Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 16:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ትዕግሥተኛ ሰው ከኀያል፥ ጥበብ ያለው ሰውም ሰፊ ርስት ካለው፥ በመንፈሱ የሠለጠነ ሰውም ሀገርን ከሚገዛ ሰው ይሻላል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ታጋሽ ሰው ከጦረኛ፣ ስሜቱን የሚገዛም ከተማን በጕልበቱ ከሚይዝ ይበልጣል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ ስሜቱን የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ኀይለኛ ከመሆን ይልቅ ታጋሽ መሆን ይሻላል፤ ብዙ ከተሞችን በጦርነት ድል ነሥቶ ከመያዝ ይልቅ ራስን መቈጣጠር ይበልጣል።

See the chapter Copy




ምሳሌ 16:32
16 Cross References  

ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤


ቍጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ ትዕግሥተኛ ሰው ግን የሆነውን ስንኳ ያጠፋል። ትዕግሥተኛ ሰው ክርክርን ያጠፋል፥ ኀጢአተኛ ሰው ግን ጠብን ፈጽሞ ያነሣል።


ትዕግሥተኛ ሰው ጥበብ የበዛለት ይሆናል፤ ትዕግሥት የጐደለው ሰው ግን ሰነፍ ነው፤


ክፉ​ውን በመ​ል​ካም ሥራ ድል ንሣው እንጂ ክፉ​ውን በክፉ ድል አት​ን​ሣው።


ይቅር ባይ ሰው ይታገሣል፥ መመካቱም ኀጢአተኞችን ይቃወማቸዋል፥


ወደ ተራ​ሮች ይወ​ጣሉ፥ ወደ ሜዳ፥ ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ህ​ላ​ቸው ስፍ​ራም ይወ​ር​ዳሉ፥


እን​ግ​ዲህ እንደ ተወ​ደዱ ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሰሉ።


እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ።


ከተሳዳቢዎች ጋር ምርኮን ከሚካፈል፥ በትሕትና ቍጣን የሚያርቅ ይሻላል።


የደ​ማ​ስቆ ወን​ዞች ባብ​ናና ፋርፋ ከእ​ስ​ራ​ኤል ውኆች ሁሉ አይ​ሻ​ሉ​ምን? ሄጄስ በእ​ነ​ርሱ ውስጥ መጠ​መ​ቅና መን​ጻት አይ​ቻ​ለ​ኝም ኖሮ​አ​ልን?” ብሎ በቍጣ ተመ​ልሶ ሄደ።


መልካም ሽምግልና የክብር አክሊል ነው፥ እርሱም በጽድቅ መንገድ ይገኛል።


የበደለኛ ሰው በደሉ ሁሉ ወደ ጕያው ይመለሳል። ጽድቅ ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።


የነ​ገር ፍጻሜ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ይሻ​ላል፤ ታጋ​ሽም ከልብ ትዕ​ቢ​ተኛ ይሻ​ላል።


በመ​ን​ፈ​ስህ ለቍጣ ችኩል አት​ሁን፥ ቍጣ በሰ​ነ​ፎች ብብት ያር​ፋ​ልና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements