Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 14:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የዐዋቂ ሰው ልብ ለሰውነቱ ኀዘን ነው፤ ደስ ባለውም ጊዜ ከጥል ጋር ግንኙነት የለውም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እያንዳንዱ ልብ የራሱን መራራ ሐዘን ያውቃል፤ ደስታውንም ማንም ሊጋራው አይችልም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የራሱን ኀዘን ልብ ያውቃል፥ ከደስታውም ጋር ሌላ ሰው አይገናኝም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ደስታህም ሆነ ሐዘንህ የራስህ ነው፤ ማንም የሚካፈልህ የለም።

See the chapter Copy




ምሳሌ 14:10
20 Cross References  

ሁሉ የሚ​ገ​ኝ​ባት፥ ከል​ቡ​ናና ከአ​ሳብ ሁሉ በላይ የም​ት​ሆን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰላም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ልባ​ች​ሁ​ንና አሳ​ባ​ች​ሁን ታጽ​ናው።


ብልህ አገልጋይ የጌታውን ቍጣ ያበርዳል፥ አእምሮ የጐደለውን ሰው ማን ይችለዋል?


ልብ ደስ ሲለው ፊት ይበራል፤ ልብ ሲያዝን ግን ፊት ይጠቍራል።


“ነፍሴ ስለ ተጨ​ነ​ቀች ቃሌን በእ​ን​ጕ​ር​ጕሮ አሰ​ማ​ለሁ፤ ነፍ​ሴም እየ​ተ​ጨ​ነ​ቀች በም​ሬት እና​ገ​ራ​ለሁ።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፤ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል።


እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።


“የሙት ልጆች ትሆኑ ዘንድ አል​ተ​ዋ​ች​ሁም፤ ወደ እና​ንተ እመ​ጣ​ለሁ።


ስለ​ዚ​ህም እኔ አፌን አል​ከ​ለ​ክ​ልም፤ በመ​ን​ፈሴ ጭን​ቀ​ትን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ የነ​ፍ​ሴ​ንም ምሬት በኀ​ዘን እገ​ል​ጣ​ለሁ።


እር​ስ​ዋም በል​ብዋ አዝና አለ​ቀ​ሰች፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለ​የች።


“አሁ​ንስ ነፍሴ ታወ​ከች፤ ግን ምን እላ​ለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚች ሰዓት ነፍ​ሴን አድ​ናት፤ ነገር ግን ስለ​ዚህ ነገር ለዚች ሰዓት ደር​ሻ​ለሁ።


መን​ፈ​ስም አን​ሥቶ ወሰ​ደኝ፤ እኔም በም​ሬ​ትና በመ​ን​ፈሴ ሙቀት ሄድሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በላዬ በር​ትታ ነበር።


እተ​ነ​ፍስ ዘንድ አይ​ተ​ወ​ኝም፤ ነገር ግን መራራ ነገ​ርን አጥ​ግ​ቦ​ኛል።


ወደ ተራ​ራ​ውም ወደ ኤል​ሳዕ ደርሳ እግ​ሮ​ቹን ጨበ​ጠች፤ ግያ​ዝም ሊያ​ር​ቃት መጣ፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “ነፍ​ስዋ አዝ​ና​ለ​ችና ተዋት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያን ከእኔ ሰው​ሮ​ታል፤ አል​ነ​ገ​ረ​ኝ​ምም” አለ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ አለው፥ “የሚ​ወ​ደኝ ቃሌን ይጠ​ብ​ቃል፤ አባ​ቴም ይወ​ደ​ዋል፤ ወደ እር​ሱም መጥ​ተን በእ​ርሱ ዘንድ ማደ​ሪያ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።


እነ​ር​ሱም እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲህ ተባ​ባሉ፥ “በእ​ው​ነት ወን​ድ​ማ​ች​ንን በድ​ለ​ናል፤ እኛን በመ​ማ​ጠን ነፍሱ ስት​ጨ​ነቅ አይ​ተን አል​ሰ​ማ​ነ​ው​ምና፤ ስለ​ዚህ ይህ መከራ መጣ​ብን።”


ሌላ​ውም ሰው መል​ካ​ምን ነገር ከቶ ሳይ​በላ በተ​መ​ረ​ረች ነፍሱ ይሞ​ታል።


ሐናም መልሳ እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አይ​ደ​ለም፤ እኔስ ወራት የባ​ሳት ሴት ነኝ፤ ጠጅና ሌላ የሚ​ያ​ሰ​ክር ነገር አል​ጠ​ጣ​ሁም፤ ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነፍ​ሴን አፈ​ሰ​ስሁ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements