Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 21:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከጽድቅ መንገድ የሚሳሳት ሰው፥ በረዐይት ጉባኤ ያርፋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የማስተዋልን መንገድ የሚስት ሰው፣ በሙታን ጉባኤ ያርፋል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከማስተዋል መንገድ የሚሳሳት ሰው በሙታን ጉባኤ ያርፋል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከማስተዋል መንገድ የሚርቀውን ሰው ሞት ይጠብቀዋል።

See the chapter Copy




ምሳሌ 21:16
20 Cross References  

ጻድቅ በእ​ም​ነት ይድ​ናል፤ ወደ​ኋላ ቢመ​ለስ ግን ልቡ​ናዬ በእ​ርሱ ደስ አይ​ላ​ትም።”


በል​ቅሶ የሚ​ዘሩ በደ​ስታ ይሰ​በ​ስ​ባሉ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ስ​ጋ​ናን መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ፥ ለል​ዑ​ልም ጸሎ​ት​ህን ስጥ፤


እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውሃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥


ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።


እና​ን​ተም በኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ምው​ታን ሆና​ችሁ ነበር።


እግዚአብሔርንም ከመከተል የተመለሱትን፥ እግዚአብሔርንም ያልፈለጉትንና ያልጠየቁትን አጠፋለሁ።


ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ ከአላዋቂዎች ጋር የሚሄድ ግን አላዋቂ ይሆናል።


ነገር ግን እርሱ ከኀያላን ወገን በእርሷ ዘንድ የሚጠፉ እንዳሉ፥ የሲኦል ወጥመድም በቤቷ እንደሚገኝ አያውቅም። ነገር ግን ፈጥነህ ሂድ፥ በቦታዋም አትዘግይ፥ የባዕድን ውኃ እንደምትሻገር በዐይንህ ወደ እርሷ መመልከትን አታዘውትር። ከባዕድ ውኃ ራቅ፥ ብዙ ዘመን ትኖር ዘንድ ከባዕድ ምንጭ ውኃ አትጠጣ። የሕይወትህም ዓመታት ይጨመሩልሃል።


እነርሱ በጨለማ መንገድ ይሄዱ ዘንድ የቀናውን ጎዳና ለሚተዉ፥


ጻድቅ ልጅ ለሕይወት ይወለዳል፤ የኃጥኣን መወለድ ግን ለሞት ነው።


ጻድቁ ግን ከጽ​ድቁ ቢመ​ለስ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም ቢሠራ፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ገው ርኵ​ሰት ሁሉ ቢያ​ደ​ርግ፥ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ልን? የሠ​ራው ጽድቅ ሁሉ አይ​ታ​ሰ​ብ​ለ​ትም፤ በአ​ደ​ረ​ገው ዐመ​ፅና በሠ​ራት ኀጢ​አት በዚ​ያች ይሞ​ታል።


እርሱ ከሰነፎች ጋር ይሞታል፤ ከስንፍናውም ብዛት የተነሣ ሕይወቱ ይጣላል፤ ስለ ስንፍናውም ይጠፋል።


ትእዛዛትን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ መንገዶቹን የሚያቃልል ግን ይጠፋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements