮች ጋር ገን​ዘ​ብ​ህን ሁሉ የጨ​ረሰ ይህ ልጅህ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ግን የሰ​ባ​ውን ፍሪዳ አረ​ድ​ህ​ለት።’


ከቤ​ት​ህም የቀ​ረው ሁሉ ይመ​ጣል፤ ከካ​ህ​ና​ትም ወደ አን​ዲቱ ዕጣ፥ እን​ጀራ ወደ​ም​በ​ላ​በት እባ​ክህ ላከኝ ብሎ ለአ​ንድ ብር መሐ​ልቅ ለቍ​ራሽ እን​ጀራ በፊቱ ይሰ​ግ​ዳል።”


እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ነፍ​ስን ለማ​ጥ​መድ ለእጅ ድጋፍ ሁሉ መከዳ ለሚ​ሰፉ፥ ለሰ​ውም ሁሉ ራስ እንደ እየ​ቁ​መቱ ሽፋን ለሚ​ሠሩ ሴቶች ወዮ​ላ​ቸው! የሕ​ዝ​ቤን ነፍስ ታጠ​ም​ዳ​ላ​ችሁ፤ በውኑ እና​ንተ ነፍ​ሳ​ች​ሁን ታድ​ና​ላ​ችሁ?


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከንቱ ነገ​ርን ስለ ተና​ገ​ራ​ችሁ፥ ሐሰ​ተኛ ራእ​ይ​ንም ስለ አያ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ እነሆ እኔ በእ​ና​ንተ ላይ ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ወደ ወጥመድ እንደሚቸኩል ዎፍ፥ ሳያውቅም ለነፍሱ ጥፋት እንደሚሮጥ።


ባዕዳን በሀብትህ እንዳይጠግቡ፥ የድካምህም ፍሬ በባዕድ ሰው ቤት እንዳይገባ።


የቤ​ቷን ሰዎች ወደ እር​ስዋ ጠርታ እን​ዲህ ብላ ነገ​ረ​ቻ​ቸው፥ “እዩ፤ ይህ ዕብ​ራዊ ባርያ በእኛ እን​ዲ​ሣ​ለቅ አመ​ጣ​ብን፤ እርሱ ወደ እኔ ገብቶ ከእኔ ጋር ተኚ አለኝ፤ እኔም ድም​ፄን ከፍ አድ​ርጌ ጮኽሁ፤


ሕይወትህን ለሌላ እንዳትሰጥ፥ ንብረትህንም ምሕረት ለሌላቸው፤


በጕያው እሳትን የሚታቀፍ፥ ልብሶቹስ የማይቃጠሉ ማን ነው?


ወደ እርሷ የሄደ ፈጥኖ ይጠፋል፥ ጠማማ ሰውም ሁሉ ያልቃል።


ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ የጌ​ታው ሚስት በዮ​ሴፍ ላይ ዐይ​ን​ዋን ጣለ​ች​በት፤ “ከእ​ኔም ጋር ተኛ” አለ​ችው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements