Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 5:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ልጄ ሆይ፥ ከሌላዪቱ ሴት ጋር አትኑር፤ የአንተ ወዳልሆነችውም እጅህን አትዘርጋ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ልጄ ሆይ፤ በአመንዝራ ሴት ፍቅር ለምን ትሰክራለህ? የሌላዪቱንስ ሴት ብብት ስለ ምን ታቅፋለህ?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ልጄ ሆይ፥ ስለምን ጋለሞታ ሴት ትወድዳለህ? የሌላይቱንስ ብብት ለምን ታቅፋለህ?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ልጄ ሆይ! በአመንዝራይቱ ሴት ለምን ትማረካለህ? ለምንስ ከሌላው ሰው ሚስት ጋር ትባልጋለህ?

See the chapter Copy




ምሳሌ 5:20
10 Cross References  

ከባዕድና ከክፉ ሴት ዋዛ ነገርንም ከምታመጣብህ ትጠብቅህ ዘንድ።


ከጐልማሳ ሚስት፥ ከሌላዪቱም አንደበት ነገረ ሠሪነት ትጠብቅህ ዘንድ ትእዛዜን ጠብቅ፥


ዐይኖችህ ጋለሞታዎችን ያያሉ፥ ያንጊዜም አፍህ ጠማማ ነገርን ይናገራል።


የዐመፀኛ አፍ ጥልቅ ጕድጓድ ነው፤ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተጠላ በእርሱ ውስጥ ይወድቃል። በሰው ፊት ክፉዎች መንገዶች አሉ፥ ከእነርሱም ይርቅ ዘንድ አይወድድም። ከክፉና ከጠማማ መንገድም መራቅ አግባብ ነው።


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ሴቶ​ችን ይወድ ነበር፥ ከባ​ዕ​ዳን ሕዝ​ብም የፈ​ር​ዖ​ንን ልጅ፥ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ት​ንና አሞ​ና​ው​ያ​ትን፥ ሶር​ያ​ው​ያ​ት​ንና ሲዶ​ና​ው​ያ​ትን፥ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ት​ንና አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ት​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ት​ንም፦ ሚስ​ቶ​ችን አገባ።


ከአመንዝራ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና፥ ወደ አመንዝራ ሴት አትመልከት፥ ለጊዜው ጕሮሮህን ያጣፍጣል፥


እናንተም፦ ስለ ምንድር ነው? ብላችኋል። ሚስትህ ባልንጀራህና የቃል ኪዳንህ ሚስት ሆና ሳለች እርስዋን አታልለሃታልና እግዚአብሔር በአንተና በልጅነት ሚስትህ መካከል ምስክር ስለ ሆነ ነው።


መፋታትን እጠላለሁ፥ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፥ ልብሱንም በግፍ ሥራ የሚከድነውን ሰው እጠላለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ስለዚህ እንዳታታልሉ መንፈሳችሁን ጠብቁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements