Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 23:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በሰነፍ ጆሮ አንዳች አትናገር፥ የነገርህን ጥበብ እንዳይንቅብህ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከሞኝ ጋራ አትነጋገር፤ የቃልህን ጥበብ ያንኳስሳልና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በሞኝ ጆሮ ምንም አትናገር፥ በቃልህ ጥበብ ያፌዛልና።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ጥበብ የሞላበት ምክርህን ስለሚንቅብህ ለሞኝ ሰው ቁም ነገር አታጫውተው፤

See the chapter Copy




ምሳሌ 23:9
17 Cross References  

በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።


የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ዕውቀት ለሚያደርጋት ሁሉ መልካም ናት። እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፥ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።


ከእ​ነ​ር​ሱም ብዙ​ዎች፥ “ጋኔን ይዞት ያብ​ዳል፤ ለም​ንስ ታዳ​ም​ጡ​ታ​ላ​ችሁ?” አሉ።


እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ አን​ዳ​ችም አል​መ​ለ​ሱ​ለ​ትም፤ ንጉሡ እን​ዳ​ይ​መ​ል​ሱ​ለት አዝዞ ነበ​ርና።


የሙ​ታ​ን​ንም ትን​ሣኤ በሰሙ ጊዜ እኩ​ሌ​ቶቹ አፌ​ዙ​በት፤ ሌሎ​ችም፥ “ስለ​ዚህ ነገር በሌላ ቀን እና​ዳ​ም​ጥ​ሃ​ለን” አሉት።


የኤ​ፌ​ቆ​ሮ​ስን ትም​ህ​ርት ከተ​ማሩ ፈላ​ስ​ፋ​ዎች መካ​ከ​ልና ረዋ​ቅ​ያ​ው​ያን ከሚ​ባ​ሉት ወገን የሆኑ ሌሎች ፈላ​ስ​ፎ​ችም የተ​ከ​ራ​ከ​ሩት ነበሩ፤ እኩ​ሌ​ቶ​ችም፥ “ይህ ለፍ​ላፊ ምን ሊና​ገር ይፈ​ል​ጋል?” ይሉ ነበር፤ ሌሎ​ችም፥ “ስለ ኢየ​ሱስ ከሙ​ታን ስለ መነ​ሣ​ቱም ሰብ​ኮ​ላ​ቸ​ዋ​ልና የአ​ዲስ አም​ላክ ትም​ህ​ር​ትን ያስ​ተ​ም​ራል” አሉ።


አይ​ሁ​ድም እን​ዲህ አሉት፥ “አሁን ጋኔን እን​ዳ​ለ​ብህ ዐወ​ቅን፤ አብ​ር​ሃም ስንኳ ሞቶ​አል፤ ነቢ​ያ​ትም ሞተ​ዋል፤ አንተ ግን ቃሌን የሚ​ጠ​ብቅ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሞትን አይ​ቀ​ም​ስም ትላ​ለህ።


ገን​ዘ​ብን የሚ​ወዱ ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ይህን ሁሉ ነገር ሰም​ተው ተጠ​ቃ​ቀ​ሱ​በት።


ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ይህን ሲና​ገር ሰም​ተው፥ “እኛ ደግሞ ዕዉ​ሮች ነን?” አሉት።


በሰነፍ ሰው ፊት ሁሉ ጠማማ ነው፥ የብልሆች ከንፈር ግን የዕውቀት ጋሻ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements