Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 18:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከመውደቅ በፊት የሰው ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ሳይከብርም ይዋረዳል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከውድቀቱ በፊት ሰው ልቡ ይታበያል፤ ትሕትና ግን ክብርን ትቀድማለች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሰው ሳይወድቅ በፊት ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ትዕቢት ጥፋትን ያመጣል፤ ትሕትና ግን ክብርን ያጐናጽፋል። ክብርን ግን ትሕትና ይቀድመዋል።

See the chapter Copy




ምሳሌ 18:12
17 Cross References  

እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።


ትዕቢት ባለበት በዚያ ውርደት አለ፤ የየዋሃን አፍ ግን ጥበብን ይማራል።


“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የጢ​ሮ​ስን አለቃ እን​ዲህ በለው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ልብህ ኰር​ት​ዋል፥ አንተ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሕር መካ​ከል እን​ዲ​ቀ​መጥ እኔም ተቀ​ም​ጫ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና፤ አንተ ሰው ስት​ሆን ልብ​ህን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ ብታ​ደ​ር​ግም አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ህም።


ከጥል በፊት ስድብ ይቀድማል፥ ከመውደቅም በፊት ክፋትን ማወቅ።


ራሱን ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም ያሚ​ያ​ዋ​ርድ ከፍ ይላ​ልና።”


አንተ ሰው ስት​ሆን ለሚ​ገ​ድ​ሉህ ሰዎች፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ትላ​ቸ​ዋ​ለ​ህን? ሰው ነህ እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ህም።


የግ​ብ​ፅም ምድር ባድ​ማና ውድማ ትሆ​ና​ለች፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ፤ አንተ፦ ወንዙ የእኔ ነው፤ የሠ​ራ​ሁ​ትም እኔ ነኝ ብለ​ሃ​ልና።


አሁ​ንም አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ እኔን ባሪ​ያ​ህን በአ​ባቴ በዳ​ዊት ፋንታ አን​ግ​ሠ​ኸ​ኛል፤ እኔም መው​ጫ​ዬ​ንና መግ​ቢ​ያ​ዬን የማ​ላ​ውቅ ታናሽ ብላ​ቴና ነኝ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements