Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 22:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የዐመፀኛ አፍ ጥልቅ ጕድጓድ ነው፤ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተጠላ በእርሱ ውስጥ ይወድቃል። በሰው ፊት ክፉዎች መንገዶች አሉ፥ ከእነርሱም ይርቅ ዘንድ አይወድድም። ከክፉና ከጠማማ መንገድም መራቅ አግባብ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የአመንዝራ ሴት አፍ ጥልቅ ጕድጓድ ነው፤ እግዚአብሔር የተቈጣውም ይገባበታል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የአመንዝራ ሴት አፍ የጠለቀ ጉድጓድ ነው፥ ጌታ የተቈጣው በውስጡ ይወድቃል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የአመንዝራ ሴት አፍ እንደ ጥልቅ ጒድጓድ ነው። እግዚአብሔር የጠላቸው ሰዎችም ተይዘው ይወድቁበታል።

See the chapter Copy




ምሳሌ 22:14
10 Cross References  

እኔም ከሞት ይልቅ የመ​ረ​ረች ነገ​ርን አገ​ኘሁ፤ እር​ስ​ዋም ልብዋ ወጥ​መ​ድና መረብ የሆነ፥ በእ​ጆ​ች​ዋም ማሰ​ሪያ ያላት ሴት ናት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ደግ የሆነ ከእ​ርሷ ያመ​ል​ጣል። ኀጢ​አ​ተኛ ግን ይጠ​መ​ድ​ባ​ታል።


አመንዝራ ሴት የተነደለች ማድጋ ናት፥ ሌላዪቱም ሴት የጠበበች ጕድጓድ ናት።


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሰሎ​ሞን በዚህ ነገር ኀጢ​አት አድ​ርጎ የለ​ምን? በብዙ አሕ​ዛ​ብም መካ​ከል እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም፤ በአ​ም​ላ​ኩም ዘንድ የተ​ወ​ደደ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ አን​ግ​ሦት ነበር፤ እር​ሱ​ንም እንኳ እን​ግ​ዶች ሴቶች አሳ​ቱት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አይቶ ቀና፤ በወ​ን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችም ፈጽሞ ተቈጣ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements