Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 24:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ጥበብና መልካም ዕውቀት በብልሆች በር ትገኛለች፤ ብልሆች ከእግዚአብሔር ቃል አይርቁም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ጥበብ ለቂል በጣም ሩቅ ናት፤ በከተማዪቱ በር ሸንጎ ላይም መናገር አይችልም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጥበብ ለሞኝ ሰው ከፍ ብላ የራቀች ናት፥ በከተማውም በር ላይ መናገር አይችልም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ማስተዋል የጐደለው ሰው ጥበብን መገንዘብ አይችልም፤ ሰዎች ቁም ነገር ባለው ጉዳይ ላይ ሲወያዩ እርሱ የሚያቀርበው አስተያየት የለም።

See the chapter Copy




ምሳሌ 24:7
21 Cross References  

በክፉዎች ዘንድ ጥበብን ትፈልጋለህ፥ አታገኛትምም፤ ዕውቀት ግን በብልሆች ዘንድ በቀላሉ ይገኛል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድ​ቁ​ንና ኃጥ​ኡን ይመ​ረ​ም​ራል፤ ዐመ​ፃን የወ​ደ​ዳት ግን ነፍ​ሱን ጠል​ቶ​አል።


ለሥ​ጋዊ ሰው ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነገር ሞኝ​ነት ይመ​ስ​ለ​ዋ​ልና፥ አይ​ቀ​በ​ለ​ውም፤ በመ​ን​ፈ​ስም የሚ​መ​ረ​መር ስለ​ሆነ ሊያ​ውቅ አይ​ች​ልም።


ክፉ​ውን ጥሉ፤ መል​ካ​ሙ​ንም ውደዱ፤ በበ​ሩም አደ​ባ​ባይ ፍር​ድን አጽኑ፤ ምና​ል​ባት ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዮ​ሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆ​ናል።


ጻድ​ቁን የም​ታ​ስ​ጨ​ንቁ፥ ጉቦ​ንም የም​ት​ቀ​በሉ፥ በበ​ሩም የች​ግ​ረ​ኛ​ውን ፍርድ የም​ታ​ጣ​ምሙ እና​ንተ ሆይ! በደ​ላ​ችሁ እን​ዴት እንደ በዛ፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም እን​ዴት እንደ ጸና እኔ ዐው​ቃ​ለ​ሁና።


በበሩ የሚ​ገ​ሥ​ጸ​ውን ጠሉ፤ እው​ነ​ት​ንም የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ተጸ​የፉ።


እነ​ዚ​ህም ሰውን በነ​ገር በደ​ለኛ የሚ​ያ​ደ​ርጉ፥ በበ​ርም ለሚ​ገ​ሥ​ጸው አሽ​ክላ የሚ​ያ​ኖሩ፥ ጻድ​ቁ​ንም በከ​ንቱ ነገር የሚ​ያ​ስቱ ናቸው።


ድሃን በግድ አትበለው፥ ድሃ ነውና ችግረኛውንም በበር አትግፋው፤


የብልህ ሰው ፊት ዐዋቂ ነው፤ የአላዋቂ ሰው ዐይኖች ግን በምድር ዳርቻ ናቸው።


ሸሽቶ ከሲኦል ያመልጥ ዘንድ፥ የአስተዋይ ሰው ልብ የሕይወት መንገድ ነው።


ብዙ ረዳት እን​ዳ​ለኝ ተማ​ምኜ በድ​ሃ​አ​ደጉ ላይ እጄን አን​ሥቼ እንደ ሆነ፥


ልጆ​ቻ​ቸው ከደ​ኅ​ን​ነት ርቀ​ዋል፥ በበ​ርም ውስጥ ይቀ​ጠ​ቅ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ መከ​ራም ያጸ​ኑ​ባ​ቸ​ዋል፥ የሚ​ታ​ደ​ጋ​ቸ​ውም የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጽ​ዮን ይባ​ር​ክህ፤ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መል​ካ​ም​ነት ታያ​ለህ።


የታመነች ከንፈር ለሰነፍ፥ የሐሰት ከንፈርም ለጻድቅ አትስማማውም።


ለአላዋቂ ሰው ገንዘብ ለምንድን ነው? አላዋቂ ሰው ጥበብን ገንዘብ ማድረግ አይችልምና፥ ቤቱን የሚያስረዝም ሰው ለራሱ ጥፋትን ይሻል፤ ለመማርም የሚጨንቀው ወደ ክፉ ይወድቃል።


ሰነፍ ግን ስን​ፍ​ናን ይና​ገ​ራል፤ ልቡም ዐመ​ፅን ያደ​ርግ ዘንድ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ስሕ​ተ​ትን ይና​ገር ዘንድ፥ የተ​ራ​በ​ች​ው​ንም ሰው​ነት ይበ​ትን ዘንድ፥ የተ​ጠ​ማ​ች​ንም ነፍስ ባዶ ያደ​ርግ ዘንድ ከን​ቱን ያስ​ባል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements