Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 14:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በክፉዎች ዘንድ ጥበብን ትፈልጋለህ፥ አታገኛትምም፤ ዕውቀት ግን በብልሆች ዘንድ በቀላሉ ይገኛል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ፌዘኛ ጥበብን ይሻል፤ ሆኖም አያገኛትም፤ ዕውቀት ግን ለአስተዋዮች በቀላሉ ትገኛለች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ፌዘኛ ሰው ጥበብን ይፈልጋል አያገኛትም፥ ለአስተዋይ ግን እውቀትን ማግኘት አያስቸግረውም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ፌዘኛ ሰው ጥበብን ይፈልጋል፤ አያገኛትም። አስተዋዮች ግን ዕውቀትን በቀላሉ ይገበያሉ።

See the chapter Copy




ምሳሌ 14:6
24 Cross References  

ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።


ዐወ​ቅሁ የሚል ቢኖር፥ ሊያ​ውቅ የሚ​ገ​ባ​ውን ገና አላ​ወ​ቀም።


በሚያውቁ ፊት ሁሉ የቀና ነው፥ ዕውቀትንም ለሚያገኙ ሰዎች የቀና ነው።


ጥበ​በ​ኞች አፍ​ረ​ዋል፤ ደን​ግ​ጠ​ው​ማል፤ ተማ​ር​ከ​ው​ማል፤ እነሆ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጥለ​ዋል፤ ምን ዓይ​ነት ጥበብ አላ​ቸው?


ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም ይሉ ዘንድ፥ ለእ​ር​ሱም ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሕግን ለር​ዳታ ሰጥ​ቶ​አ​ልና።


የዕውቀት ድሃ ጥበብን አይወድድም፤ ነገር ግን ስንፍና ይገዛዋል።


የብልህ ሰው ፊት ዐዋቂ ነው፤ የአላዋቂ ሰው ዐይኖች ግን በምድር ዳርቻ ናቸው።


ጠቢብ እነዚህን በመስማት ጥበብን ይጨምራል፥ አስተዋይ ግን ምክርን ገንዘብ ያደርጋል።


የታመነ ምስክር አይዋሽም፤ የሐሰት ምስክር ግን ሐሰትን ያቀጣጥላል።


በሰነፍ ሰው ፊት ሁሉ ጠማማ ነው፥ የብልሆች ከንፈር ግን የዕውቀት ጋሻ ነው።


ጥበብና መልካም ዕውቀት በብልሆች በር ትገኛለች፤ ብልሆች ከእግዚአብሔር ቃል አይርቁም።


የአፌ ቃላት ሁሉ እውነት ናቸው፤ ጠማማና እንቅፋት በውስጣቸው የለም።


አላዋቂ ሰው የሚዘልፈውን አይወድድም፥ ከጠቢባንም ጋር አይነጋገርም።


ለአላዋቂ ሰው ገንዘብ ለምንድን ነው? አላዋቂ ሰው ጥበብን ገንዘብ ማድረግ አይችልምና፥ ቤቱን የሚያስረዝም ሰው ለራሱ ጥፋትን ይሻል፤ ለመማርም የሚጨንቀው ወደ ክፉ ይወድቃል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements