Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከአመንዝራ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና፥ ወደ አመንዝራ ሴት አትመልከት፥ ለጊዜው ጕሮሮህን ያጣፍጣል፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የአመንዝራ ሴት ከንፈር ማር ያንጠባጥባልና፤ አንደበቷም ከቅቤ ይለሰልሳል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከጋለሞታ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና፥ አፍዋም ከዘይት የለዘበ ነውና፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የአመንዝራ ሴት ከንፈር የማር ወለላ የሚያንጠባጥብ ይመስላል፤ ንግግርዋም ከዘይት ይልቅ የለዘበ ነው።

See the chapter Copy




ምሳሌ 5:3
10 Cross References  

ከቀናች መንገድ እንዳያርቁህ፥ እውነትንም ከማወቅ የተለየህ እንዳያደርጉህ፤ ልጄ ሆይ፥ በሕፃንነትህ ትምህርትን የምታስተው፥ ክፉ ምክር አታግኝህ፤


በብዙ ጨዋታዋ እንዲስት ታደርገዋለች፤ በከንፈርዋ ወጥመድም ትጐትተዋለች።


ከባዕድና ከክፉ ሴት ዋዛ ነገርንም ከምታመጣብህ ትጠብቅህ ዘንድ።


ከጐልማሳ ሚስት፥ ከሌላዪቱም አንደበት ነገረ ሠሪነት ትጠብቅህ ዘንድ ትእዛዜን ጠብቅ፥


ልጄ ሆይ፥ ከሌላዪቱ ሴት ጋር አትኑር፤ የአንተ ወዳልሆነችውም እጅህን አትዘርጋ።


የዐመፀኛ አፍ ጥልቅ ጕድጓድ ነው፤ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተጠላ በእርሱ ውስጥ ይወድቃል። በሰው ፊት ክፉዎች መንገዶች አሉ፥ ከእነርሱም ይርቅ ዘንድ አይወድድም። ከክፉና ከጠማማ መንገድም መራቅ አግባብ ነው።


ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ከከ​ን​ፈ​ሮ​ችሽ የማር ወለላ ይን​ጠ​ባ​ጠ​ባል፤ ከም​ላ​ስ​ሽም በታች ማርና ወተት አለ፥ የል​ብ​ስ​ሽም መዓዛ እንደ ዕጣን መዓዛ ነው።


እኔም ከሞት ይልቅ የመ​ረ​ረች ነገ​ርን አገ​ኘሁ፤ እር​ስ​ዋም ልብዋ ወጥ​መ​ድና መረብ የሆነ፥ በእ​ጆ​ች​ዋም ማሰ​ሪያ ያላት ሴት ናት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ደግ የሆነ ከእ​ርሷ ያመ​ል​ጣል። ኀጢ​አ​ተኛ ግን ይጠ​መ​ድ​ባ​ታል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements