Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 4:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የኀጢአት መብልን ይበላሉ፥ በግፍ የወይን ጠጅም ይሰክራሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የክፋት እንጀራ ይበላሉ፤ የዐመፅ ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የክፋትን እንጀራ ይበላሉና፥ የግፍንም ወይን ጠጅ ይጠጣሉና።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ዐመፅና ግፍ ለእነርሱ እንደ መብልና እንደ መጠጥ ናቸው።

See the chapter Copy




ምሳሌ 4:17
17 Cross References  

ባለ ጠጎችዋን ግፍ ሞልቶባቸዋል፥ በእርስዋም የሚኖሩ በሐሰት ተናግረዋል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ተንኰለኛ ነው።


ኀጢ​አ​ተኛ በፊቱ የተ​ናቀ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈ​ሩ​ትን የሚ​ያ​ከ​ብር፥ ለባ​ል​ን​ጀ​ራው ምሎ የማ​ይ​ከዳ።


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።


በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፣ ፈራጆችዋም እስከ ነገ ድረስ ምንም እንደማያስቀሩ እንደ ማታ ተኵላዎች ናቸው።


እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት እንዲህ ይላል፥ በጥርሳቸው ሲነክሱ በሰላም ይሰብካሉ፥ በአፋቸው ግን አንዳች በማይሰጥ ሰው ላይ ሰልፍን ያስቡበታል።


የሐሰት እንጀራ ለሰው የጣፈጠ ነው፤ ከዚህ በኋላ ግን አፉ ጭንጫ ይሞላል።


“የተሸሸገ እንጀራን አሰማምረህ ዳስስ። ጣፋጭ የስርቆት ውኃንም ጠጣ፥”


ደግ ሰው ከጽድቅ ፍሬ መልካምን ይበላል፤ የዐመፀኞች ነፍሳት ግን በጨርቋነታቸው ይጠፋሉ።


እጆቻቸውን ለክፋት ያነሣሉ፥ አለቃውና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፥ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጕናሉ።


በደ​ልን እንደ ረዥም ገመድ ለሚ​ስቡ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም እንደ በሬ ቀን​በር ለሚ​ያ​ስሩ ወዮ​ላ​ቸው!


ክፉ​ውን መል​ካም መል​ካ​ሙ​ንም ክፉ ለሚሉ፥ ጨለ​ማ​ውን ብር​ሃን ብር​ሃ​ኑ​ንም ጨለማ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ፥ ጣፋ​ጩን መራራ መራ​ራ​ው​ንም ጣፋጭ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ወዮ​ላ​ቸው!


ወን​ድ​ምም ሁሉ ያሰ​ና​ክ​ላ​ልና፥ ባል​ን​ጀ​ራም ሁሉ በጠ​ማ​ማ​ነት ይሄ​ዳ​ልና እና​ንተ ሁሉ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ፤ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም አት​ታ​መኑ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements